በዚያም ስፍራ ባረከው። ያዕቆብም፥ “እግዚአብሔርን ፊት ለፊት አየሁ፤ ሰውነቴም ዳነች” ሲል የዚያን ቦታ ስም “ራእየ እግዚአብሔር” ብሎ ጠራው።
ዕብራውያን 12:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከሁሉ ጋር ወደ ሰላም ሩጡ፤ ቅድስናችሁንም አትተዉ፤ ያለ እርሱ ግን እግዚአብሔርን የሚያየው የለም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከሰው ሁሉ ጋራ በሰላም ለመኖር የሚቻላችሁን ሁሉ አድርጉ፤ ለመቀደስም ፈልጉ፤ ያለ ቅድስና ማንም ጌታን ማየት አይችልም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከሰው ሁሉ ጋር በሰላም ለመኖር ጣሩ፤ ያለ ቅድስናም ጌታን ሊያይ የሚችል የለምና ለመቀደስም ፈልጉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ያለ ቅድስና ማንም ጌታን ማየት ስለማይችል ከሰው ሁሉ ጋር በሰላም ኑሩ፤ በቅድስናም ለመኖር ትጉ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከሰው ሁሉ ጋር ሰላምን ተከታተሉ ትቀደሱም ዘንድ ፈልጉ፥ ያለ እርሱ ጌታን ሊያይ የሚችል የለምና። |
በዚያም ስፍራ ባረከው። ያዕቆብም፥ “እግዚአብሔርን ፊት ለፊት አየሁ፤ ሰውነቴም ዳነች” ሲል የዚያን ቦታ ስም “ራእየ እግዚአብሔር” ብሎ ጠራው።
ወደ እግዚአብሔር ይጸልያል፥ ጸሎቱም ተቀባይነትን ያገኛል። በደስተኛም ፊት እያመሰገነ ይገባል፥ ለሰውም ጽድቁን ይመልስለታል።
በእግዚአብሔር ቤት፥ በአምላካችን ቤት አደባባዮች የምትቆሙ እናንተ የእግዚአብሔር ባሪያዎች ሁላችሁ፥ እነሆ፥ እግዚአብሔርን አመስግኑ።
እናንተ ጽድቅን የምትከተሉ እግዚአብሔርንም የምትሹ፥ ስሙኝ፤ የተቈረጣችሁበትን ጽኑዕ ዓለት የተቈፈራችሁባትንም ጥልቅ ጕድጓድ ተመልከቱ።
ዛሬ ግን ከኀጢአት ነጻ ወጣችሁ፤ ራሳችሁንም ለጽድቅ አስገዛችሁ፤ ለቅድስናም ፍሬን አፈራችሁ፤ ፍጻሜው ግን የዘለዓለም ሕይወት ነው።
ወንድሞቻችን! አንድ ቃል እንድትናገሩ፥ እንዳታዝኑ፥ ፍጹማንም እንድትሆኑ፥ ሁላችሁንም፦ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እማልዳችኋለሁ፤ እንዳትለያዩም አንድ ልብና አንድ አሳብ ሆናችሁ ኑሩ።
አሁን ግን ታወቀኝ፤ በግልጥም ተረዳኝ፤ በመስታወትም እንደሚያይ ሰው ዛሬ በድንግዝግዝታ እናያለን፤ ያን ጊዜ ግን ፊት ለፊት እናያለን፤ አሁን በከፊል፥ ኋላ ግን እንደ ተገለጠልኝ መጠን ሁሉን አውቃለሁ።
ስለዚህም “ከመካከላቸው ተለይታችሁ ውጡ፤ ከእነርሱም ተለዩ፤ ወደ ርኩሳንም አትቅረቡ፥ እኔም እቀበላችኋለሁ።
ወንድሞቻችን ሆይ፥ እንግዲህ ይህ ተስፋ ያለን ስለሆን ራሳችንን እናንጻ፤ ሥጋችንን አናርክስ፤ ነፍሳችንንም አናሳድፍ፤ እግዚአብሔርንም በመፍራት የምንቀደስበትን እንሥራ።
እንግዲህ ኦሪት እግዚአብሔር የሰጠውን ተስፋ ልትከለክል መጣችን? አይደለም፤ ማዳን የሚቻለው ሕግ ተሠርቶ ቢሆንማ፥ በእውነት በዚያ ሕግ ጽድቅ በተገኘ ነበር።
ሴሰኛ፥ ወይም ኀጢአተኛ፥ ወይም ቀማኛ፥ ወይም ጣዖትን የሚያመልክ ሁሉ በእግዚአብሔር ልጅ በክርስቶስ መንግሥት ዕድል ፋንታ እንደሌለው ይህን ዕወቁ።
ነገር ግን ይህን ፈጽሜ የተቀበልሁ አይደለም፤ ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ እርሱ እኔን የመረጠበትን አገኝ ዘንድ እሮጣለሁ እንጂ።
እነርሱ መልካም ሆኖ እንደ ታያቸው ለጥቂት ቀን ይቀጡናል፤ እርሱ ግን ከቅድስናው እንድንካፈል ለጥቅማችን ይቀጣናል።
እንዲሁ ክርስቶስም የብዙዎችን ኀጢአት ያስተሰርይ ዘንድ ራሱን አንድ ጊዜ ሠዋ፤ በኋላ ግን ያድናቸው ዘንድ ተስፋ ለሚያደርጉት ያለ ኀጢአት ይገለጥላቸዋል።
ይህ ሁሉ እንዲህ የሚቀልጥ ከሆነ፥ የእግዚአብሔርን ቀን መምጣት እየጠበቃችሁና እያስቸኰላችሁ በቅዱስ ኑሮ እግዚአብሔርንም በመምሰል እንደ ምን ልትሆኑ ይገባችኋል? ስለዚያ ቀን ሰማያት ተቃጥለው ይቀልጣሉ፤ የሰማይም ፍጥረት በትልቅ ትኵሳት ይፈታል፤
ነገር ግን በጌታችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና እውቀት እደጉ። ለእርሱ አሁንም እስከ ዘላለምም ቀን ድረስ ክብር ይሁን፤ አሜን።
ዮፍታሔም የላካቸው ወደ ዮፍታሔ ተመለሱ፤ ዮፍታሔም ወደ አሞን ልጆች ንጉሥ መልእክተኞችን እንደ ገና ላከ፤ እንዲህም አለው፦