እርስ በርሳቸውም፥ “ኑ ለእኛ ከተማና ራሱ ወደ ሰማይ የሚደርስ ግንብ እንሥራ፤ በምድር ፊት ሁሉ ላይ ሳንበተን ስማችንን እናስጠራው” ተባባሉ።
ዘዳግም 4:27 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም በአሕዛብ መካከል ይበትናችኋል፤ እግዚአብሔር በውስጣቸው በሚያኖራችሁ በአሕዛብ መካከልም በቍጥር ጥቂቶች ሆናችሁ ትቀራላችሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር እናንተን በአሕዛብ መካከል ይበትናችኋል፤ እግዚአብሔር በሚበትናችሁ አሕዛብ መካከል የምትተርፉት ጥቂቶቻችሁ ብቻ ናችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታም በአሕዛብ መካከል ይበትናችኋል፥ ጌታ በውስጣቸው በሚያኖራችሁ በአሕዛብ መካከልም ጥቂቶች ሆናችሁ ትቀራላችሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር በሌሎች ሕዝቦች መካከል ይበታትናችኋል፤ እግዚአብሔር በሚያኖራችሁ በአሕዛብ መካከል ጥቂቶቻችሁ ብቻ ትተርፋላችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም በአሕዛብ መካከል ይበትናችኋል፥ እግዚአብሔር በውስጣቸው በሚያኖራችሁ በአሕዛብ መካከልም ጥቂቶች ሆናችሁ ትቀራላችሁ። |
እርስ በርሳቸውም፥ “ኑ ለእኛ ከተማና ራሱ ወደ ሰማይ የሚደርስ ግንብ እንሥራ፤ በምድር ፊት ሁሉ ላይ ሳንበተን ስማችንን እናስጠራው” ተባባሉ።
ያዕቆብም ስምዖንንና ሌዊን እንዲህ አላቸው፥ “ክፉ አደረጋችሁብኝ፤ በዚች ሀገር በሚኖሩ በከነዓናውያንና በፌርዜዎናውያን ሰዎች ዘንድ አስጠላችሁኝ። እኔ በቍጥር ጥቂት ነኝ፤ እነርሱ በእኔ ላይ ይሰበሰቡና ይወጉኛል፤ እኔና ቤቴም እንጠፋለን።”
እነርሱም፥ “በዚያ ስፍራ ያሉት ከምርኮ የተረፉት ቅሬታዎች በታላቅ መከራና ስድብ አሉ፤ የኢየሩሳሌምም ቅጥር ፈርሶአል፥ በሮችዋም በእሳት ተቃጥለዋል” አሉኝ።
ወይራ በተመታ ጊዜ ሁለት ወይም ሦስት ፍሬ በራሱ ላይ እንደሚቀር፥ አራት ወይም አምስት በዛፊቱ ጫፍ እንደሚገኝ፥ በእርሱ ዘንድ ቃርሚያ ይቀራል” ይላል የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር።
ስለዚህ ከዚች ምድር እናንተና አባቶቻችሁ ወደ አላወቃችኋት ምድር እጥላችኋለሁ፤ በዚያም ምሕረትን ለማያደርጉላችሁ ሌሎች አማልክት ቀንና ሌሊት ታገለግላላችሁ።”
ስለዚህ፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እኔ ወደ አሕዛብ አርቄአቸዋለሁ፤ ወደ ሀገሮችም እበትናቸዋለሁ፤ ይሁን እንጂ በመጡባቸው ሀገሮች በእነዚያ ትንሽ መቅደስ እሆናቸዋለሁ በል።
“ሞሳሕና ቶቤል፥ ሠራዊታቸውም ሁሉ በዚያ አሉ፤ መቃብራቸውም በዙሪያቸው ነው፤ ሁሉም ሳይገረዙ በሰይፍ ተገድለዋል፤ በሕያዋን ምድር ያስፈሩ ነበርና።
እናንተንም በአሕዛብ መካከል እበትናችኋለሁ፤ በሄዳችሁበትም ሁሉ ሰይፍ ታጠፋችኋለች፤ ምድራችሁም የተፈታች ትሆናለች፤ ከተሞቻችሁም ባድማ ይሆናሉ።
ወደ ማያውቁአቸውም አሕዛብ ሁሉ በዐውሎ ነፋስ በተንኋቸው። እንዲሁ ከእነርሱ በኋላ ምድሪቱ ባድማ ሆናለች፥ የሚተላለፍባትና የሚመላለስባትም አልነበረም፣ ያማረችውንም ምድር ባድማ አደረጉአት።
“እግዚአብሔርም አንተን፥ በአንተም ላይ የምትሾማቸውን አለቆችህን አንተና አባቶችህ ወዳላወቃችኋቸው ሕዝብ ይወስድሃል፤ በዚያም ሌሎችን የእንጨትና የድንጋይ አማልክትን ታመልካለህ።
ዛሬም እንዳሉ እግዚአብሔር በቍጣና በመቅሠፍት፥ በታላቅም መዓት ከምድራቸው ነቀላቸው፤ ወደ ሌላም ምድር ጣላቸው።
እግዚአብሔርም ኀጢአትህን ይቅር ይልሃል ይራራልህማል፤ እግዚአብሔርም አንተን ከበተነበት ከአሕዛብ ሁሉ መካከል መልሶ ይሰበስብሃል።