Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ሐዋርያት ሥራ 7:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 የግ​ዝ​ረ​ት​ንም ኪዳን ሰጠው፤ ከዚ​ህም በኋላ ይስ​ሐ​ቅን ወለደ፤ በስ​ም​ን​ተ​ኛው ቀንም ገረ​ዘው፤ እን​ዲሁ ይስ​ሐ​ቅም ያዕ​ቆ​ብን፥ ያዕ​ቆ​ብም ዐሥራ ሁለ​ቱን የቀ​ደሙ አባ​ቶ​ችን ገረዙ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 ከዚያም የግዝረትን ኪዳን ሰጠው፤ አብርሃምም ይሥሐቅን ወለደ፤ በስምንተኛውም ቀን ገረዘው። ይሥሐቅም ያዕቆብን ወለደ፤ ያዕቆብም ዐሥራ ሁለቱን የነገድ አባቶች ወለደ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 የመገረዝንም ኪዳን ሰጠው፤ እንዲሁም ይስሐቅን ወለደ፤ በስምንተኛውም ቀን ገረዘው፤ ይስሐቅም ያዕቆብን ያዕቆብም ዐሥራ ሁለቱን የአባቶችን አለቆች።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 የመገረዝንም ኪዳን ሰጠው፤ ስለዚህ አብርሃም ይስሐቅን በወለደ ጊዜ በስምንተኛው ቀን ገረዘው፤ እንዲሁም ይስሐቅ ልጁን ያዕቆብን ገረዘው። ያዕቆብም የነገድ አባቶች የሆኑትን ዐሥራ ሁለቱን ልጆቹን ገረዘ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 የመገረዝንም ኪዳን ሰጠው፤ እንዲሁም ይስሐቅን ወለደ በስምንተኛውም ቀን ገረዘው ይስሐቅም ያዕቆብን ያዕቆብም አሥራ ሁለቱን የአባቶችን አለቆች።

Ver Capítulo Copiar




ሐዋርያት ሥራ 7:8
20 Referencias Cruzadas  

“እና​ንተ ወን​ድ​ሞች ሆይ፥ ስለ አባ​ቶች አለቃ ስለ ዳዊት ነገር እንደ ሞተ እንደ ተቀ​በ​ረም፥ መቃ​ብ​ሩም እስከ ዛሬ ድረስ በእኛ ዘንድ እንደ አለ ገልጬ እን​ድ​ነ​ግ​ራ​ችሁ ትፈ​ቅ​ዱ​ል​ኛ​ላ​ች​ሁን?


ያዕ​ቆ​ብም ከቤ​ቴል ተጓዘ፤ በጋ​ዲር ግንብ አጠ​ገብ ድን​ኳን ተከለ፤ ወደ ኤፍ​ራ​ታም ለመ​ድ​ረስ በቀ​ረበ ጊዜ ራሔ​ልን ምጥ ያዛት፤ በም​ጡም ተጨ​ነ​ቀች።


የአ​ባ​ቶች አለቃ አብ​ር​ሃም ከም​ር​ኮው ሁሉ የሚ​ሻ​ለ​ውን ዐሥ​ራት የሰ​ጠ​ውን የዚ​ህን ካህን ክብር ታያ​ላ​ች​ሁን?


እን​ግ​ዲህ እን​ዲህ እላ​ለሁ፦ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ሰጠ ይህ ኪዳን ጽኑዕ ነው፤ ከዚ​ህም በኋላ በአ​ራት መቶ ሠላሳ ዓመት ኦሪት መጣች፤ ነገር ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሰ​ጠ​ውን ተስፋ ልት​ከ​ለ​ክል አይ​ደ​ለም።


ወን​ድ​ሞች ሆይ፥ እንደ ሰው ልማድ እን​ና​ገ​ራ​ለን፤ ሰውም እን​ኳን የጸ​ና​ውን ኪዳን አይ​ን​ቅም አይ​ጨ​ም​ር​በ​ት​ምም።


ለአ​ብ​ር​ሃም ጽድቅ ሆኖ የተ​ቈ​ጠ​ረ​ለት መቼ ነው? ተገ​ዝሮ ሳለ ነውን? ወይስ ሳይ​ገ​ዘር? ሳይ​ገ​ዘር ነው እንጂ ተገ​ዝሮ ሳለ አይ​ደ​ለም።


ስለ​ዚህ ሙሴ ግዝ​ረ​ትን ሰጥ​ቶ​አ​ችሁ ነበር፤ ነገር ግን ከአ​ባ​ቶች ናት እንጂ ከሙሴ አይ​ደ​ለ​ችም፤ በሰ​ን​በ​ትም ሰውን ትገ​ዝ​ሩ​ታ​ላ​ችሁ።


አብርሃም ይስሐቅን ወለደ፤ ይስሐቅም ያዕቆብን ወለደ፤ ያዕቆብም ይሁዳንና ወንድሞቹን ወለደ፤


አብ​ር​ሃ​ምም ይስ​ሐ​ቅን ወለደ። የይ​ስ​ሐ​ቅም ልጆች ዔሳ​ውና ያዕ​ቆብ ነበሩ።


ከዚ​ያም በኋላ ነፍ​ስዋ ልት​ወጣ ደረ​ሰች፤ ሞትዋ በእ​ርሱ ሆኖ​አ​ልና ስሙን የጭ​ን​ቀቴ ልጅ ብላ ጠራ​ችው ፤ አባቱ ግን ብን​ያም አለው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ልያ የተ​ጠ​ላች መሆ​ን​ዋን በአየ ጊዜ ማኅ​ፀ​ን​ዋን ከፈ​ተ​ላት፤ ራሔል ግን መካን ነበ​ረች።


የራ​ሔል አገ​ል​ጋይ ባላም ፀነ​ስች፤ ወንድ ልጅ​ንም ለያ​ዕ​ቆብ ወለ​ደ​ች​ለት።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios