Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




መዝሙር 78:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 ያዕ​ቆ​ብን በል​ተ​ው​ታ​ልና፥ ስፍ​ራ​ው​ንም ባድማ አድ​ር​ገ​ዋ​ልና።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 እነርሱም በእግዚአብሔር ይታመናሉ፤ የእርሱንም ሥራ አይረሱም፤ ትእዛዞቹንም ይጠብቃሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 ተስፋቸውን በእግዚአብሔር እንዲያደርጉ፥ የእግዚአብሔርንም ሥራ እንዳይረሱ፥ ትእዛዙንም እንዲጠብቁ፥

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 በዚህ ዐይነት እነርሱም በእግዚአብሔር ላይ ይታመናሉ፤ ትእዛዞቹንም ዘወትር ይፈጽማሉ እንጂ ያደረገውን ሁሉ አይረሱም።

Ver Capítulo Copiar




መዝሙር 78:7
26 Referencias Cruzadas  

ብር​ሃ​ንን እንደ ልብስ ተጐ​ና​ጸ​ፍህ፤ ሰማ​ይ​ንም እንደ መጋ​ረጃ ዘረ​ጋህ፤


ለእ​ነ​ር​ሱም ኪዳ​ኑን አሰበ፥ እንደ ምሕ​ረ​ቱም ብዛት አዘ​ነ​ላ​ቸው።


የመ​ረ​ጥ​ሃ​ቸ​ውን በጎ​ነት እናይ ዘንድ፥ በሕ​ዝ​ብ​ህም ደስታ ደስ ይለን ዘንድ፥ ከር​ስ​ት​ህም ጋር እን​ከ​ብር ዘንድ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታላቅ ነው፥ ኀይ​ሉም ታላቅ ነው፥ ለጥ​በ​ቡም ቍጥር የለ​ውም።


እኔስ፥ “አቤቱ፥ ይቅር በለኝ፤ አን​ተን በድ​ያ​ለ​ሁና ለነ​ፍሴ አስ​ተ​ስ​ር​ይ​ላት” አልሁ።


ነፍሴ በቅ​ቤና በስብ እን​ደ​ሚ​ጠ​ግቡ ትጠ​ግ​ባ​ለች፥ ደስ​ተ​ኞች ከን​ፈ​ሮቼም ስም​ህን ያመ​ሰ​ግ​ናሉ።


ያን​ጊዜ በመ​ል​ካም ሽም​ግ​ልና ይበ​ዛሉ፤ ዕረ​ፍት ያላ​ቸ​ውም ሆነው ይኖ​ራሉ።


አመ​ሰ​ገነ፤ ባረከ፤ ፈተተ፤ እን​ዲ​ህም አላ​ቸው፥ “እንኩ ብሉ፤ ስለ እና​ንተ የሚ​ሰ​ጠው ሥጋዬ ይህ ነው፤ መታ​ሰ​ቢ​ያ​ዬ​ንም እን​ዲሁ አድ​ርጉ።”


“ለራ​ስህ ዕወቅ፤ ሰው​ነ​ት​ህን ፈጽ​መህ ጠብቅ፤ ዐይ​ኖ​ችህ ያዩ​ትን ይህን ሁሉ ነገር አት​ርሳ፤ በሕ​ይ​ወ​ትህ ዘመን ሁሉ ከል​ቡ​ናህ አይ​ውጣ፤ ለል​ጆ​ች​ህና ለልጅ ልጆ​ች​ህም አስ​ተ​ም​ራ​ቸው።


ለእ​ነ​ርሱ፥ ለዘ​ለ​ዓ​ለ​ምም ለል​ጆ​ቻ​ቸው መል​ካም ይሆ​ን​ላ​ቸው ዘንድ፥ እን​ዲ​ፈ​ሩኝ፥ ሁል​ጊ​ዜም ትእ​ዛ​ዜን ሁሉ እን​ዲ​ጠ​ብቁ እን​ዲህ ያለ ልብ ማን በሰ​ጣ​ቸው፥


ከግ​ብፅ ምድር ከባ​ር​ነት ቤት ያወ​ጣ​ህን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እን​ዳ​ት​ረሳ ተጠ​ን​ቀቅ።


አንተ ልጅ​ህን በለው፦ በግ​ብፅ የፈ​ር​ዖን ባሪ​ያ​ዎች ነበ​ርን፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በጽኑ እጅ፥ በተ​ዘ​ረ​ጋ​ችም ክንድ ከዚያ አወ​ጣን፤


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እን​ዳ​ዘ​ዘን በአ​ም​ላ​ካ​ችን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት እና​ደ​ር​ጋት ዘንድ ይህ​ችን ትእ​ዛዝ ሁሉ ብን​ጠ​ብቅ ለእኛ ምሕ​ረት ይሆ​ን​ል​ናል።”


“ዛሬ እኔ አን​ተን የማ​ዝ​ዘ​ውን ትእ​ዛ​ዙ​ንና ፍር​ዱን፥ ሥር​ዐ​ቱ​ንም ባለ​መ​ጠ​በቅ አም​ላ​ክ​ህን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እን​ዳ​ት​ረሳ ተጠ​ን​ቀቅ፤


አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይፈ​ት​ንህ ዘንድ፥ በል​ብ​ህም ያለ​ውን ትእ​ዛ​ዙን ትጠ​ብቅ ወይም አት​ጠ​ብቅ እንደ ሆነ ያውቅ ዘንድ፥ ሊያ​ስ​ጨ​ን​ቅህ በም​ድረ በዳ የመ​ራ​ህን መን​ገድ ሁሉ አስብ።


ትእዛዛቱን ልንጠብቅ የእግዚአብሔር ፍቅር ይህ ነውና፤ ትእዛዛቱም ከባዶች አይደሉም።


የእግዚአብሔርን ትእዛዛት የሚጠብቁት ኢየሱስንም በማመን የሚጸኑት ቅዱሳን ትዕግሥታቸው በዚህ ነው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos