Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




2 ዜና መዋዕል 26:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 ነገር ግን በበ​ረታ ጊዜ ለጥ​ፋት ልቡ ታበየ፤ አም​ላ​ኩ​ንም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን በደለ፤ በዕ​ጣን መሠ​ዊ​ያ​ውም ላይ ያጥን ዘንድ ወደ መቅ​ደስ ገባ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 ዖዝያን ከበረታ በኋላ ግን ዕብሪቱ ለውድቀት ዳረገው። በዕጣን መሠዊያው ላይ ዕጣን ለማጠን ወደ እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ በመግባቱ አምላኩን እግዚአብሔርን በደለ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 ነገር ግን በበረታ ጊዜ ለጥፋት ልቡ ታበየ፥ አምላኩንም ጌታን በደለ፤ ወደ ጌታ መቅደስ ገብቶ በዕጣን መሠዊያ ላይ ዐጠነ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 ንጉሥ ዖዝያ መንግሥቱን ባጠናከረ ጊዜ ዕብሪተኛ ሆነ፤ ይህም ዕብሪተኛነቱ ወደ ውድቀት አደረሰው፤ በዕጣን መሠዊያው ላይ ዕጣን ለማጠን ወደ ቤተ መቅደስ በድፍረት በመግባቱ እግዚአብሔርን አሳዘነ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 ነገር ግን በበረታ ጊዜ ለጥፋት ልቡ ታበየ፤ አምላኩንም እግዚአብሔርን በደለ፤ ወደ መቅደስ ገብቶ በዕጣን መሠዊያ ላይ ዐጠነ።

Ver Capítulo Copiar




2 ዜና መዋዕል 26:16
24 Referencias Cruzadas  

በስ​ም​ን​ተ​ኛ​ውም ወር በዐ​ሥራ አም​ስ​ተ​ኛው ቀን በልቡ ባሰ​በው ቀን ወደ ሠራው መሠ​ዊያ ወጣ፤ ለእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች በዓል አደ​ረ​ገ​ላ​ቸው፤ ወደ መሠ​ዊ​ያ​ውም ሊሠዋ ወጣ።


እነ​ሆም፥ አንድ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ከይ​ሁዳ ወደ ቤቴል መጣ፤ ኢዮ​ር​ብ​ዓ​ምም መሥ​ዋ​ዕት ይሠዋ ዘንድ በመ​ሠ​ዊ​ያው አጠ​ገብ ቆሞ ነበር።


ኤዶ​ም​ያ​ስን በእ​ው​ነት መታህ፤ ልብ​ህ​ንም ከፍ ከፍ አደ​ረ​ግህ፤ በዚያ ተመካ፤ በቤ​ት​ህም ተቀ​መጥ፤ አንተ፥ ይሁ​ዳም ከአ​ንተ ጋር ትወ​ድቁ ዘንድ ስለ ምን መከ​ራን ትሻ​ለህ?” ብሎ ወደ ይሁዳ ንጉሥ ወደ አሜ​ስ​ያስ ላከ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ንጉ​ሡን በደዌ ዳሰ​ሰው፤ እስ​ከ​ሚ​ሞ​ት​በ​ትም ቀን ለም​ጻም ሆነ፤ በተ​ለየ ቤትም ይቀ​መጥ ነበር፤ የን​ጉ​ሡም ልጅ ኢዮ​አ​ታም በን​ጉሡ ቤት ላይ ሠል​ጥኖ ለሀ​ገሩ ሕዝብ ይፈ​ርድ ነበር።


እን​ዲ​ህም ሆነ፤ የሮ​ብ​ዓም መን​ግ​ሥት በጸ​ናች ጊዜ፥ እር​ሱም በበ​ረታ ጊዜ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሕግ ረሳ፤ እስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ ከእ​ርሱ ጋር ረሱ።


አን​ተም፦ እነሆ፥ ኤዶ​ም​ያ​ስን መት​ቻ​ለሁ ብለህ በል​ብህ ኰር​ተ​ሃል፤ በቤ​ትህ ተቀ​መጥ፤ አንተ ከይ​ሁዳ ጋር ትወ​ድቅ ዘንድ ስለ​ምን መከ​ራን በራ​ስህ ትሻ​ለህ?”


በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም በብ​ል​ሃ​ተ​ኞች እጅ የተ​ሠ​ሩ​ትን ፥ በግ​ን​ብና በቅ​ጥር ላይ የሚ​ኖ​ሩ​ትን፥ ፍላ​ጻና መርግ የሚ​ወ​ረ​ወ​ር​ባ​ቸ​ውን መሣ​ሪ​ያ​ዎች አደ​ረገ፤ እስ​ኪ​በ​ረ​ታም ድረስ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በድ​ንቅ ረድ​ቶ​ታ​ልና የመ​ሣ​ሪ​ያ​ዎቹ ዝና እስከ ሩቅ ድረስ ተሰማ።


አባ​ቱም ዖዝ​ያን እን​ዳ​ደ​ረገ ሁሉ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ቅን ነገር አደ​ረገ፤ ነገር ግን ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መቅ​ደስ አል​ገ​ባም፤ ሕዝ​ቡም ገና ይበ​ድል ነበር።


ሕዝ​ቅ​ያስ ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሰጠው ቸር​ነት መጠን አላ​ደ​ረ​ገም፤ ልቡም ኮራ፤ ስለ​ዚ​ህም በእ​ር​ሱና በይ​ሁዳ፥ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ላይ ቍጣ ሆነ።


ከጥል በፊት ስድብ ይቀድማል፥ ከመውደቅም በፊት ክፋትን ማወቅ።


እነሆ፥ ነፍሱ ኰርታለች፥ በውስጡም ቅን አይደለችም፣ ጻድቅ ግን በእምነቱ በሕይወት ይኖራል።


የሌ​ዊም ልጅ የቀ​ዓት ልጅ የይ​ስ​ዓር ልጅ ቆሬ ከኤ​ል​ያብ ልጆች ከዳ​ታ​ንና ከአ​ቤ​ሮን፥ ከሮ​ቤ​ልም ልጅ ከፋ​ሌት ልጅ ከአ​ው​ናን ጋር ተና​ገረ።


እያ​ን​ዳ​ን​ዱም ጥና​ውን ወሰደ፤ እሳ​ትም አደ​ረ​ገ​በት፤ ዕጣ​ንም ጨመ​ረ​በት፤ ሙሴና አሮ​ንም በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ደጃፍ ቆሙ።


እሳ​ትም ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ወጥታ ያጥኑ የነ​በ​ሩ​ትን ሁለት መቶ አምሳ ሰዎች በላች።


ነገም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት እሳት አድ​ር​ጉ​ባ​ቸው፤ ዕጣ​ንም ጨም​ሩ​ባ​ቸው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የሚ​መ​ር​ጠው ይህ ሰው ለሌዊ ልጆች ቅዱስ ይሁ​ን​ላ​ቸው።”


እን​ዲ​ህም ይሆ​ናል፤ የመ​ረ​ጥ​ሁት ሰው በትር ትለ​መ​ል​ማ​ለች፤ በእ​ና​ን​ተም ላይ የሚ​ያ​ጕ​ረ​መ​ር​ሙ​ባ​ችሁ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ማጕ​ረ​ም​ረም ከእኔ ዘንድ አጠ​ፋ​ለሁ።”


ከግ​ብፅ ምድር ከባ​ር​ነት ቤት ያወ​ጣ​ህን፥


በል​ብ​ህም፦ በጕ​ል​በቴ፥ በእ​ጄም ብር​ታት ይህን ሁሉ ታላቅ ኀይል አደ​ረ​ግሁ እን​ዳ​ትል።


በመ​ታ​ለ​ልና ራስን ዝቅ በማ​ድ​ረግ ለመ​ላ​እ​ክት አም​ልኮ ትታ​ዘዙ ዘንድ ወድዶ፥ በአ​ላ​የ​ውም በከ​ንቱ የሥ​ጋው ምክር እየ​ተ​መካ የሚ​ያ​ሰ​ን​ፋ​ችሁ አይ​ኑር።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos