ነገር ግን በእርስዋ ሄዱ እንጂ እስራኤልን ካሳተበት ከኢዮርብዓም ቤት ኀጢአት አልራቁም፤ ደግሞም የማምለኪያ ዐፀድ በሰማርያ ቆሞ ነበረ።
ኢሳይያስ 26:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በምድር ጽድቅን የማይማርና መልካምን የማያደርግ ኃጥእ አልቆአልና፥ የእግዚአብሔርን ክብር እንዳያይ ኀጢአተኛን ያስወግዱታል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ክፉዎች ርኅራኄ ቢደረግላቸው እንኳ፣ ጽድቅን አይማሩም፤ በቅንነት ምድር እንኳ ክፋትን ያደርጋሉ፤ የእግዚአብሔርንም ግርማ አያስተውሉም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ክፉዎች እድል ቢሰጣቸው እንኳን ጽድቅን አይማሩም፤ በቅኖች ምድር ክፉን ነገር ያደርጋሉ፥ የጌታንም ግርማ አያዩም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ክፉ ሰዎች ቸርነት ብታደርግላቸው እንኳ መልካም መሥራትን አይማሩም፤ በዚህ ጽድቅ በሰፈነበት ምድር እያሉ እንኳ ክፋት ከማድረግ አይቈጠቡም፤ ታላቅነትህንም አይገነዘቡም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለኃጢአተኛ ሞገስ ቢደረግለት ጽድቅን አይማርም፥ በቅኖች ምድር ክፉን ነገር ያደርጋል፥ የእግዚአብሔርንም ግርማ አያይም። |
ነገር ግን በእርስዋ ሄዱ እንጂ እስራኤልን ካሳተበት ከኢዮርብዓም ቤት ኀጢአት አልራቁም፤ ደግሞም የማምለኪያ ዐፀድ በሰማርያ ቆሞ ነበረ።
ፈርዖንም ዝናቡ፥ በረዶውም፥ ነጐድጓዱም ጸጥ እንደ አለ በአየ ጊዜ በደልን ጨመረ፤ እርሱና ሹሞቹም ልባቸውን አደነደኑ።
ክፉን ከሚያደርጉ ወገን ፈጥኖ ክርክርን የሚያደርግ የለምና፤ ስለዚህ የሰው ልጆች ልብ በእነርሱ ክፉን ለመሥራት ጠነከረ።
ፍርድ መልቶባት የነበረ የታመነችይቱ የጽዮን ከተማ እንዴት ጋለሞታ ሆነች! ጽድቅ አድሮባት ነበር፤ አሁን ግን ወንበዴዎችና ነፍሰ ገዳዮች አሉባት።
አሁንም ምድርን ያነዋውጣት ዘንድ በተነሣ ጊዜ እግዚአብሔርን ከመፍራትና ከግርማው ክብር የተነሣ ወደ ድንጋይ ዋሻ ግቡ፤ በመሬት ውስጥም ተሸሸጉ።
ምድርም በሚቀመጡባት ሰዎች ምክንያት በደለች፤ ሕጉን ተላልፈዋልና፥ ሥርዐቱንም ለውጠዋልና፥ የዘለዓለሙንም ቃል ኪዳን አፍርሰዋልና።
በዚያም ቀን እንዲህ ይሆናል፤ ታላቅ መለከት ይነፋል፤ በአሦርም የጠፉ፥ በግብፅ ምድርም የተሰደዱ ይመጣሉ፤ በተቀደሰውም ተራራ በኢየሩሳሌም ለእግዚአብሔር ይሰግዳሉ።
ሰነፍ ግን ስንፍናን ይናገራል፤ ልቡም ዐመፅን ያደርግ ዘንድ፥ በእግዚአብሔር ላይ ስሕተትን ይናገር ዘንድ፥ የተራበችውንም ሰውነት ይበትን ዘንድ፥ የተጠማችንም ነፍስ ባዶ ያደርግ ዘንድ ከንቱን ያስባል።
በዐመፃቸው ነገር ድሃውን ይገድሉት ዘንድ፥ የድሆችንም ፍርድ ይገለብጡ ዘንድ የክፉዎች ሕሊና ዐመፅን ትመክራለች።
በመሰንቆና በበገና፥ በከበሮና በእምቢልታም እየዘፈኑ የወይን ጠጅን ይጠጣሉ፤ የእግዚአብሔርን ሥራ ግን አልተመለከቱም፤ የእጁንም ሥራ አላስተዋሉም።
ፍሬዋንና በረከቷንም ትበሉ ዘንድ ወደ ቀርሜሎስ አገባኋችሁ፤ ነገር ግን በገባችሁ ጊዜ ምድሬን አረከሳችሁ፤ ርስቴንም አጐሳቈላችሁ።
የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “ምርኮአቸውን በመለስሁ ጊዜ በይሁዳ ሀገር በከተሞችዋ፦ የጽድቅ ማደሪያ ሆይ! የቅድስና ተራራ ሆይ! እግዚአብሔር ይባርክህ የሚል ነገርን እንደ ገና ይናገራሉ።
ያዕቆብ በላ፤ ጠገበም፤ የተወደደውን ጥጋብ አቀናጣው፤ ሰባ፥ ወፈረ፥ ሰፋ፤ የፈጠረውንም እግዚአሔርን ተወ፤ ከሕይወቱ ከእግዚአብሔርም ራቀ።
ሳሙኤልም ሳኦልን አለው፥ “በፊቱ ምንም ታናሽ ብትሆን ለእስራኤል ነገዶች አለቃ አልሆንህምን? እግዚአብሔርም በእስራኤል ላይ ንጉሥ ትሆን ዘንድ ቀባህ።