Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




1 ተሰሎንቄ 5:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 ማንም ለሌላው በክፉ ፈንታ ክፉ እንዳይመልስ ተጠንቀቁ፤ ነገር ግን ሁልጊዜ እርስ በርሳችሁ ለሁሉም መልካሙን ለማድረግ ትጉ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 ማንም በክፉ ፈንታ ክፉ እንዳይመልስ ተጠንቀቁ፤ ነገር ግን እርስ በርሳችሁም ሆነ ለሌሎች ሰዎች ሁልጊዜ መልካም የሆነውን ነገር ለማድረግ ተጣጣሩ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 ማንም ለሌላው በክፉ ፈንታ ክፉ እንዳይመልስ ተጠንቀቁ፤ ነገር ግን ሁልጊዜ እርስ በርሳችሁ እንዲሁም ለሁሉም መልካሙን ለማድረግ ትጉ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 ማንም ሰው በክፉ ፋንታ ክፉ እንዳይመልስ ተጠንቀቁ፤ ይልቅስ ሁልጊዜ እናንተ ለእርስ በርሳችሁም ሆነ እንዲሁም ለሌሎች ሰዎች ሁሉ መልካም ለማድረግ ትጉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 ማንም ለሌላው በክፉ ፈንታ ክፉ እንዳይመልስ ተጠንቀቁ፥ ነገር ግን ሁልጊዜ እርስ በርሳችሁ ለሁሉም መልካሙን ለማድረግ ትጉ።

Ver Capítulo Copiar




1 ተሰሎንቄ 5:15
39 Referencias Cruzadas  

ዮሴ​ፍም ወን​ድ​ሞ​ቹን አሰ​ና​በ​ታ​ቸው፤ እን​ዲ​ህም አላ​ቸው፥ “በመ​ን​ገድ እርስ በር​ሳ​ችሁ አት​ጣሉ።”


ክፉ ላደ​ረ​ጉ​ብ​ኝም ክፉን መል​ሼ​ላ​ቸው ብሆን፥ ጠላ​ቶቼ ዕራ​ቁ​ቴን ይጣ​ሉኝ።


በመልካም ፋንታ ክፉን የሚመልስ፥ ክፉ ነገር ከቤቱ አይርቅም።


ጠላቴን እበቀለዋለሁ አትበል፤ ነገር ግን እንዲረዳህ እግዚአብሔርን ተማመን።


ጠላትህ ቢወድቅ ደስ አይበልህ፥ በመሰናከሉም አትታበይ።


እኔ ከሰው ሁሉ ይልቅ ሰነፍ ነኝና፥ የሰውም ማስተዋል በእኔ ላይ አልነበረምና።


አት​በ​ቀል፤ በሕ​ዝ​ብ​ህም ልጆች ቂም አት​ያዝ፤ ነገር ግን ባል​ን​ጀ​ራ​ህን እንደ ራስህ ውደድ፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክህ ነኝና።


እኔ ግን እላችኋለሁ፤ ክፉውን አትቃወሙ፤ ዳሩ ግን ቀኝ ጉንጭህን በጥፊ ለሚመታህ ሁሉ ሁለተኛውን ደግሞ አዙርለት፤


አሁ​ንም ጠላ​ቶ​ቻ​ች​ሁን ውደዱ፤ መል​ካ​ምም አድ​ር​ጉ​ላ​ቸው፤ እን​ዲ​መ​ል​ሱ​ላ​ችሁ ተስፋ ሳታ​ደ​ርጉ አበ​ድሩ፤ ዋጋ​ች​ሁም ብዙ ይሆ​ናል፤ የል​ዑ​ልም ልጆች ትሆ​ና​ላ​ችሁ፤ እርሱ ለበ​ጎ​ዎ​ችና ለክ​ፉ​ዎች ቸር ነውና።


ጳው​ሎ​ስም፥ “በራ​ስህ ክፉ ነገር አታ​ድ​ርግ፤ ሁላ​ች​ንም ከዚህ አለን” ብሎ በታ​ላቅ ቃል ጮኸ።


ፍቅ​ራ​ችሁ ያለ ግብ​ዝ​ነት ይሁን፤ ከክፉ ራቁ፤ በጎ​ው​ንም ያዙ፤ ለጽ​ድቅ አድሉ፤


አሁ​ንም ወን​ድ​ማ​ችን ይታ​ነጽ ዘንድ ሰላ​ምን እን​ከ​ተ​ላት።


ፍቅ​ርን ተከ​ተ​ሏት፤ ለመ​ን​ፈ​ሳዊ ስጦታ፥ ይል​ቁ​ንም ትን​ቢት ለመ​ና​ገር ተፎ​ካ​ከሩ።


ጢሞ​ቴ​ዎ​ስም በመጣ ጊዜ በእ​ና​ንተ ዘንድ ያለ ፍር​ሀት እን​ዲ​ኖር ተጠ​ን​ቀቁ፤ እንደ እኔ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሥራ ይሠ​ራ​ልና።


