ማሕፀንን የሚከፍተውን ሁሉ ለይ፤ ከመንጋህና ከከብትህም መጀመሪያ የሚወለደው ተባት ለእግዚአብሔር ይሆናል።
ዘዳግም 15:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ላምህና በግህ የወለዱትን ተባት የሆነውን በኵራት ለአምላክህ ለእግዚአብሔር ትቀድሳለህ፤ በበሬህ በኵራት አትሥራበት፤ የበግህንም በኵራት አትሸልት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የቀንድ ከብት፣ የበግና የፍየል መንጋዎችህን ተባዕት በኵር ሁሉ ለአምላክህ ለእግዚአብሔር ቀድስ። የበሬህን በኵር አትሥራበት፤ የበግህንም በኵር አትሸልት፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “የቀንድ ከብት፥ የበግና የፍየል መንጋዎችህን ተባዕት በኩር ሁሉ ለጌታ ለእግዚአብሔር ትቀድሳለህ። የበሬህን በኩር አትሥራበት፤ የበግህንም በኩር አትሸልት፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ከከብትህ ወይም ከበግህ መንጋ የሚወለደውን ወንድ የሆነ በኲር ሁሉ ለአምላክህ ለእግዚአብሔር የተለየ እንዲሆን አድርግ፤ በኲር የሆኑትን በሬዎች ለማንኛውም ተግባር አትጠቀምባቸው፤ እንዲሁም ከበጎች መንጋ በኲሮችን ጠጒራቸውን አትሸልት፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ላምህና በግህ የወለዱትን ተባት የሆነውን በኩራት ለአምላክህ ለእግዚአብሔር ትቀድሳለህ፤ በበሬህ በኩራት አትሥራበት፥ የበግህንም በኩራት አትሸልት። |
ማሕፀንን የሚከፍተውን ሁሉ ለይ፤ ከመንጋህና ከከብትህም መጀመሪያ የሚወለደው ተባት ለእግዚአብሔር ይሆናል።
“በእስራኤል ልጆች ዘንድ ከሰውም፥ ከእንስሳም መጀመሪያ የተወለደውን ማሕፀንን የሚከፍት በኵር ሁሉ ለእኔ ለይልኝ፤ የእኔ ነው።”
እንዲሁም በበሬዎችህና በበጎችህ፥ በአህያህም ታደርገዋለህ፤ ሰባት ቀን ከእናቱ ጋር ይቀመጥ፤ በስምንተኛውም ቀን ለእኔ ትሰጠዋለህ።
“ከእንስሳህ የሚወለድ በኵር ሁሉ ለእግዚአብሔር ነው፤ ማንም ይለውጠው ዘንድ አይቻለውም፤ በሬ ቢሆን ወይም በግ ለእግዚአብሔር ነው።
ከሰው እስከ እንስሳ ቢሆን፥ ለእግዚአብሔር ከሚያቀርቡት ሥጋ ሁሉ፥ መጀመሪያ የሚወለድ ሁሉ ለአንተ ይሆናል፤ ነገር ግን የሰውን በኵራት ፈጽሞ ትቤዠዋለህ፤ ያልነጹትንም እንስሳት በኵራት ትቤዣለህ።
ነገር ግን የላሞቹን በኵራት፥ ወይም የበጎቹን በኵራት፥ የፍየሎችንም በኵራት አትቤዥም፤ ቅዱሳን ናቸውና፤ ደማቸውን በመሠዊያው ላይ ትረጨዋለህ፤ ስባቸውንም ለእግዚአብሔር በጎ መዓዛ እንዲሆን መሥዋዕት ታደርገዋለህ።
በኵር ሁሉ ለእኔ ነውና፤ በግብፅ ምድር በኵርን ሁሉ በመታሁ ቀን ከእስራኤል ዘንድ በኵርን ሁሉ፥ ሰውንና እንስሳን፥ ለእኔ ለይችአለሁ፤ ለእኔ ይሁኑ። እኔ እግዚአብሔር ነኝና።”
ልጁ በብዙዎች ወንድሞች መካከል በኵር ይሆን ዘንድ አስቀድሞ ያወቃቸውንና የመረጣቸውን እነርሱን ልጁን ይመስሉ ዘንድ አዘጋጅቶአቸዋል።
በዚያን ጊዜ አምላካችሁ እግዚአብሔር ስሙ ይጠራበት ዘንድ ወደዚያ ወደ መረጠው ስፍራ፥ እኔ የማዝዛችሁን ሁሉ፥ የሚቃጠለውን መሥዋዕታችሁን፥ ቍርባናችሁንም፥ ዐሥራታችሁንም፥ ከእጃችሁ ሥራ ቀዳምያቱን የተመረጠውንም መባችሁን ሁሉ፥ ለአምላካችሁም የተሳላችሁትን ሁሉ ውሰዱ።
የእህልህን፥ የወይን ጠጅህን፥ የዘይትህንም ዐሥራት፥ የላምህንና የበግህንም በኵራት፥ የተሳልኸውንም ስእለት ሁሉ፥ በፈቃድህ ያቀረብኸውን፥ የእጅህንም ቀዳምያት በከተሞችህ ሁሉ ውስጥ መብላት አትችልም።
በዘመንህም ሁሉ አምላክህን እግዚአብሔርን መፍራትን ትማር ዘንድ፥ ስሙ እንዲጠራበት በመረጠው ስፍራ በአምላክህ በእግዚአብሔር ፊት የእህልህን፥ የወይንህን፥ የዘይትህንም ዐሥራት፥ የላምህንና የበግህንም በኵራት ብላ።
እርሱንም አርነት ባወጣኸው ጊዜ የምንደኝነቱን ሥራ ሁለት ዕጥፍ አድርጎ ስድስት ዓመት አገልግሎሃልና አያስጨንቅህ፤ አምላክህም እግዚአብሔር በምትሠራው ሁሉ ይባርክሃል።
አንተ፥ ወንድ ልጅህና ሴት ልጅህ፥ ወንድ ባሪያህና ሴት ባሪያህ፥ በሀገርህም ውስጥ ያለው ሌዋዊ፥ በመካከልህም ያሉ መጻተኛና ድሃ-አደግ፥ መበለትም አምላክህ እግዚአብሔር በዚያ ስሙ ይጠራበት ዘንድ በሚመርጠው ስፍራ በአምላክህ በእግዚአብሔር ፊት ደስ ይበላችሁ።
አንተም፥ ወንድ ልጅህና ሴት ልጅህ፥ ወንድ ባሪያህና ሴት ባሪያህ፥ በሀገርህም ውስጥ ያለ ሌዋዊና መጻተኛ፥ ድሃ-አደግና መበለትም በበዓልህ ደስ ይበላችሁ።
ስማቸው በሰማይ ወደ ተጻፈ ወደ ማኅበረ በኵርም፥ ሁሉን ወደሚገዛም ወደ እግዚአብሔር፥ ወደ ፍጹማን ጻድቃንም ነፍሳት፥