ኢሳይያስ 5:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሔር ወይን ቦታ እርሱ የእስራኤል ቤት ነው፤ ተወዳጁ አዲስ ተክልም የይሁዳ ሰዎች ናቸው፤ ፍርድን ያደርጋል ብየ እጠብቅ ነበር፤ እነሆም፥ ዐመፅን አደረገ፤ ጽድቅንም አይደለም፥ ጩኸትን እንጂ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሰራዊት ጌታ የእግዚአብሔር የወይን ቦታው የእስራኤል ቤት ነው፤ የይሁዳ ሰዎችም የደስታው አትክልት ናቸው። ፍትሕን ፈለገ፤ ነገር ግን ደም ማፍሰስን አየ፤ ጽድቅን ፈለገ፤ ነገር ግን የጭንቅን ጩኸት ሰማ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር የወይን ቦታ የእስራኤል ቤት ነው፤ የይሁዳ ሰዎችም የደስታው አትክልት ናቸው። ፍትሕን ፈለገ፤ ነገር ግን ደም ማፍሰስን አየ፤ ጽድቅን ፈለገ፤ ነገር ግን የጭንቅን ጩኸት ሰማ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህም የሠራዊት አምላክ የወይን ቦታ የተባለው የእስራኤል ሕዝብ ነው፤ እርሱም የይሁዳ ሕዝብ ደስ የሚሰኝበት ተክል ነው። መልካም ሥራ እንዲሠሩ ተስፋ ያደርግ ነበር፤ በዚህ ፈንታ ነፍሰ ገዳዮች ሆኑ፤ ቅን ፍርድ ይሰጣሉ ብሎ ተስፋ ያደርግ ነበር፤ እነርሱ ግን ፍርድን በማጓደላቸው የሕዝቡ ጩኸት በዛ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሔር ወይን ቦታ እርሱ የእስራኤል ቤት ነው፥ የደስታውም አትክልት የይሁዳ ሰዎች ናቸው፥ ፍርድን ተስፋ ያደርግ ነበር፥ እነሆም፥ ደም ማፍሰስ ሆነ፥ ጽድቅንም ይተማመን ነበር፥ እነሆም፥ ጩኸት ሆነ። |
ለሕዝቤም ለእስራኤል ስፍራ አደርጋለሁ፤ እተክላቸውማለሁ፤ ብቻቸውን ይቀመጣሉ፤ ከዚያም በኋላ የሚጠራጠሩት የለም፤ እንደ ቀድሞው ዘመን የኀጢአት ልጅ መከራ አያጸናባቸውም።
እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፥ “በግብፅ ያለውን የሕዝቤን መከራ በእውነት አየሁ፦ ከአሠሪዎቻቸውም የተነሣ ጩኸታቸውን ሰማሁ፤ ሥቃያቸውንም ዐውቄአለሁ፤
እኔም ተመለስሁ፥ ከፀሓይ በታችም የሚደረገውን ግፍ ሁሉ አየሁ፤ እነሆም፥ የተገፉት ሰዎች እንባ ነበረ፤ የሚያጽናናቸውም አልነበረም፤ በሚገፉአቸውም እጅ ኀይል ነበረ። እነርሱን ግን የሚያጽናናቸው አልነበረም።
በራስሽ ላይ ያለው ጠጕርሽ እንደ ቀርሜሎስ ተራራ ነው፤ የጠጕርሽም ሹርባ እንደ ሐምራዊ ሐር ነው፥ ንጉሡም በሹርባው ታስሯል።
ፍርድ መልቶባት የነበረ የታመነችይቱ የጽዮን ከተማ እንዴት ጋለሞታ ሆነች! ጽድቅ አድሮባት ነበር፤ አሁን ግን ወንበዴዎችና ነፍሰ ገዳዮች አሉባት።
ከእግር ጫማ አንሥቶ እስከ ራስ ድረስ ጤና የለውም፤ ቍስልና እበጥ የሚመግልም ነው፤ አልፈረጠም፤ አልተጠገነምም፤ በዘይትም አልለዘበም።