እን​ግ​ዲህ ፀብና ክር​ክር ካላ​ችሁ፥ ከመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ጀምሮ ውር​ደት እን​ደ​ሚ​ሆ​ን​ባ​ችሁ ዕወቁ፤ እን​ግ​ዲ​ያማ እን​ዴት አት​ነ​ጠ​ቁም? እን​ዴ​ትስ አት​ገ​ፉም?


እን​ግ​ዲህ ጊዜ ሳለን ለሁሉ መል​ካም ሥራ እና​ድ​ርግ፤ ይል​ቁ​ንም ለሃ​ይ​ማ​ኖት ሰዎች።


እን​ግ​ዲህ እንደ ዐዋ​ቂ​ዎች እንጂ እንደ አላ​ዋ​ቂ​ዎች ሳይ​ሆን እን​ዴት እን​ደ​ም​ት​መ​ላ​ለሱ በጥ​ን​ቃቄ ዕወቁ።


እን​ግ​ዲ​ያስ እና​ን​ተም ሁላ​ችሁ እን​ዲሁ ሚስ​ቶ​ቻ​ች​ሁን እንደ ራሳ​ችሁ ውደዱ፥ ሴትም ባል​ዋን ትፍ​ራው።


በሕ​ይ​ወት ትኖር ዘንድ፥ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የሚ​ሰ​ጥ​ህን ምድር ትወ​ርስ ዘንድ እው​ነ​ተ​ኛ​ውን ፍርድ ተከ​ተል።


አንተ ግን የእግዚአብሔር ሰው ሆይ! ከዚህ ሽሽ፤ ጽድቅንና እግዚአብሔርን መምሰል እምነትንም ፍቅርንም መጽናትንም የዋህነትንም ተከታተል።


የጌታም ባሪያ ለሰው ሁሉ ገር፥ ለማስተማርም የሚበቃ፥ ለትዕግሥትም የሚጸና ሊሆን እንጂ ሊጣላ አይገባውም።


ከሁሉ ጋር ወደ ሰላም ሩጡ፤ ቅድ​ስ​ና​ች​ሁ​ንም አት​ተዉ፤ ያለ እርሱ ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሚ​ያ​የው የለም።


ለእውነት እየታዘዛችሁ ግብዝነት ለሌለበት ለወንድማማች መዋደድ ነፍሳችሁን አንጽታችሁ እርስ በርሳችሁ ከልባችሁ አጥብቃችሁ ተዋደዱ።


ሁሉን አክብሩ፤ ወንድሞችን ውደዱ፤ እግዚአብሔርን ፍሩ፤ ንጉሥን አክብሩ።


ክፉን በክፉ ፈንታ ወይም ስድብን በስድብ ፈንታ አትመልሱ፤ በዚህ ፈንታ ባርኩ እንጂ፤ በረከትን ልትወርሱ ለዚህ ተጠርታችኋልና።


ወዳጅ ሆይ! በጎ የሆነውን እንጂ ክፉን አትምሰል። በጎ የሚያደርግ ከእግዚአብሔር ነው፤ ክፉን የሚያደርግ ግን እግዚአብሔርን አላየውም።


ልሰግድለትም በእግሩ ፊት ተደፋሁ። እርሱም “እንዳታደርገው ተጠንቀቅ፤ ከአንተ ጋር የኢየሱስም ምስክር ካላቸው ከወንድሞችህ ጋር አብሬ ባሪያ ነኝ፤ ለእግዚአብሔር ስገድ፤ የኢየሱስ ምስክር የትንቢት መንፈስ ነውና፤” አለኝ።


እርሱም “እንዳታደርገው ተጠንቀቅ፤ ከአንተ ጋር ከወንድሞችህም ነቢያት ጋር የዚህንም መጽሐፍ ቃል ከሚጠብቁ ጋር አብሬ ባሪያ ነኝ፤ ለእግዚአብሔር ስገድ፤” አለኝ።


እግ​ዚ​እ​ብ​ሔር በእ​ኔና በአ​ንተ መካ​ከል ይፍ​ረድ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አን​ተን ይበ​ቀ​ል​ልኝ፤ እጄ ግን በአ​ንተ ላይ አት​ሆ​ንም።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos