Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘፍጥረት 11:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 እርስ በር​ሳ​ቸ​ውም፥ “ኑ ለእኛ ከተ​ማና ራሱ ወደ ሰማይ የሚ​ደ​ርስ ግንብ እን​ሥራ፤ በም​ድር ፊት ሁሉ ላይ ሳን​በ​ተን ስማ​ች​ንን እና​ስ​ጠ​ራው” ተባ​ባሉ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 ከዚያም “ለስማችን መጠሪያ እንዲሆንና በምድር ላይ እንዳንበተን፣ ኑ፤ ከተማ፣ ሰማይ የሚደርስ ግንብም ለራሳችን እንሥራ” አሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 እንዲህም፦ “ኑ ለእኛ ከተማ እንመስርት፥ በዚያም ጫፉ እስከ ሰማይ የሚደርስ ግንብ እንሥራ፤ በምድር ላይ ሳንበታተንም ስማችንን እናስጠራ” አሉ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 እንዲህም አሉ፦ “ኑ አንድ ከተማ እንመሥርት፤ በዚያም ጫፉ እስከ ሰማይ የሚደርስ ግንብ እንሥራ፤ በምድር ላይ እንዳንበታተን ስማችንን እናስጠራ።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 እንዲህም፤ ኑ ለእኛ ከተማና ራሱ ወደ ሰማይ የሚደርስ ግንብ እንሥራ፤ በምድር ላይ ሳንበተንም ስምችንን እናስጠራው አሉ።

Ver Capítulo Copiar




ዘፍጥረት 11:4
17 Referencias Cruzadas  

በእ​ነ​ዚ​ያም ወራት ረዓ​ይት በም​ድር ላይ ነበሩ። ከዚ​ያም በኋላ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጆች ወደ ሰው ሴቶች ልጆች በገቡ ጊዜ ልጆ​ችን ወለ​ዱ​ላ​ቸው፤ እነ​ር​ሱም በዱሮ ዘመን ስማ​ቸ​ውን ያስ​ጠሩ ኀያ​ላን ሰዎች ሆኑ።


ዳዊ​ትም በተ​መ​ለሰ ጊዜ ከኤ​ዶ​ም​ያስ ዐሥራ ስም​ንት ሺህ ሰዎች በጨው ሸለቆ ውስጥ በመ​ም​ታቱ ስሙ ተጠራ።


የጻድቃን መታሰቢያ ከምስጋና ጋር ነው። የኃጥኣን ስም ግን ይጠፋል።


ባቢ​ሎ​ንም ወደ ሰማይ ብት​ወጣ፥ ቅፅ​ሮ​ች​ዋ​ንም በኀ​ይ​ልዋ ብታ​ጸና፥ ከእኔ ዘንድ አጥ​ፊ​ዎች ይመ​ጡ​ባ​ታል፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


በክ​ንዱ ኀይ​ልን አደ​ረገ፤ በል​ባ​ቸው ዐሳብ የሚ​ታ​በ​ዩ​ት​ንም በተ​ና​ቸው።


ከባ​ል​ን​ጀ​ራ​ችሁ ክብ​ርን የም​ት​መ​ርጡ፥ ከአ​ንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ክብ​ርን የማ​ትሹ እና​ንተ እን​ዴት ልታ​ምኑ ትች​ላ​ላ​ችሁ?


ወዴት እን​ወ​ጣ​ለን? ሕዝቡ ታላ​ቅና ብዙ ነው፤ ከእ​ኛም ይጠ​ነ​ክ​ራሉ፤ ከተ​ሞ​ቹም ታላ​ላ​ቆች፥ የተ​መ​ሸ​ጉም፥ እስከ ሰማ​ይም የደ​ረሱ ናቸው፤ የረ​ዐ​ይ​ት​ንም ልጆች ደግሞ በዚያ አየ​ና​ቸው ብለው ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ልባ​ች​ንን አስ​ፈ​ሩት።’


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በአ​ሕ​ዛብ መካ​ከል ይበ​ት​ና​ች​ኋል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በው​ስ​ጣ​ቸው በሚ​ያ​ኖ​ራ​ችሁ በአ​ሕ​ዛብ መካ​ከ​ልም በቍ​ጥር ጥቂ​ቶች ሆና​ችሁ ትቀ​ራ​ላ​ችሁ።


“እስ​ራ​ኤል ሆይ፥ ስማ፤ ከአ​ንተ የበ​ለ​ጡ​ት​ንና የበ​ረ​ቱ​ትን አሕ​ዛብ፥ የቅ​ጽ​ራ​ቸው ግንብ እስከ ሰማይ የሚ​ደ​ርስ ታላ​ላ​ቆች ከተ​ሞ​ችን ለመ​ው​ረስ ትገቡ ዘንድ ዛሬ ዮር​ዳ​ኖ​ስን ትሻ​ገ​ረ​ዋ​ለህ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos