ኤዶምያስን በእውነት መታህ፤ ልብህንም ከፍ ከፍ አደረግህ፤ በዚያ ተመካ፤ በቤትህም ተቀመጥ፤ አንተ፥ ይሁዳም ከአንተ ጋር ትወድቁ ዘንድ ስለ ምን መከራን ትሻለህ?” ብሎ ወደ ይሁዳ ንጉሥ ወደ አሜስያስ ላከ።
ዘዳግም 8:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከግብፅ ምድር ከባርነት ቤት ያወጣህን፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ልብህ ይታበይና ከባርነት ምድር፣ ከግብጽ ያወጣህን አምላክህን እግዚአብሔርን ትረሳለህ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ልብህ እንዳይታበይና፥ ከግብጽም ምድር ከባርነት ቤት ያወጣህን፥ ጌታን አምላክህን እንዳትረሳ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ልብህ እንዳይታበይና በባርነት ከኖርክባት ከግብጽ ምድር ያወጣህን አምላክህን እግዚአብሔርን እንዳትረሳ ተጠንቀቅ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከግብፅም ምድር ከባርነት ቤት ያወጣህን፥ |
ኤዶምያስን በእውነት መታህ፤ ልብህንም ከፍ ከፍ አደረግህ፤ በዚያ ተመካ፤ በቤትህም ተቀመጥ፤ አንተ፥ ይሁዳም ከአንተ ጋር ትወድቁ ዘንድ ስለ ምን መከራን ትሻለህ?” ብሎ ወደ ይሁዳ ንጉሥ ወደ አሜስያስ ላከ።
ነገር ግን በበረታ ጊዜ ለጥፋት ልቡ ታበየ፤ አምላኩንም እግዚአብሔርን በደለ፤ በዕጣን መሠዊያውም ላይ ያጥን ዘንድ ወደ መቅደስ ገባ።
ሕዝቅያስ ግን እግዚአብሔር እንደ ሰጠው ቸርነት መጠን አላደረገም፤ ልቡም ኮራ፤ ስለዚህም በእርሱና በይሁዳ፥ በኢየሩሳሌምም ላይ ቍጣ ሆነ።
ሙሴም ሕዝቡን አለ፥ “ከባርነት ቤት ከግብፅ የወጣችሁባትን ይህችን ቀን ዐስቡ፤ እግዚአብሔር ከዚህ ቦታ በበረታች እጅ አውጥቶአችኋልና። ስለዚህ የቦካ እንጀራ አትብሉ።
የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ። በውኑ ለእስራኤል ምድረ በዳ ወይስ የጨለመች ምድር ሆንሁበትን? ሕዝቤስ ስለ ምን፦ እኛ አንገዛልህም፤ ከእንግዲህም ወዲህ ወደ አንተ አንመለስም ይላል?
እነርሱም፥ “ከግብፅ ምድር ያወጣን፥ በምድረ በዳና በባድማ፥ ዕንጨትና ውኃ፥ የእንጨት ፍሬም በሌለበት ምድር፥ ሰው በማያልፍበትና የሰው ልጅም በማይቀመጥበት ምድር የመራን እግዚአብሔር ወዴት አለ? አላሉም።
አባቶቻቸው ስለ በዓል ስሜን እንደ ረሱ፥ እያንዳንዱ ለባልንጀራው በሚናገራት ሕልማቸው ሕዝቤን ስሜን ለማስረሳት ያስባሉ።
እርሱም በዘርፉ ይሁንላችሁ፤ ትመለከቱታላችሁም፤ የእግዚአብሔርንም ትእዛዛት ታስባላችሁ፤ ታደርጉአቸውማላችሁ፤ እነርሱን በመከተል ያመነዘራችሁባትን የሕሊናችሁንና የዐይኖቻችሁን ፈቃድ አትከተሉ።
“የአባትህ ወይም የእናትህ ልጅ ወንድምህ ወይም ወንድ ልጅህ ወይም ሴት ልጅህ ወይም አብራህ የምትተኛ ሚስትህ ወይም እንደ ነፍስህ ያለ ወዳጅህ በስውር፦ ና፥ ሄደን አንተም አባቶችህም የማታውቋቸውን ሌሎች አማልክት እናምልክ ብሎ ቢያስትህ፥
ልቡ በወንድሞቹ ላይ እንዳይኰራ፥ የአምላኩ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ እንዳይተው፥ ቀኝና ግራም እንዳይል፥ እርሱም ልጆቹም በእስራኤል ልጆች መካከል ረዥም ዘመን ይገዙ ዘንድ።
“ለራስህ ዕወቅ፤ ሰውነትህን ፈጽመህ ጠብቅ፤ ዐይኖችህ ያዩትን ይህን ሁሉ ነገር አትርሳ፤ በሕይወትህ ዘመን ሁሉ ከልቡናህ አይውጣ፤ ለልጆችህና ለልጅ ልጆችህም አስተምራቸው።
ያልሞላሃቸውንም ሀብትን የሞሉ ቤቶች፥ ያልማስሃቸውንም የተማሱ ጕድጓዶች፥ ያልተከልሃቸውንም ወይንና ወይራ በሰጠህ ጊዜ፥ በበላህና በጠገብህም ጊዜ፤
“ዛሬ እኔ አንተን የማዝዘውን ትእዛዙንና ፍርዱን፥ ሥርዐቱንም ባለመጠበቅ አምላክህን እግዚአብሔርን እንዳትረሳ ተጠንቀቅ፤
የእስራኤልም ልጆች በእግዚአብሔር ፊት ክፉ አደረጉ፤ አምላካቸውንም እግዚአብሔርን ረስተው በዓሊምንና አስታሮትን አመለኩ።