Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኢሳይያስ 26:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 አቤቱ፥ አም​ላኬ ሆይ፥ ትእ​ዛ​ዝህ በም​ድር ላይ ብር​ሃን ነውና ነፍሴ በሌ​ሊት ወደ አንተ ትገ​ሠ​ግ​ሣ​ለች። በም​ድር የም​ት​ኖ​ሩም ጽድቅ መሥ​ራ​ትን ተማሩ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 ነፍሴ በሌሊት ትናፍቅሃለች፤ መንፈሴም በውስጤ ትፈልግሃለች። ፍርድህ ወደ ምድር በመጣ ጊዜ፣ የዓለም ሕዝቦች ጽድቅን ይማራሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 ፍርድህን በምድር ላይ በፈረድክ ጊዜ በዓለም የሚኖሩ ጽድቅን ይማራሉና ነፍሴ በሌሊት ትናፍቅሃለች፥ መንፈሴም በውስጤ ወደ አንተ ትገሠግሣለች።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 ፍርድህ በምድር ላይ በሚሰፍን ጊዜ የዓለም ሕዝቦች እውነትን ይማራሉ። ነፍሴ በሌሊት አንተን ትናፍቃለች፤ በውስጤም ያለው መንፈስ አንተን ትሻለች።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 ፍርድህን በምድር ባደረግህ ጊዜ በዓለም የሚኖሩ ጽድቅን ይማራሉና ነፍሴ በሌሊት ትናፍቅሃለች፥ መንፈሴም በውስጤ ወደ አንተ ትገሠግሣለች።

Ver Capítulo Copiar




ኢሳይያስ 26:9
28 Referencias Cruzadas  

እርሱ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ችን ነው፤ ፍርዱ በም​ድር ሁሉ ነው።


አባ​ቶ​ቻ​ችን በግ​ብፅ ሀገር ሳሉ ተአ​ም​ራ​ት​ህን አላ​ስ​ተ​ዋ​ሉም፥ የም​ሕ​ረ​ት​ህ​ንም ብዛት አላ​ሰ​ቡም፤ በኤ​ር​ትራ ባሕር ባለፉ ጊዜ አስ​መ​ረ​ሩህ።


ሕግ​ህን እን​ዳ​ይ​ረሱ አት​ግ​ደ​ላ​ቸው፤ አቤቱ፥ አም​ላ​ኬና ረዳቴ፥ በኀ​ይ​ልህ በት​ና​ቸው፥ አዋ​ር​ዳ​ቸ​ውም።


አቤቱ፥ ወደ አንተ የለ​መ​ን​ሁ​ትን ጸሎ​ቴን ስማኝ፥ ከጠ​ላ​ትም ጥር​ጥር ነፍ​ሴን አድ​ናት።


ለእ​ነ​ርሱ ለራ​ሳ​ቸው ክፉ ነገ​ርን አጸኑ፤ ወጥ​መ​ድን ይሰ​ውሩ ዘንድ ተማ​ከሩ፤ የሚ​ያ​ም​ንም የለም ይላሉ።


ምድ​ርን ጐበ​ኘ​ሃት አረ​ካ​ሃ​ትም፥ ብል​ጽ​ግ​ና​ዋ​ንም እጅግ አበ​ዛህ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወንዝ ውኆ​ችን የተ​መላ ነው፤ ምግ​ባ​ቸ​ውን አዘ​ጋ​ጀህ፥ እን​ዲሁ ታሰ​ና​ዳ​ለ​ህና።


እኔ የሚወድዱኝን እወድዳለሁ፥ እኔንም የሚሹ ሞገስን ያገኛሉ።


ስለ​ዚ​ህም የማ​ም​ለ​ኪያ ዐፀ​ዶ​ችና የፀ​ሐይ ምስ​ሎች ዳግ​መኛ እን​ዳ​ይ​ነሡ የመ​ሠ​ዊ​ያ​ውን ድን​ጋይ ሁሉ እንደ ደቀቀ እንደ ኖራ ድን​ጋይ ባደ​ረገ ጊዜ ፥ እን​ዲሁ የያ​ዕ​ቆብ በደል ይሰ​ረ​ያል፤ ይህም ኀጢ​አ​ትን የማ​ስ​ወ​ገድ ፍሬ ሁሉ ነው።


ከእ​ና​ንተ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሚ​ፈራ፥ ማን ነው? የባ​ሪ​ያ​ው​ንም ቃል ይስማ፤ በጨ​ለ​ማም የም​ት​ሄዱ፥ ብር​ሃ​ንም የሌ​ላ​ችሁ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም ታመኑ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ተደ​ገፉ፤


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሚ​ገ​ኝ​በት ጊዜ ፈል​ጉት፤ ቀር​ቦም ሳለ ጥሩት፤


ቆፍ። ተነሺ፤ በሌ​ሊት በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ሰዓት ጩኺ፥ በጌ​ታም ፊት ልብ​ሽን እንደ ውኃ አፍ​ስሺ፤ በጎ​ዳና ሁሉ ራስ ላይ በራብ ስለ ደከሙ ስለ ሕፃ​ና​ትሽ ነፍስ እጆ​ች​ሽን ወደ እርሱ አንሺ።


ጤት። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለሚ​ታ​ገ​ሡት ቸር ነው፤


በቍ​ጣ​ዬና በመ​ቅ​ሠ​ፍቴ በተ​በ​ቀ​ል​ሁሽ ጊዜ በዙ​ሪ​ያሽ በአሉ በአ​ሕ​ዛብ ዘንድ ትጨ​ነ​ቂ​ያ​ለሽ፤ ትደ​ነ​ግ​ጫ​ለ​ሽም፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይህን ተና​ግ​ሬ​አ​ለሁ።


እስ​ኪ​ጠፉ ድረስ፥ ፊቴ​ንም እስ​ኪሹ ድረስ እሄ​ዳ​ለሁ፤ ወደ ስፍ​ራ​ዬም እመ​ለ​ሳ​ለሁ።


ነገር ግን አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ፥ ይህም ሁሉ ይጨመርላችኋል።


ማለዳም ተነሥቶ ገና ሌሊት ሳለ ወጣ፤ ወደ ምድረ በዳም ሄዶ በዚያ ጸለየ።


በዚ​ያም ወራት ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ሊጸ​ልይ ወደ ተራራ ወጣ፤ ሌሊ​ቱን ሁሉ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይጸ​ልይ ነበር፤


በዚያም ሰዓት ታላቅ የምድር መናወጥ ሆነ፤ ከከተማይቱም ዐሥረኛው እጅ ወደቀ፤ በመናወጥም ሰባት ሺህ ሰዎች ተገደሉ፤ የቀሩትንም ፍርሃት ያዛቸው፤ ለሰማዩም አምላክ ክብር ሰጡ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos