Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኢሳይያስ 1:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 ከእ​ግር ጫማ አን​ሥቶ እስከ ራስ ድረስ ጤና የለ​ውም፤ ቍስ​ልና እበጥ የሚ​መ​ግ​ልም ነው፤ አል​ፈ​ረ​ጠም፤ አል​ተ​ጠ​ገ​ነ​ምም፤ በዘ​ይ​ትም አል​ለ​ዘ​በም።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 ከእግር ጥፍራችሁ እስከ ራስ ጠጕራችሁ ጤና የላችሁም፤ ቍስልና ዕባጭ እንዲሁም እዥ ብቻ ነው፤ አልታጠበም፤ አልታሰረም፤ በዘይትም አልለዘበም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 ከእግር ጥፍራችሁ እስከ ራስ ጠጉራችሁ ጤና የላችሁም፤ ቁስልና ዕባጭ እንዲሁም እዥ ብቻ ነው፤ አልታጠበም፤ አልታሰረም፤ በዘይትም አልለዘበም።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 ከዚህም የተነሣ ከእግር ጥፍር እስከ ራስ ጠጒር ድረስ ጤናማ የሆነ የአካል ክፍል የላችሁም፤ ቊስልና እባጭ መግልም የሞላበት ሆኖአል፤ ይህም ቊስላችሁ አልፈረጠም፤ አልታሰረም፤ ወይም በዘይት አለሰለሰም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 ከእግር ጫማ አንስቶ እስከ ራስ ድረስ ጤና የለውም፥ ቍስልና እበጥ የሚመግልም ነው፥ አልፈረጠም፥ አልተጠገነም፥ በዘይትም አልለዘበም።

Ver Capítulo Copiar




ኢሳይያስ 1:6
20 Referencias Cruzadas  

የሕ​ዝ​ቤ​ንም ስብ​ራት በጥ​ቂቱ ይፈ​ው​ሳሉ፤ ሰላም ሳይ​ሆን፦ ሰላም ሰላም ይላሉ።


ኢየሱስም ሰምቶ “ሕመምተኞች እንጂ ባለ ጤነኞች ባለ መድኃኒት አያስፈልጋቸውም፤


እነሆ ፈው​ስ​ንና መድ​ኀ​ኒ​ትን እሰ​ጣ​ታ​ለሁ፤ እፈ​ው​ሳ​ታ​ለ​ሁም፤ የሰ​ላ​ም​ንና የእ​ው​ነ​ት​ንም መን​ገድ እገ​ል​ጥ​ላ​ቸ​ዋ​ለሁ።


ወደ እር​ሱም ቀረበ፤ ቍስ​ሉ​ንም አጋ​ጥሞ አሰ​ረ​ለት፤ በቍ​ስሉ ላይም ወይ​ንና ዘይት ጨመ​ረ​ለት፤ በአ​ህ​ያ​ውም ላይ አስ​ቀ​ምጦ እን​ዲ​ፈ​ው​ሰው የእ​ን​ግ​ዶ​ችን ቤት ወደ​ሚ​ጠ​ብ​ቀው ወሰ​ደው፤ የሚ​ድ​ን​በ​ት​ንም ዐሰበ።


ነገር ግን ስሜን ለምትፈሩት ለእናንተ የጽድቅ ፀሐይ ትወጣላችኋለች፥ ፈውስም በክንፎችዋ ውስጥ ይሆናል፣ እናንተም ትወጣላችሁ፥ እንደ ሰባም እምቦሳ ትፈነጫላችሁ።


አፌን በም​ሳሌ እከ​ፍ​ታ​ለሁ፤ ከቀ​ድሞ ጀምሮ ያለ​ው​ንም ምሳሌ እና​ገ​ራ​ለሁ።


እርሱ ይሰ​ብ​ራል፥ ዳግ​መ​ኛም ይጠ​ግ​ናል፤ ይቀ​ሥ​ፋል፥ እጆ​ቹም ይፈ​ው​ሳሉ።


ስብራትህ አይፈወስም፥ ቁስልህም ክፉ ነው፣ ወሬህንም የሚሰሙ ሁሉ እጃቸውን በአንተ ላይ ያጨበጭባሉ፣ ክፋትህ ሁልጊዜ ያላለፈችበት ሰው ማን ነውና?


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ስብ​ራ​ትህ የማ​ይ​ፈ​ወስ፥ ቍስ​ል​ህም ክፉ ነው።


በእ​ስ​ራ​ኤል ሁሉ ዘንድ እንደ አቤ​ሴ​ሎም በው​በቱ ያማረ ሰው አል​ነ​በ​ረም፤ ከእ​ግሩ እስከ ራሱ ድረስ ነውር አል​ነ​በ​ረ​በ​ትም።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የሕ​ዝ​ቡን ስብ​ራት በጠ​ገነ ዕለት፥ በመ​ቅ​ሠ​ፍቱ የቈ​ሰ​ለ​ው​ንም በፈ​ወሰ ዕለት፥ የጨ​ረቃ ብር​ሃን እንደ ፀሐይ ብር​ሃን፥ የፀ​ሐ​ይም ብር​ሃን እንደ ሰባት ቀን ብር​ሃን ሰባት እጥፍ ይሆ​ናል።


“የሰው ልብ ከሁሉ ይልቅ ጥልቅ ነው፤ ማንስ ያው​ቀ​ዋል?


በጕ​ድ​ጓድ ውኃ እን​ደ​ሚ​ፈ​ልቅ፥ እን​ዲሁ ክፋቷ ከእ​ር​ስዋ ዘንድ ይፈ​ል​ቃል፤ ግፍና ቅሚያ በእ​ር​ስዋ ዘንድ ይሰ​ማል፤ ደዌና ቍስ​ልም ሁል​ጊዜ በፊቷ አለ።


ቍስ​ልህ የማ​ይ​ፈ​ወስ ሆኖ​አ​ልና ስለ ስብ​ራ​ትህ ለምን ትጮ​ኻ​ለህ? በደ​ልህ ታላቅ ስለ ሆነ፥ ኀጢ​አ​ት​ህም ስለ በዛ፥ ይህን አድ​ር​ጌ​ብ​ሃ​ለሁ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios