Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘዳግም 13:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 “የአ​ባ​ትህ ወይም የእ​ና​ትህ ልጅ ወን​ድ​ምህ ወይም ወንድ ልጅህ ወይም ሴት ልጅህ ወይም አብ​ራህ የም​ት​ተኛ ሚስ​ትህ ወይም እንደ ነፍ​ስህ ያለ ወዳ​ጅህ በስ​ውር፦ ና፥ ሄደን አን​ተም አባ​ቶ​ች​ህም የማ​ታ​ው​ቋ​ቸ​ውን ሌሎች አማ​ል​ክት እና​ም​ልክ ብሎ ቢያ​ስ​ትህ፥

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 የእናትህ ልጅ ወንድምህ፣ ወንድ ወይም ሴት ልጅህ፣ ወይም የምትወድዳት ሚስትህ ወይም የልብ ጓደኛህ፣ (አንተም ሆንህ አባቶችህ የማታውቋቸውን አማልክት) “ሄደን ሌሎችን አማልክት እናምልክ” ብሎ በስውር ሊያስትህ ቢሞክር፣

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 “የአባትህ፥ ወይም የእናትህ ልጅ ወንድምህ፥ ወንድ ልጅህ፥ ወይም ሴት ልጅህ ወይም የምትወዳት ሚስትህ ወይም የቅርብ ወዳጅህ አንዳቸው ቢሆኑ በምሥጢር ሊያስትህ ቢሞክር፥

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6-7 “በቅርብም ሆነ በሩቅ ካሉት፥ ከአንዱ የምድር ዳርቻ በአካባቢህ ካሉ ከአሕዛብ አማልክት አንተ ወይም አባቶችህ የማታውቁትን አንዱን እናምልክ በማለት ሌላ እንኳ ቀርቶ የአባትህ፥ ወይም የእናትህ ልጅ ወንድምህ፥ ወንድ ልጅህ፥ ወይም ሴት ልጅህ ወይም የምትወዳት ሚስትህ ወይም የቅርብ ወዳጅህ በምሥጢር ይገፋፋህ ይሆናል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6-7 የእናትህ ልጅ ወንድምህ ወይም ወንድ ልጅህ ወይም ሴት ልጅህ ወይም በብብትህ ያለች ሚስትህ ወይም እንደ ነፍስህ ያለ ወዳጅህ በስውር፦ ና፥ ሄደን ከምድር ዳር ጀምሮ እስከ ምድር ዳር ድረስ ወደ አንተ የቀረቡት ከአንተም የራቁት አንተን ከብበውህ ያሉ አሕዛብ ከሚያመልኩአቸው አማልክት፥ አንተም አባቶችህም የማታውቍቸውን ሌሎች አማልክት እናምልክ ብሎ ቢያስትህ፥ እሺ አትበለው፥

Ver Capítulo Copiar




ዘዳግም 13:6
50 Referencias Cruzadas  

ነገር ግን ሐሰተኞች ነቢያት ደግሞ በሕዝቡ መካከል ነበሩ፤ እንዲሁም በመካከላችሁ ደግሞ ሐሰተኞች አስተማሪዎች ይሆናሉ፤ እነርሱም የዋጃቸውን ጌታ እንኳ ክደው የሚፈጥንን ጥፋት በራሳቸው ላይ እየሳቡ የሚያጠፋ ኑፋቄን አሹልከው ያገባሉ፤


እን​ግ​ዲህ በሽ​ን​ገ​ላ​ቸው ያስቱ ዘንድ በሚ​ተ​ና​ኰሉ ሰዎች ተን​ኰል ምክ​ን​ያት በት​ም​ህ​ርት ነፋስ ሁሉ ወዲ​ያና ወዲህ እየ​ተ​ፍ​ገ​መ​ገ​ም​ንና እየ​ተ​ን​ሳ​ፈ​ፍን ሕፃ​ናት አን​ሁን።


ሺህ ዓመትም አሰረው፤ ወደ ጥልቅም ጣለው፤ አሕዛብንም ወደ ፊት እንዳያስት ሺህ ዓመት እስኪፈጸም ድረስ በእርሱ ላይ ዘግቶ ማኅተም አደረገበት፤ ከዚያም በኋላ ለጥቂት ጊዜ ይፈታ ዘንድ ይገባዋል።


ዓለሙንም ሁሉ የሚያስተው፥ ዲያብሎስና ሰይጣን የሚባለው ታላቁ ዘንዶ እርሱም የቀደመው እባብ ተጣለ፤ ወደ ምድር ተጣለ፤ መላእክቱም ከእርሱ ጋር ተጣሉ።


ዮና​ታ​ንም ዳዊ​ትን እንደ ነፍሱ ይወ​ድድ ነበ​ርና እንደ ገና ማለ​ለት።


ዮና​ታ​ንም እንደ ነፍሱ ስለ ወደ​ደው ዮና​ታ​ንና ዳዊት ቃል ኪዳን አደ​ረጉ።


እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ዳዊት ለሳ​ኦል መን​ገ​ሩን በፈ​ጸመ ጊዜ የዮ​ና​ታን ነፍስ በዳ​ዊት ነፍስ ታሰ​ረች፤ ዮና​ታ​ንም እንደ ነፍሱ ወደ​ደው።


ሄዶ የእ​ነ​ዚ​ያን አሕ​ዛብ አማ​ል​ክት ያመ​ልክ ዘንድ ከአ​ም​ላ​ካ​ችሁ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልቡን ዛሬ የሚ​ያ​ስት ወንድ ወይም ሴት ወይም ወገን ወይም ነገድ አይ​ኑ​ር​ባ​ችሁ፤ ሐሞ​ትና እሬ​ትም የሚ​ያ​በ​ቅል ሥር አይ​ሁ​ን​ባ​ችሁ።


በአ​ንተ ዘንድ የተ​ደ​ላ​ደ​ለና የተ​ቀ​ማ​ጠለ ሰው በወ​ን​ድሙ፥ አብ​ራ​ውም በም​ት​ተኛ በሚ​ስቱ፥ በቀ​ሩ​ትም ልጆቹ ይቀ​ናል፤


በአውሬውም ፊት ያደርግ ዘንድ ከተሰጡት ምልክቶች የተነሣ በምድር የሚኖሩትን ያስታል፤ የሰይፍም ቍስል ለነበረውና በሕይወት ለኖረው ለአውሬው ምስልን እንዲያደርጉ በምድር የሚኖሩትን ይናገራል።


ይህ​ንም የም​ላ​ችሁ በሚ​ያ​ባ​ብል ነገር የሚ​ያ​ስ​ታ​ችሁ እን​ዳ​ይ​ኖር ነው።


ይኸ​ውም ባሪ​ያ​ዎች ያደ​ር​ጉን ዘንድ በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ያገ​ኘ​ና​ትን ነጻ​ነት ሊሰ​ልሉ በስ​ውር ወደ እኛ የገቡ ሐሰ​ተ​ኞች መም​ህ​ራ​ንን ደስ አይ​በ​ላ​ቸው ብዬ ነው።


ስለ​ዚህ ከአ​ሁን ጀምሮ በሥጋ የም​ና​ው​ቀው የለም፤ ክር​ስ​ቶ​ስ​ንም በሥጋ ብና​ው​ቀው አሁን ግን ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ የም​ና​ው​ቀው አይ​ደ​ለም።


ልቤ በስ​ውር ተታ​ልሎ እንደ ሆነ፥ በአ​ፌም ላይ እጄን አኑሬ ስሜ እንደ ሆነ፥


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት እንደ ገና ክፉ ሥራ ሠሩ፤ በዓ​ሊ​ም​ንና አስ​ታ​ሮ​ትን፥ የሶ​ር​ያ​ንም አማ​ል​ክት፥ የሲ​ዶ​ና​ንም አማ​ል​ክት፥ የሞ​ዓ​ብ​ንም አማ​ል​ክት፥ የአ​ሞ​ን​ንም ልጆች አማ​ል​ክት፥ የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ን​ንም አማ​ል​ክት አመ​ለኩ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ተዉ፤ አላ​መ​ለ​ኩ​ት​ምም።


አዲ​ሶች አማ​ል​ክ​ትን መረጡ፤ በዚያ ጊዜ ሰልፍ በበ​ሮች ሆነ፤ በአ​ርባ ሺህ በእ​ስ​ራ​ኤል ዘንድ ጦርና ጋሻ አል​ታ​ዩም።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ትተው በዓ​ል​ንና አስ​ታ​ሮ​ትን አመ​ለኩ።


ሦራም አብ​ራ​ምን፥ “ከአ​ንተ የተ​ነሣ እገ​ፋ​ለሁ፤ እኔ አገ​ል​ጋ​ዬን በብ​ብ​ትህ ሰጠ​ሁህ፤ እንደ ፀነ​ሰ​ችም ባየች ጊዜ እኔን ማክ​በ​ርን ተወች፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ኔና በአ​ንተ መካ​ከል ይፍ​ረድ” አለ​ችው።


ልጄ ሆይ፥ ከሌላዪቱ ሴት ጋር አትኑር፤ የአንተ ወዳልሆነችውም እጅህን አትዘርጋ።


ወን​ድሜ ዮና​ታን ሆይ፥ እኔ ስለ አንተ እጨ​ነ​ቃ​ለሁ፤ አንተ በእኔ ዘንድ እጅግ የተ​ወ​ደ​ድህ ነበ​ርህ፤ ከሴት ፍቅር ይልቅ ፍቅ​ርህ ለእኔ ድንቅ ነበረ።


እር​ሱም፦ ሄደን የማ​ታ​ው​ቃ​ቸ​ውን ሌሎች አማ​ል​ክት እን​ከ​ተል እና​ም​ል​ካ​ቸ​ውም ብሎ የተ​ና​ገ​ረህ ምል​ክቱ ወይም ተአ​ም​ራቱ ቢፈ​ጸም፥


ከም​ድር ዳር ጀምሮ እስከ ምድር ዳር ድረስ ወደ አንተ የቀ​ረ​ቡት ከአ​ን​ተም የራ​ቁት አን​ተን ከብ​በ​ውህ ያሉ አሕ​ዛብ ከሚ​ያ​መ​ል​ኩ​አ​ቸው አማ​ል​ክት፥


የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የማ​ይ​ፈ​ልግ፥ ታናሽ ወይም ታላቅ፥ ወንድ ወይም ሴት ቢሆን፥ ይገ​ደል ዘንድ ማሉ።


የሀ​ገ​ሩም ሕዝብ ሁሉ ወደ በዓል ቤት ሄደው አፈ​ረ​ሱት፤ መሠ​ዊ​ያ​ዎ​ቹ​ንና ምስ​ሎ​ቹ​ንም አደ​ቀቁ፤ የበ​ዓ​ል​ንም ካህን ማታ​ንን በመ​ሠ​ዊ​ያው ፊት ገደ​ሉት።


ይህም የሆ​ነው ያስ​ቈ​ጡኝ ዘንድ ስላ​ደ​ረ​ጉት ክፋት፥ እነ​ር​ሱና አባ​ቶ​ቻ​ቸው ለማ​ያ​ው​ቁ​አ​ቸው ለሌ​ሎች አማ​ል​ክት ያጥኑ ዘንድ፥ ያመ​ል​ኳ​ቸ​ውም ዘንድ ስለ​ሄዱ ነው።


ማንም ደግሞ ትንቢት ቢናገር የወለዱት አባቱና እናቱ፦ አንተ በእግዚአብሔር ስም ሐሰትን ተናግረሃልና በሕይወት አትኖርም ይሉታል፣ ትንቢትንም ሲናገር የወለዱት አባቱና እናቱ ይወጉታል።


ሙሴም ሕዝ​ቡን አለ፥ “ከባ​ር​ነት ቤት ከግ​ብፅ የወ​ጣ​ች​ሁ​ባ​ትን ይህ​ችን ቀን ዐስቡ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከዚህ ቦታ በበ​ረ​ታች እጅ አው​ጥ​ቶ​አ​ች​ኋ​ልና። ስለ​ዚህ የቦካ እን​ጀራ አት​ብሉ።


እር​ሱም፦ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “እያ​ን​ዳ​ንዱ ሰይ​ፉን በወ​ገቡ ላይ ይታ​ጠቅ፤ ሂዱና በሰ​ፈሩ ውስጥ ከበር እስከ በር ተመ​ላ​ለሱ፤ እያ​ን​ዳ​ን​ዱም ወን​ድ​ሙን፥ እያ​ን​ዳ​ን​ዱም ጎረ​ቤ​ቱን፥ እያ​ን​ዳ​ን​ዱም የቅ​ር​ቡን ይግ​ደል” አላ​ቸው።


ከግ​ብፅ ምድር ከባ​ር​ነት ቤት ያወ​ጣ​ህን፥


እኔም ዛሬ በፊ​ታ​ችሁ የማ​ኖ​ራ​ትን ሥር​ዐ​ትና ፍርድ ሁሉ ታደ​ርጉ ዘንድ ጠብቁ።


ማና​ቸ​ውም ሰው ቢኰራ፥ በአ​ም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም ለማ​ገ​ል​ገል የሚ​ቆ​መ​ውን ካህ​ኑን ወይም በዚያ ወራት ያለ​ውን ፈራ​ጁን ባይ​ሰማ ያ ሰው ይሙት፤ ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ዘንድ ክፉ​ውን አስ​ወ​ግዱ፤


ነገር ግን ይና​ገር ዘንድ ያላ​ዘ​ዝ​ሁ​ትን ቃል በስሜ የሚ​ና​ገር ነቢይ፥ በሌላ አማ​ል​ክት ስም የሚ​ና​ገር ነቢ​ይም፥ እርሱ ይገ​ደል።


