Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኢሳይያስ 62:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 ጐል​ማ​ሳም ከድ​ን​ግ​ሊቱ ጋር እን​ደ​ሚ​ኖር፥ እን​ዲሁ ልጆ​ችሽ ከአ​ንቺ ጋር ይኖ​ራሉ፤ ሙሽ​ራም በሙ​ሽ​ራ​ዪቱ ደስ እን​ደ​ሚ​ለው፥ እን​ዲሁ አም​ላ​ክሽ በአ​ንቺ ደስ ይለ​ዋል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 ጕልማሳ ድንግሊቱን እንደሚያገባ፣ ልጆችሽ እንዲሁ ያገቡሻል፤ ሙሽራ በሙሽራዪቱ ደስ እንደሚለው፣ አምላክሽም በአንቺ ደስ ይለዋል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 ጎልማሳም ድንግሊቱን እንደሚያገባ፥ እንዲሁ ልጆችሽ ያገቡሻል፤ ሙሽራም በሙሽራይቱ ደስ እንደሚለው፥ እንዲሁ አምላክሽ በአንቺ ደስ ይለዋል።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 ጐልማሳ ድንግሊቱን ሙሽራ አድርጎ እንደሚወስድ፥ የፈጠረሽ እግዚአብሔርም ለአንቺ እንደ ባል ይሆንልሻል፤ ወንዱም ሙሽራ በሴትዋ ሙሽራ ደስ እንደሚሰኝ፥ እግዚአብሔርም በአንቺ ደስ ይለዋል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 ጕልማሳም ድንግሊቱን እንደሚያገባ፥ እንዲሁ ልጆችሽ ያገቡሻል፥ ሙሽራም በሙሽራይቱ ደስ እንደሚለው፥ እንዲሁ አምላክሽ በአንቺ ደስ ይለዋል።

Ver Capítulo Copiar




ኢሳይያስ 62:5
12 Referencias Cruzadas  

እና​ንት የጽ​ዮን ቈነ​ጃ​ጅት፥ እናቱ በሠ​ርጉ ቀን በልቡ ደስታ ቀን ያቀ​ዳ​ጀ​ች​ውን አክ​ሊል ደፍቶ ንጉሥ ሰሎ​ሞ​ንን ታዩ ዘንድ ውጡ።


ሙሽ​ሪት ሆይ፥ ከሊ​ባ​ኖስ ነዪ፤ ከሊ​ባ​ኖስ ነዪ፤ ከሃ​ይ​ማ​ኖት ራስ ከሳ​ኔ​ርና ከኤ​ር​ሞን ራስ፥ ከአ​ን​በ​ሶች ጕድ​ጓድ፥ ከነ​ብ​ሮ​ችም ተራራ ተመ​ል​ከቺ።


ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ፥ “የተ​ተ​ወች” አት​ባ​ዪም፤ ምድ​ር​ሽም ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ፥ “ውድማ” አት​ባ​ልም፤ ነገር ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በአ​ንቺ ደስ ብሎ​ታ​ልና፥ ምድ​ር​ሽም ባል ታገ​ባ​ለ​ችና አንቺ፥ “ደስ​ታዬ የሚ​ኖ​ር​ባት” ትባ​ያ​ለሽ፤ ምድ​ር​ሽም፥ “ባል ያገ​ባች” ትባ​ላ​ለች።


እኔም በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ሐሤ​ትን አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ በሕ​ዝ​ቤም ደስ ይለ​ኛል፤ ከዚ​ያም ወዲያ የል​ቅሶ ድም​ፅና የዋ​ይታ ድምፅ በው​ስ​ጥዋ አይ​ሰ​ማም።


ለእ​ነ​ር​ሱም መል​ካ​ምን በማ​ድ​ረግ ይቅር እላ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ በእ​ው​ነ​ትም በፍ​ጹም ልቤና በፍ​ጹም ነፍሴ በዚ​ህች ምድር እተ​ክ​ላ​ቸ​ዋ​ለሁ።


ለዘ​ለ​ዓ​ለ​ምም ለእኔ እን​ድ​ት​ሆኚ አጭ​ሻ​ለሁ፤ በጽ​ድ​ቅና በፍ​ርድ በም​ሕ​ረ​ትና በይ​ቅ​ርታ አጭ​ሻ​ለሁ።


በዚ​ያም ቀን እን​ዲህ ይሆ​ናል፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ለሰ​ማይ እመ​ል​ሳ​ለሁ፤ ሰማ​ይም ለም​ድር ይመ​ል​ሳል፤


አምላክሽ እግዚአብሔር በመካከልሽ ታዳጊ ኃያል ነው፣ በደስታ በአንቺ ደስ ይለዋል፥ በፍቅሩም ያርፋል፥ በእልልታም በአንቺ ደስ ይለዋል ይባላል።


የተድላ ምድር ትሆናላችሁና አሕዛብ ሁሉ ብፁዓን ብለው ይጠሩአችኋል፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።


የእ​ም​ነ​ታ​ች​ን​ንም ራስና ፈጻ​ሚ​ውን ኢየ​ሱ​ስን እን​ከ​ተ​ለው፤ እርሱ ነው​ርን ንቆ፥ በፊ​ቱም ስላ​ለው ደስታ በመ​ስ​ቀል ታግሦ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዙፋን ቀኝ ተቀ​ም​ጦ​አ​ልና።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos