ዘፍጥረት 29:31 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም ልያ የተጠላች መሆንዋን በአየ ጊዜ ማኅፀንዋን ከፈተላት፤ ራሔል ግን መካን ነበረች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ልያ እንዳልተወደደች ባየ ጊዜ ማሕፀኗን ከፈተላት፤ ራሔል ግን መካን ነበረች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እግዚአብሔርም ልያ የተጠላች መሆንዋን ባየ ጊዜ ማኅፀንዋን ከፈተላት፥ ራሔል ግን መካን ነበረች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ልያ የራሔልን ያኽል እንዳልተወደደች እግዚአብሔር ባየ ጊዜ ልጅ መውለድ እንድትችል ማሕፀንዋን ከፈተላት፤ ራሔል ግን መኻን ሆነች፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም ልያ የተጠላች መሆንዋን ባየ ጊዜ ማኅፀንዋን ከፈተላት፤ ራሔል ግን መካን ነበረች። |
ይስሐቅም ስለ ሚስቱ ርብቃ ወደ እግዚአብሔር ለመነ፤ መካን ነበረችና፤ እግዚአብሔርም ሰማው፤ ሚስቱ ርብቃም ፀነሰች።
ዔሳውም አባቱ ስለ ባረከው በያዕቆብ ቂም ያዘበት፤ ዔሳውም በልቡ አለ፥ “ለአባቴ የልቅሶ ቀን ትቅረብ፤ ወንድሜን ያዕቆብን እገድለዋለሁ።”
ልያም ፀነሰች፤ ወንድ ልጅንም ወለደች፥ ስሙንም ሮቤል ብላ ጠራችው፥ “እግዚአብሔር መዋረዴን አይቶአልና፥ እንግዲህስ ወዲህ ባሌ ይወድደኛል” ስትል።
ሚስትህ በቤትህ እልፍኝ ውስጥ እንደሚያፈራ ወይን ትሆናለች፤ ልጆችህም በማዕድህ ዙሪያ እንደ አዲስ የወይራ ተክል ይሆናሉ።
እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፥ “በግብፅ ያለውን የሕዝቤን መከራ በእውነት አየሁ፦ ከአሠሪዎቻቸውም የተነሣ ጩኸታቸውን ሰማሁ፤ ሥቃያቸውንም ዐውቄአለሁ፤
ከእኔ ይልቅ አባቱን ወይም እናቱን የሚወድ ለእኔ ሊሆን አይገባውም፤ ከእኔ ይልቅም ወንድ ልጁን ወይም ሴት ልጁን የሚወድ ለእኔ ሊሆን አይገባውም።
“ለሁለት ጌቶች መገዛት የሚቻለው ማንም የለም፤ ወይም አንዱን ይጠላል ሁለተኛውንም ይወዳል፤ ወይም ወደ አንዱ ይጠጋል ሁለተኛውንም ይንቃል፤ ለእግዚአብሔርና ለገንዘብ መገዛት አትችሉም።
“ወደ እኔ የሚመጣ፥ ሊከተለኝም የሚወድ አባቱንና እናቱን፥ ሚስቱንና ልጆቹን፥ ወንድሞቹንና እኅቶቹን፥ የራሱንም ሰውነት እንኳ ቢሆን የማይጠላ ደቀ መዝሙሬ ሊሆን አይችልም።
የግዝረትንም ኪዳን ሰጠው፤ ከዚህም በኋላ ይስሐቅን ወለደ፤ በስምንተኛው ቀንም ገረዘው፤ እንዲሁ ይስሐቅም ያዕቆብን፥ ያዕቆብም ዐሥራ ሁለቱን የቀደሙ አባቶችን ገረዙ።
“ለአንድ ሰው አንዲቱ የተወደደች፥ አንዲቱም የተጠላች ሁለት ሚስቶች ቢኖሩት፥ ለእርሱም የተወደደችው፥ ደግሞም የተጠላችው ልጆችን ቢወልዱ፥ በኵሩም ከተጠላችው ሚስት የተወለደው ልጅ ቢሆን፥
የመውለጃዋም ወራት በደረሰ ጊዜ ሐና ወንድ ልጅ ወለደች፤ እርስዋም፥ “ከሠራዊት ጌታ ከእግዚአብሔር ለምኜዋለሁ” ስትል ስሙን “ሳሙኤል” ብላ ጠራችው።
ለሐናም ልጅ ስላልነበራት አንድ ዕድል ፋንታ ሰጣት፤ ሕልቃናም ከዚያችኛይቱ ይልቅ ሐናን ይወድድ ነበር። እግዚአብሔር ግን ማኅፀንዋን ዘግቶ ነበር።
እግዚአብሔርም ሐናን ጐበኘ፤ ዳግመኛም ፀነሰች፥ ሦስት ወንዶችና ሁለት ሴቶች ልጆችን ወለደች። ብላቴናው ሳሙኤልም በእግዚአብሔር ፊት አደገ።