በወ​ን​ድሙ ላይ ክፋ​ትን ያደ​ርግ ዘንድ እንደ ወደደ በእ​ርሱ ላይ ታደ​ር​ጉ​በ​ታ​ላ​ችሁ፤ እን​ዲ​ሁም ከእ​ና​ንተ መካ​ከል ክፉ​ውን ታስ​ወ​ግ​ዳ​ላ​ችሁ።


የከ​ተ​ማ​ዉም ሰዎች ሁሉ በድ​ን​ጋይ ደብ​ድ​በው ይግ​ደ​ሉት፤ እን​ዲ​ህም ክፉ​ውን ነገር ከመ​ካ​ከ​ልህ ታር​ቃ​ለህ፤ እስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ ሰም​ተው ይፈ​ራሉ።


ብላ​ቴ​ና​ዪ​ቱን ወደ አባቷ ቤት ደጅ ያው​ጡ​አት፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ዘንድ ስን​ፍ​ናን አድ​ር​ጋ​ለ​ችና፥ የአ​ባ​ቷ​ንም ቤት አስ​ነ​ው​ራ​ለ​ችና የከ​ተ​ማው ሰዎች በድ​ን​ጋይ ወግ​ረው ይግ​ደ​ሉ​አት፤ እን​ዲ​ሁም ክፉ​ውን ነገር ከመ​ካ​ከ​ልህ ታስ​ወ​ግ​ዳ​ለህ።


“ማንም ሰው ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ከወ​ን​ድ​ሞቹ ሰውን አፍኖ ሲሰ​ር​ቅና ሲሸጥ ቢገኝ ያን የሰ​ረ​ቀ​ውን ሰው ይግ​ደ​ሉት፤ እን​ዲ​ሁም ክፉ​ውን ነገር ከመ​ካ​ከ​ላ​ችሁ አርቁ።


ተነ​ሣና ሕዝ​ቡን ቀድስ እን​ዲ​ህም በላ​ቸው፦ ‘እስ​ራ​ኤል ሆይ! እርም የሆነ ነገር በመ​ካ​ከ​ልህ አለ፤ እር​ምም የሆ​ነ​ውን ነገር ከመ​ካ​ከ​ላ​ችሁ እስ​ክ​ታ​ጠፉ ድረስ በጠ​ላ​ቶ​ቻ​ችሁ ፊት መቆም አት​ች​ሉም’ ብሎ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተና​ግ​ሮ​አ​ልና እስከ ነገ ራሳ​ች​ሁን አንጹ።


“አሁ​ንም በገ​ባ​ዖን ውስጥ የበ​ደሉ የዐ​መፅ ሰዎ​ችን እን​ድ​ን​ገ​ድ​ላ​ቸው አው​ጥ​ታ​ችሁ ስጡን፤ ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ክፋ​ትን እና​ር​ቃ​ለን።” የብ​ን​ያም ልጆች ግን የወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ቸ​ውን የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ቃል ሊሰሙ አል​ወ​ደ​ዱም።


ኤል​ያ​ስም ሕዝ​ቡን፥ “የበ​ዓ​ልን ነቢ​ያት ያዙ፤ ከእ​ነ​ርሱ አንድ ሰው እን​ኳን የሚ​ያ​መ​ልጥ አይ​ኑር፤” አላ​ቸው። ያዙ​አ​ቸ​ውም፤ ኤል​ያ​ስም ወደ ቂሶን ወንዝ ወስዶ፥ በዚያ እየ​ወጋ ጣላ​ቸው።


የሀ​ገ​ሩም ሕዝብ ሁሉ ወደ በዓል ቤት ሄደው ሰበ​ሩት፤ መሠ​ዊ​ያ​ዎ​ቹ​ንም አፈ​ረሱ፤ ምስ​ሎ​ቹ​ንም አደ​ቀቁ፥ የበ​ዓ​ል​ንም ካህን ማታ​ንን በመ​ሠ​ዊ​ያው ፊት ገደ​ሉት። ካህኑ ዮዳ​ሄም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ጠባ​ቂ​ዎ​ችን ሾመ።


ነቢ​ዩም ኤር​ም​ያስ ሐሰ​ተ​ኛ​ውን ሐና​ን​ያን፥ “ሐና​ንያ ሆይ ስማ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አል​ላ​ከ​ህም፤ ነገር ግን ይህ ሕዝብ በሐ​ሰት እን​ዲ​ታ​መን አድ​ር​ገ​ሃል።


ስለ​ዚህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እነሆ ከገጸ ምድር አስ​ወ​ግ​ድ​ሃ​ለሁ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላይ ዐመ​ፅን ተና​ግ​ረ​ሃ​ልና በዚህ ዓመት ትሞ​ታ​ለህ” አለው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios