Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘዳግም 8:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 “ዛሬ እኔ አን​ተን የማ​ዝ​ዘ​ውን ትእ​ዛ​ዙ​ንና ፍር​ዱን፥ ሥር​ዐ​ቱ​ንም ባለ​መ​ጠ​በቅ አም​ላ​ክ​ህን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እን​ዳ​ት​ረሳ ተጠ​ን​ቀቅ፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 በዛሬዪቱ ዕለት የምሰጥህን ትእዛዙን፣ ሕጉንና ሥርዐቱን ባለመጠበቅ አምላክህን እግዚአብሔርን እንዳትረሳው ተጠንቀቅ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 “ዛሬ እኔ አንተን የማዘውን ትእዛዞቹንና ፍርዱን ሥርዓቱንም ባለመጠበቅ፥ ጌታ አምላክህን እንዳትረሳ ተጠንቀቅ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 “እግዚአብሔር አምላክህን በመርሳት፥ እኔ ዛሬ የማዝህን ትእዛዞች፥ ደንቦችና ሥርዓቶች እንዳታፈርስ ተጠንቀቅ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 ዛሬ እኔ አንተን የማዝዘውን ትእዛዙንና ፍርዱን ሥርዓቱንም ባለመጠበቅ አምላክህን እግዚአብሔርን እንዳትረሳ ተጠንቀቅ፤

Ver Capítulo Copiar




ዘዳግም 8:11
19 Referencias Cruzadas  

የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ምሕ​ረት ለሰው ልጆ​ችም ያደ​ረ​ገ​ውን ድን​ቁን ንገሩ፤


አላዋቂዎችን አለመመለሳቸው ትገድላቸዋለችና፥ ሰነፎችንም ምርመራቸው ትገድላቸዋለች።


እር​ሱም በዘ​ርፉ ይሁ​ን​ላ​ችሁ፤ ትመ​ለ​ከ​ቱ​ታ​ላ​ች​ሁም፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ትእ​ዛ​ዛት ታስ​ባ​ላ​ችሁ፤ ታደ​ር​ጉ​አ​ቸ​ው​ማ​ላ​ችሁ፤ እነ​ር​ሱን በመ​ከ​ተል ያመ​ነ​ዘ​ራ​ች​ሁ​ባ​ትን የሕ​ሊ​ና​ች​ሁ​ንና የዐ​ይ​ኖ​ቻ​ች​ሁን ፈቃድ አት​ከ​ተሉ።


“ለራ​ስህ ዕወቅ፤ ሰው​ነ​ት​ህን ፈጽ​መህ ጠብቅ፤ ዐይ​ኖ​ችህ ያዩ​ትን ይህን ሁሉ ነገር አት​ርሳ፤ በሕ​ይ​ወ​ትህ ዘመን ሁሉ ከል​ቡ​ናህ አይ​ውጣ፤ ለል​ጆ​ች​ህና ለልጅ ልጆ​ች​ህም አስ​ተ​ም​ራ​ቸው።


ከግ​ብፅ ምድር ከባ​ር​ነት ቤት ያወ​ጣ​ህን፥


ብር​ሃ​ንን እንደ ልብስ ተጐ​ና​ጸ​ፍህ፤ ሰማ​ይ​ንም እንደ መጋ​ረጃ ዘረ​ጋህ፤


አንቺ ግን ሰማ​ያ​ትን የፈ​ጠ​ረ​ውን፥ ምድ​ር​ንም የመ​ሠ​ረ​ታ​ትን ፈጣ​ሪ​ሽን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ረስ​ተ​ሻል፤ ያጠ​ፋሽ ዘንድ ባዘ​ጋጀ ጊዜ ከአ​ስ​ጨ​ና​ቂው ቍጣ የተ​ነሣ ሁል​ጊዜ ቀኑን ሁሉ ፈር​ተ​ሻል፤ ይቈ​ጣሽ ዘንድ መክ​ሮ​አ​ልና፤ አሁን የሚ​ያ​ስ​ጨ​ን​ቅሽ ቍጣው የት አለ?


ለእስራኤል ሁሉ ሥርዓትንና ፍርድን አድርጌ በኮሬብ ያዘዝሁትን የባሪያዬን የሙሴን ሕግ አስቡ።


በድሩ ወይም በማጉ ላይ ቢሆን፥ የበግ ጠጕር ወይም የተ​ልባ እግር ቢሆን፥ ቆዳ ወይም ከቆዳ የሚ​ደ​ረግ ነገር ቢሆን፥


“አሁ​ንም እስ​ራ​ኤል ሆይ፥ እን​ድ​ታ​ደ​ር​ጉ​አ​ቸው፥ በሕ​ይ​ወ​ትም እን​ድ​ት​ኖሩ፥ እን​ድ​ት​በ​ዙም፥ የአ​ባ​ቶ​ቻ​ች​ሁም አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወደ​ሚ​ሰ​ጣ​ችሁ ምድር ገብ​ታ​ችሁ እን​ድ​ት​ወ​ርሱ፥ ዛሬ የማ​ስ​ተ​ም​ራ​ች​ሁን ሥር​ዐ​ትና ፍርድ ስሙ።


እነሆ፥ እና​ንተ ገብ​ታ​ችሁ በም​ት​ወ​ር​ሱ​አት ምድር ውስጥ እን​ዲህ ታደ​ርጉ ዘንድ አም​ላኬ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዳ​ዘ​ዘኝ ሥር​ዐ​ትና ፍር​ድን አሳ​የ​ኋ​ችሁ።


ያል​ሞ​ላ​ሃ​ቸ​ው​ንም ሀብ​ትን የሞሉ ቤቶች፥ ያል​ማ​ስ​ሃ​ቸ​ው​ንም የተ​ማሱ ጕድ​ጓ​ዶች፥ ያል​ተ​ከ​ል​ሃ​ቸ​ው​ንም ወይ​ንና ወይራ በሰ​ጠህ ጊዜ፥ በበ​ላ​ህና በጠ​ገ​ብ​ህም ጊዜ፤


እን​ግ​ዲህ ታደ​ር​ጓት ዘንድ እኔ ዛሬ ለእ​ና​ንተ የማ​ዝ​ዛ​ትን ትእ​ዛ​ዝና ሥር​ዐት፥ ፍር​ድ​ንም ጠብቁ።


እኔም ዛሬ በፊ​ታ​ችሁ የማ​ኖ​ራ​ትን ሥር​ዐ​ትና ፍርድ ሁሉ ታደ​ርጉ ዘንድ ጠብቁ።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ክፉ አደ​ረጉ፤ አም​ላ​ካ​ቸ​ው​ንም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ረስ​ተው በዓ​ሊ​ም​ንና አስ​ታ​ሮ​ትን አመ​ለኩ።


አባ​ቶ​ቻ​ቸው ስለ በዓል ስሜን እንደ ረሱ፥ እያ​ን​ዳ​ንዱ ለባ​ል​ን​ጀ​ራው በሚ​ና​ገ​ራት ሕል​ማ​ቸው ሕዝ​ቤን ስሜን ለማ​ስ​ረ​ሳት ያስ​ባሉ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios