የአሦርም ንጉሥ ሰማው፤ የአሦርም ንጉሥ ወደ ደማስቆ ወጣ፤ ያዛትም፤ ሕዝብዋንም ወደ ቂር አፈለሳቸው፤ ረአሶንንም ገደለው።
ኢሳይያስ 17:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኤፍሬም የሚጠጋበት ምሽግ አይኖርም፤ ከእንግዲህም ወዲያ ንጉሥ በደማስቆ አይነግሥም። የሶርያ ቅሬታ ሆይ፥ ከእስራኤል ልጆች ከክብራቸው የምትሻል አይደለህም” ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የተመሸገ ከተማ ከኤፍሬም፣ የመንግሥት ሥልጣን ከደማስቆ ይወርዳል፤ የሶርያም ቅሬታ እንደ እስራኤላውያን ክብር ይሆናል” ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ምሽግም ከኤፍሬም፥ መንግሥትም ከደማስቆ ይወገዳል፤ የሶርያም ትሩፍ እንደ እስራኤል ልጆች ክብር ይሆናል፤ ይላል የሠራዊት ጌታ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እስራኤል ያለ መከላከያ ትቀራለች፤ ደማስቆም ነጻነትዋን ትገፈፋለች፤ ከጥፋት የተረፉ እነዚያ ሶርያውያን እንደ እስራኤል ሕዝብ የተዋረዱ ይሆናሉ፤ እኔ የሠራዊት አምላክ ይህን ተናግሬአለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ምሽግም ከኤፍሬም፥ መንግሥትም ከደማስቆ ተወገደች የሶርያም ቅሬታ እንደ እስራኤል ልጆች ክብር ይሆናል ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር። |
የአሦርም ንጉሥ ሰማው፤ የአሦርም ንጉሥ ወደ ደማስቆ ወጣ፤ ያዛትም፤ ሕዝብዋንም ወደ ቂር አፈለሳቸው፤ ረአሶንንም ገደለው።
በሆሴዕም በዘጠነኛው ዓመት የአሦር ንጉሥ ሰማርያን ያዘ፤ እስራኤልንም ወደ አሶር አፈለሰ፤ በአላሔና በአቦር፤ በጎዛንም ወንዝ፤ በሜዶንም ከተሞች አኖራቸው።
እንደ ሔማት አርፋድ፥ እንደ አርፋድ ሴፋሩሔም፥ እንደ ሴፋሩሔም ካሌና፥ እንደ ካሌናም ደማስቆ፥ እንደ ደማስቆም ሰማርያ አይደለችምን?
አሁንም እንዲህ እላለሁ፤ በሦስት ዓመት ውስጥ እንደ ምንደኛ ዓመት የሞዓብ ክብር ከብዙ ሀብትዋ ጋር ይዋረዳል፤ በቍጥርም ጥቂት ይቀራል፤ ክብርዋም አይገኝም።
ከተሞችን ትቢያ አደረግህ፤ የተመሸጉ ከተሞችን፥ የኃጥኣንንም መሠረት አፈረስህ፤ ከተሞቻቸውም ለዘለዓለም አይሠሩም።
የአራም ራስ ደማስቆ ነው፤ የደማስቆም ራስ ረአሶን ነው፤ በስድሳ አምስት ዓመት ውስጥ የኤፍሬም መንግሥት ከሕዝብ ይጠፋል፤
እግዚአብሔርም፥ “ከጥቂት ዘመን በኋላ የኢይዝራኤልን ደም በይሁዳ ቤት ላይ እበቀላለሁና፥ ከእስራኤልም ቤት መንግሥትን እሽራለሁና ስሙን ኢይዝራኤል ብለህ ጥራው፤
ደግሞ ፀነሰች፤ ሴት ልጅንም ወለደች። እግዚአብሔርም፥ “መለየትን እለያቸዋለሁ እንጂ ይቅር እላቸው ዘንድ የእስራኤልን ቤት ከእንግዲህ ወዲህ አልምራቸውምና ስምዋን ኢሥህልት ብለህ ጥራት፤
በሕዝብህም መካከል ጥፋት ይነሣል፤ እናትም በልጆችዋ ላይ በተጣለች ጊዜ የሰልማን አለቃ ቤትአርብኤልን በጦርነት ቀን እንዳፈረሰ፥ አምባዎችህ ሁሉ ይፈርሳሉ።
የእስራኤል ልጆች ያለ ንጉሥና ያለ አለቃ፥ ያለ መሥዋዕትና ያለ ምሥዋዕ፤ ያለ ካህንና ያለ ራእይ፤ ያለ ኤፉድና ያለ ተራፊም ብዙ ወራት ይቀመጣሉና፤
ዳን ሆይ፥ ሕያው አምላክህን! ደግሞም፦ ሕያው የቤርሳቤህን አምላክ ብለው በሰማርያ መማፀኛ የሚምሉ፥ እነርሱ ይወድቃሉ፥ ደግሞም አይነሡም።”