እግዚአብሔር ከሕዝቡ ሽማግሌዎችና ከአለቆቻቸው ጋር ለፍርድ ይመጣል፤ እንዲህም ይላል፥ “ወይኔን አቃጥላችኋል፤ ከድሃው የበዘበዛችሁትም በቤታችሁ አለ፤
ስለዚህ የእስራኤል ቅዱስ እንዲህ ይላል፥ “ይህችን ቃል አቃልላችኋልና፥ በሐሰትና በጠማማነት ተስፋ አድርጋችኋልና፥ አጕረምርማችኋልምና፥ በዚህም ቃል ታምናችኋልና፤
አጥር አጠርሁ፤ በዙሪያውም ቈፈርሁ፤ ድንጋዮችንም ለቅሜ አወጣሁ፤ ምርጥ የሆነውንም ወይን ተከልሁ፤ በመካከሉም ግንብ ሠራሁ፤ ደግሞም የመጥመቂያ ጕድጓድ ማስሁለት፤ ወይንንም ያፈራ ዘንድ ጠበቅሁት፤ ዳሩ ግን እሾህን አፈራ።
በድለናል፤ ዋሽተናልም፤ አምላካችንንም መከተል ትተናል፤ ዐመፃን ተናግረናል፤ ከድተንሃልም፤ የኀጢአትንም ቃል ፀንሰን፤ ከልብ አውጥተናል።
ፍርድን ከመከተል ወደ ኋላ ርቀናል፤ ጽድቅም በሩቅ ቆሞአል፤ እውነትም ከመንገዳቸው ታጥቶአል፤ በቀና መንገድም መሄድ አልቻሉም።
ጽድቅን የሚናገር በእውነትም የሚፈርድ የለም፤ በከንቱ ነገር ታምነዋል፤ የማይጠቅማቸውንም ተናግረዋል፤ ኀጢአትን ፀንሰዋል፤ በደልንም ወልደዋል።
ጐልማሳም ከድንግሊቱ ጋር እንደሚኖር፥ እንዲሁ ልጆችሽ ከአንቺ ጋር ይኖራሉ፤ ሙሽራም በሙሽራዪቱ ደስ እንደሚለው፥ እንዲሁ አምላክሽ በአንቺ ደስ ይለዋል።
ብዙ እረኞች የወይኑን ቦታዬን አጥፍተዋል፤ እድል ፈንታዬንም አርክሰዋል፤ የምወድዳትንም እድል ፈንታ ምድረ በዳ አድርገዋታል።
በአንደኛዪቱ ቅርጫት አስቀድሞ እንደ ደረሰ በለስ የሚመስል እጅግ መልካም በለስ ነበረባት፤ በሁለተኛዪቱም ቅርጫት ከክፋቱ የተነሣ ይበላ ዘንድ የማይቻል እጅግ ክፉ በለስ ነበረባት።
እስራኤል ፍሬው የበዛለት የለመለመ ወይን ነው፤ እንደ ፍሬው ብዛት መሠዊያዉን አብዝቶአል፤ እንደ ምድሩም ማማር መጠን ሐውልቶችን ሠርተዋል።
ሰው ሆይ፥ መልካሙን ነግሮሃል፥ እግዚአብሔርም ከአንተ ዘንድ የሚሻው ምንድር ነው? ፍርድን ታደርግ ዘንድ፥ ምሕረትንም ትወድድ ዘንድ፥ ከአምላክህም ጋር በትሕትና ትሄድ ዘንድ አይደለምን?
አምላክሽ እግዚአብሔር በመካከልሽ ታዳጊ ኃያል ነው፣ በደስታ በአንቺ ደስ ይለዋል፥ በፍቅሩም ያርፋል፥ በእልልታም በአንቺ ደስ ይለዋል ይባላል።
“እናንተ ግብዞች ጻፎችና ፈሪሳውያን! ከአዝሙድና ከእንስላል ከከሙንም አሥራት ስለምታወጡ፥ ፍርድንና ምሕረትን ታማኝነትንም፥ በሕግ ያለውን ዋና ነገር ስለምትተዉ፥ ወዮላችሁ፤ ሌላውን ሳትተዉ ይህን ልታደርጉ ይገባችሁ ነበር።
እንግዲህ እግዚአብሔር በመዓልትና በሌሊት ወደ እርሱ ለሚጮኹ ለወዳጆቹ አይፈርድምን? ወይስ ቸል ይላቸዋልን?
በእኔ ያለውን፥ ፍሬ የማያፈራውን ቅርንጫፍም ሁሉ ያስወግደዋል፤ የሚያፈራውን ቅርንጫፍ ሁሉ ግን በብዙ እንዲያፈራ ያጠራዋል።
ሰባተኛው ዓመት የምሕረት ዓመት ቅርብ ነው፤ አልሰጠውምም ብለህ ክፉ ዐሳብ በልብህ እንዳታስብ ለራስህ ዕወቅ። ወንድምህም ዐይኑን በአንተ ላይ ያከፋል፤ እርሱም ወደ እግዚአብሔር በአንተ ላይ ይጮሃል፤ ኀጢአትም ይሆንብሃል።