Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘዳግም 29:28 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

28 ዛሬም እን​ዳሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በቍ​ጣና በመ​ቅ​ሠ​ፍት፥ በታ​ላ​ቅም መዓት ከም​ድ​ራ​ቸው ነቀ​ላ​ቸው፤ ወደ ሌላም ምድር ጣላ​ቸው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

28 በአስፈሪ ቍጣና በታላቅ መዓት እግዚአብሔር ከምድራቸው ነቀላቸው፤ አሁን እንደ ሆነውም ወደ ሌላ ምድር ጣላቸው” የሚል ይሆናል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

28 በቁጣና በመቅሠፍት፥ በታላቅም መዓት ጌታ ከምድራቸው ነቀላቸው፤ ወደ ሌላም ምድር ጣላቸው። ዛሬም በዚያው ይገኛሉ።’

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

28 እግዚአብሔርም በብርቱ ተቈጣ፤ ከብርቱ ቊጣውም የተነሣ ከምድራቸው ነቃቅሎ ወደ ባዕድ አገር እንዲሰደዱ አደረጋቸው። ስለዚህም እነሆ፥ ዛሬም በዚያው ይገኛሉ።’

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

28 ዛሬም እንዳሉ እግዚአብሔር በቁጣና በመቅሠፍት በታላቅም መዓት ከምድራቸው ነቀላቸው፥ ወደ ሌላም ምድር ጣላቸው።

Ver Capítulo Copiar




ዘዳግም 29:28
24 Referencias Cruzadas  

በዚያ ጊዜም ሸም​በቆ በውኃ ውስጥ እን​ደ​ሚ​ን​ቀ​ሳ​ቀስ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲሁ እስ​ራ​ኤ​ልን ይመ​ታል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ያስ​ቈጡ ዘንድ የማ​ም​ለ​ኪያ አፀድ ተክ​ለ​ዋ​ልና ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ከሰ​ጣ​ቸው ከዚች ከመ​ል​ካ​ሚቱ ምድር እስ​ራ​ኤ​ልን ይነ​ቅ​ላል፤ በወ​ን​ዙም ማዶ ይበ​ት​ና​ቸ​ዋል።


ስለ​ዚ​ህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ እጅግ ተቈጣ፤ ከፊ​ቱም ጣላ​ቸው፤ ከይ​ሁ​ዳም ነገድ ብቻ በቀር ማንም አል​ቀ​ረም።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በባ​ሪ​ያ​ዎቹ በነ​ቢ​ያት ሁሉ አፍ እንደ ተና​ገ​ረው እስ​ራ​ኤ​ልን ከፊቱ እስ​ኪ​ያ​ወጣ ድረስ ከእ​ር​ስዋ አል​ራ​ቁም። እስ​ራ​ኤ​ልም እስከ ዛሬ ድረስ ከም​ድሩ ወደ አሦር ፈለሰ።


በሆ​ሴ​ዕም በዘ​ጠ​ነ​ኛው ዓመት የአ​ሦር ንጉሥ ሰማ​ር​ያን ያዘ፤ እስ​ራ​ኤ​ል​ንም ወደ አሶር አፈ​ለሰ፤ በአ​ላ​ሔና በአ​ቦር፤ በጎ​ዛ​ንም ወንዝ፤ በሜ​ዶ​ንም ከተ​ሞች አኖ​ራ​ቸው።


እኔም ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ችሁ ከሰ​ጠ​ኋ​ቸው ምድር እነ​ቅ​ላ​ች​ኋ​ለሁ፤ ለስ​ሜም የቀ​ደ​ስ​ሁ​ትን ይህን ቤት ከፊቴ እጥ​ለ​ዋ​ለሁ፤ በአ​ሕ​ዛ​ብም ሁሉ መካ​ከል ምሳ​ሌና ተረት አደ​ር​ገ​ዋ​ለሁ።


ከአ​ባ​ቶ​ቻ​ችን ዘመን ጀም​ረን እስከ ዛሬ ድረስ እጅግ በድ​ለ​ናል፤ ስለ ኀጢ​አ​ታ​ችን እኛና ልጆ​ቻ​ችን ንጉ​ሦ​ቻ​ችን፥ ካህ​ና​ቶ​ቻ​ች​ንም ለሰ​ይ​ፍና ለም​ርኮ፥ ለብ​ዝ​በ​ዛና ለዕ​ፍ​ረት በአ​ሕ​ዛብ ነገ​ሥ​ታት እጅ ተጣ​ልን፤ እስከ ዛሬም ድረስ በፊ​ታ​ችን እፍ​ረት እን​ኖ​ራ​ለን።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የግ​ብ​ዞ​ችን አጥ​ን​ቶች በት​ኖ​አ​ልና በዚያ የሚ​ያ​ስ​ፈራ ሳይ​ኖር እጅግ ፈሩ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አዋ​ር​ዶ​አ​ቸ​ዋ​ልና አፈሩ።


የባ​ሪ​ያ​ዎ​ች​ህ​ንም በድ​ኖች ለሰ​ማይ ወፎች መብል አደ​ረጉ፥ የጻ​ድ​ቃ​ን​ህ​ንም ሥጋ ለም​ድር አራ​ዊት፤


የክፉዎች መንገዶች ከምድር ላይ ይጠፋሉ፤ ዓመፀኞችም ከእርስዋ ይሰደዳሉ።


አደ​ር​ግ​ባ​ችሁ ዘንድ ከአ​ሰ​ብ​ሁት ክፉ ነገር ተመ​ል​ሻ​ለ​ሁና በዚች ምድር ብት​ቀ​መጡ እሠ​ራ​ች​ኋ​ለሁ እንጂ አላ​ፈ​ር​ሳ​ች​ሁም፥ እተ​ክ​ላ​ች​ኋ​ለሁ እንጂ አል​ነ​ቅ​ላ​ች​ሁም።


ነገር ግን በመ​ዓት ተነ​ቀ​ለች፤ ወደ መሬ​ትም ተጣ​ለች፤ የሚ​ያ​ቃ​ጥ​ልም ነፋስ ፍሬ​ዋን አደ​ረቀ፤ ብር​ቱ​ዎች በት​ሮ​ች​ዋም ተሰ​በ​ሩና ደረቁ፤ እሳ​ትም በላ​ቻ​ቸው።


አሁ​ንም በም​ድረ በዳ፥ በደ​ረ​ቅና በተ​ጠ​ማች መሬት ተተ​ከ​ለች።


“እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከጠ​ላ​ቶ​ችህ ፊት የተ​መ​ታህ ያደ​ር​ግ​ሃል፤ በአ​ንድ መን​ገድ ትወ​ጣ​ባ​ቸ​ዋ​ለህ፤ በሰ​ባት መን​ገ​ድም ከእ​ነ​ርሱ ትሸ​ሻ​ለህ፤ በም​ድ​ርም መን​ግ​ሥ​ታት ሁሉ የተ​በ​ተ​ንህ ትሆ​ና​ለህ።


“እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አን​ተን፥ በአ​ን​ተም ላይ የም​ት​ሾ​ማ​ቸ​ውን አለ​ቆ​ች​ህን አን​ተና አባ​ቶ​ችህ ወዳ​ላ​ወ​ቃ​ች​ኋ​ቸው ሕዝብ ይወ​ስ​ድ​ሃል፤ በዚ​ያም ሌሎ​ችን የእ​ን​ጨ​ትና የድ​ን​ጋይ አማ​ል​ክ​ትን ታመ​ል​ካ​ለህ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከም​ድር ዳር እስከ ዳር​ቻዋ ድረስ ወደ አሉ አሕ​ዛብ ሁሉ ይበ​ት​ን​ሃል፤ በዚ​ያም አን​ተና አባ​ቶ​ችህ ያላ​ወ​ቃ​ች​ኋ​ቸ​ውን ሌሎ​ችን አማ​ል​ክት፥ እን​ጨ​ት​ንና ድን​ጋ​ይን ታመ​ል​ካ​ለህ።


“እን​ዲ​ህም ይሆ​ናል፤ እኔ በፊ​ትህ ያኖ​ር​ሁት ይህ ነገር ሁሉ፥ በረ​ከ​ቱና መር​ገሙ በወ​ረ​ደ​ብህ ጊዜ፥ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሚ​በ​ት​ንህ በዚያ በአ​ሕ​ዛብ ሁሉ መካ​ከል ሆነህ በል​ብህ ዐስ​በው፤


በእኔ ዘንድ ያለው ትእ​ዛዝ ይህ አይ​ደ​ለ​ምን? በመ​ዝ​ገ​ቤስ የታ​ተመ አይ​ደ​ለ​ምን?


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በአ​ሕ​ዛብ መካ​ከል ይበ​ት​ና​ች​ኋል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በው​ስ​ጣ​ቸው በሚ​ያ​ኖ​ራ​ችሁ በአ​ሕ​ዛብ መካ​ከ​ልም በቍ​ጥር ጥቂ​ቶች ሆና​ችሁ ትቀ​ራ​ላ​ችሁ።


እንደ ዛሬም በሕ​ይ​ወት እን​ዲ​ያ​ኖ​ረን፥ ሁል​ጊ​ዜም መል​ካም እን​ዲ​ሆ​ን​ልን፥ አም​ላ​ካ​ች​ንን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እን​ፈራ ዘንድ፥ ይህ​ች​ንም ሥር​ዐት ሁሉ እና​ደ​ርግ ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አዘ​ዘን።


ነገር ግን ዛሬ እንደ ሆነ ለአ​ባ​ቶ​ችህ የማ​ለ​ውን ቃል ኪዳን ያጸና ዘንድ እርሱ ኀይ​ልን ስለ​ሚ​ሰ​ጥህ አም​ላ​ክ​ህን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አስ​በው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos