Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




መክብብ 8:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 ክፉን ከሚ​ያ​ደ​ርጉ ወገን ፈጥኖ ክር​ክ​ርን የሚ​ያ​ደ​ርግ የለ​ምና፤ ስለ​ዚህ የሰው ልጆች ልብ በእ​ነ​ርሱ ክፉን ለመ​ሥ​ራት ጠነ​ከረ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 በወንጀል ላይ ባፋጣኝ ፍርድ ካልተሰጠ፣ የሰዎች ልብ ክፉን በማድረግ ዕቅድ ይሞላል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 በክፉ ሥራ ላይ ፈጥኖ ፍርድ አይበየንምና በሰው ልጆች ልብ ውስጥ ክፉን መሥራት ጠነከረ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 ሰዎች ሆን ብለው ወንጀል የሚሠሩት ለምንድን ነው? የዚህ ምክንያት ሌላ ሳይሆን ወንጀል በሚሠሩ ሰዎች ላይ ፈጣን የቅጣት ፍርድ ባለመሰጠቱ ነው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 በክፉ ሥራ ላይ ፈጥኖ ፍርድ አይፈረድምና ስለዚህ በሰው ልጆች ውስጥ ልባቸው ክፉን ለመሥራት ጠነከረ።

Ver Capítulo Copiar




መክብብ 8:11
19 Referencias Cruzadas  

በም​ድር ጽድ​ቅን የማ​ይ​ማ​ርና መል​ካ​ምን የማ​ያ​ደ​ርግ ኃጥእ አል​ቆ​አ​ልና፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ክብር እን​ዳ​ያይ ኀጢ​አ​ተ​ኛን ያስ​ወ​ግ​ዱ​ታል።


ወጥ​መድ በኃ​ጥ​ኣን ላይ ይዘ​ን​ባል፤ እሳ​ትና ዲን፥ ዐውሎ ነፋ​ስም የጽ​ዋ​ቸው እድል ፋንታ ነው።


“ሞአብ ከል​ጅ​ነቷ ጀምራ ዐረ​ፈች፤ በክ​ብ​ር​ዋም ቅም​ጥል ነበ​ረች፤ ወይ​ን​ዋም ከዕቃ ወደ ዕቃ አል​ተ​ገ​ላ​በ​ጠም፤ ወደ ምር​ኮም አል​ሄ​ደ​ችም፤ ስለ​ዚህ ቃናው በእ​ር​ስዋ ውስጥ ቀር​ቶ​አል፤ መዓ​ዛ​ዋም አል​ተ​ለ​ወ​ጠም።


ፈር​ዖ​ንም ጸጥታ እንደ ሆነ በአየ ጊዜ ልቡ ደነ​ደነ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እንደ ተና​ገ​ረው አል​ሰ​ማ​ቸ​ውም።


ሐሰት የተ​ና​ገ​ር​ሽው፥ እኔ​ንም ያላ​ሰ​ብ​ሽው፥ በል​ብ​ሽም ነገ​ሩን ያላ​ኖ​ር​ሽው ማንን ሰግ​ተሽ ነው? ማን​ንስ ፈር​ተሽ ነው? እኔም ዝም አል​ሁሽ፤ አን​ቺም አል​ፈ​ራ​ሽ​ኝም።


ስለ​ዚህ እና​ንተ የይ​ሁዳ ቅሬታ ሆይ! አሁን እን​ግ​ዲህ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስሙ፤ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ወደ ግብ​ፅም ትገቡ ዘንድ በዚ​ያም ትቀ​መጡ ዘንድ ፊታ​ች​ሁን ብታ​ቀኑ፤


ፈር​ዖ​ንም በዚህ ጊዜ ደግሞ ልቡን አደ​ነ​ደነ፤ ሕዝ​ቡ​ንም አል​ለ​ቀ​ቀም።


ጌታም በፊቱ አለፈ፥ “ስሜም ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ መሓሪ፥ ይቅር ባይ፥ ከመ​ዓት የራቀ ምሕ​ረቱ የበዛ ጻድቅ፥


በደ​ብ​ዳ​ቤ​ውም፥ “ኦር​ዮን ጽኑ ሰልፍ ባለ​በት በፊ​ተ​ኛው ስፍራ አቁ​ሙት፤ ተወ​ግ​ቶም ይሞት ዘንድ ከኋላ ሽሹ” ብሎ ጻፈ።


ከፀ​ሓይ በታች የተ​ደ​ረ​ገው ክፉ ሁሉ ለሁሉ ነው፤ የሁሉ ድርሻ አንድ ነውና። ደግ​ሞም የሰው ልጆች ልብ ክፋ​ትን ትሞ​ላ​ለች፥ በሕ​ይ​ወ​ታ​ቸው ሳሉ ሁከት በል​ባ​ቸው አለ፥ ከዚ​ያም በኋላ ወደ ሙታን ይወ​ር​ዳሉ።


በታ​መ​መም ጊዜ መዳ​ንን ተስፋ አያ​ደ​ር​ግም። ነገር ግን እርሱ በሕ​ማሙ ይሞ​ታል።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በቤተ መቅ​ደሱ ነው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዙፋኑ በሰ​ማይ ነው፤ ዐይ​ኖ​ቹም ወደ ድሃ ይመ​ለ​ከ​ታሉ፤ ቅን​ድ​ቦ​ቹም የሰው ልጆ​ችን ይመ​ረ​ም​ራሉ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios