Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘፀአት 22:30 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

30 እን​ዲ​ሁም በበ​ሬ​ዎ​ች​ህና በበ​ጎ​ችህ፥ በአ​ህ​ያ​ህም ታደ​ር​ገ​ዋ​ለህ፤ ሰባት ቀን ከእ​ናቱ ጋር ይቀ​መጥ፤ በስ​ም​ን​ተ​ኛ​ውም ቀን ለእኔ ትሰ​ጠ​ዋ​ለህ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

30 ከቀንድ ከብትህና ከበጎችህም እንዲሁ አድርግ፤ ለሰባት ቀን ከእናቶቻቸው ጋራ ይቈዩ፤ በስምንተኛው ቀን ግን ለእኔ ሰጠኝ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

30 ቅዱስ ወገን ትሆኑልኛላችሁ፤ ስለዚህ በሜዳ አውሬ የገደለውን ሥጋ አትብሉ፤ ለውሻ ጣሉት።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

30 ከቀንድ ከብቶችህ፥ ከበጎችህም በኲር ሆነው የሚወለዱትን ለእኔ አቅርብ፤ ይኸውም በኲር ሆኖ የተወለደ ወንድ ሁሉ ለሰባት ቀን ከእናቱ ጋር ይቈይ፤ በስምንተኛው ቀን ለእኔ ታቀርበዋለህ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

30 እንዲህም በበሬዎችህና በበጎችህ ታደርገዋለህ፤ ሰባት ቀን ከእናቱ ጋር ይቀመጥ፥ በስምንተኛውም ቀን ለእኔ ትሰጠዋለህ።

Ver Capítulo Copiar




ዘፀአት 22:30
14 Referencias Cruzadas  

“ላም፥ ወይም በግ፥ ወይም ፍየል ሲወ​ለድ ሰባት ቀን ከእ​ናቱ ጋር ይቀ​መጥ፤ በስ​ም​ን​ተ​ኛ​ውም ቀን፥ ከዚ​ያም በላይ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የእ​ሳት ቍር​ባን የሠ​መረ ይሆ​ናል።


“ላም​ህና በግህ የወ​ለ​ዱ​ትን ተባት የሆ​ነ​ውን በኵ​ራት ለአ​ም​ላ​ክህ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትቀ​ድ​ሳ​ለህ፤ በበ​ሬህ በኵ​ራት አት​ሥ​ራ​በት፤ የበ​ግ​ህ​ንም በኵ​ራት አት​ሸ​ልት።


እንደ ግዳ​ጅዋ ወራት ትረ​ክ​ሳ​ለች። በስ​ም​ን​ተ​ኛ​ውም ቀን ልጁ ከሥ​ጋው ሸለ​ፈት ይገ​ረዝ።


ማሕ​ፀ​ንን የሚ​ከ​ፍ​ተ​ውን ሁሉ ለይ፤ ከመ​ን​ጋ​ህና ከከ​ብ​ት​ህም መጀ​መ​ሪያ የሚ​ወ​ለ​ደው ተባት ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይሆ​ናል።


ሕፃ​ኑ​ንም በስ​ም​ን​ተ​ኛው ቀን ትገ​ር​ዙ​ታ​ላ​ችሁ፤ በቤት የተ​ወ​ለደ ወይም ከዘ​ራ​ችሁ ያይ​ደለ፥ በብ​ርም ከእ​ን​ግዳ ሰው የተ​ገዛ ወንድ ሁሉ በት​ው​ል​ዳ​ችሁ ይገ​ረዝ።


“የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች እን​ዲህ ብለህ ተና​ገ​ራ​ቸው፦ የበሬ ወይም የበግ ወይም የፍ​የል ስብ ከቶ አት​ብሉ።


የሞ​ተ​ውን ስብ፥ አውሬ የሰ​በ​ረ​ው​ንም ስብ ለሌላ ተግ​ባር አድ​ር​ጉት፤ እና​ንተ ግን አት​ብ​ሉት፤


በመ​ኖ​ሪ​ያ​ዎ​ቻ​ችሁ ሁሉ የወፍ ወይም የእ​ን​ስሳ ደም ቢሆን አት​ብሉ።


እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ችሁ ነኝና፤ ሰው​ነ​ታ​ች​ሁን ቀድሱ፤ ቅዱ​ሳ​ንም ሁኑ፤ እኔ አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቅዱስ ነኝና፤


በም​ድ​ርም ላይ በሚ​ሳብ ተን​ቀ​ሳ​ቃሽ ሁሉ ሰው​ነ​ታ​ች​ሁን አታ​ሳ​ድፉ። እኔ አም​ላ​ካ​ችሁ እሆን ዘንድ ከግ​ብፅ ምድር ያወ​ጣ​ኋ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝ፤ እን​ግ​ዲህ እኔ ቅዱስ ነኝና እና​ን​ተም ቅዱ​ሳን ሁኑ።


የሞ​ተ​ውን ወይም አውሬ የሰ​በ​ረ​ውን የሚ​በላ ሰው ሁሉ፥ የሀ​ገር ልጅ ወይም እን​ግዳ ቢሆን፥ ልብ​ሱን ያጥ​ባል፤ በው​ኃም ይታ​ጠ​ባል፤ እስከ ማታም ርኩስ ይሆ​ናል፤ ከዚ​ያም በኋላ ንጹሕ ይሆ​ናል።


በእ​ር​ሱም እን​ዳ​ይ​ረ​ክስ፥ የሞ​ተ​ውን፥ አው​ሬም የሰ​በ​ረ​ውን አይ​ብላ፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝና።


የበ​ከ​ተ​ዉን ሁሉ አት​ብሉ፤ ይበ​ላው ዘንድ በሀ​ገ​ርህ ደጅ ለተ​ቀ​መጠ መጻ​ተኛ ወይም ለባ​ዕድ ስጠው፤ አንተ ለአ​ም​ላ​ካህ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ቀ​ደሰ ሕዝብ ነህና፥ የፍ​የ​ሉን ጠቦት በእ​ናቱ ወተት አት​ቀ​ቅል።


እኔም፥ “የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሆይ! ይህ አግ​ባብ አይ​ደ​ለም፤ እነሆ ሰው​ነቴ አል​ረ​ከ​ሰ​ችም፤ ከታ​ና​ሽ​ነቴ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ጥን​ብና አውሬ የሰ​በ​ረ​ውን ከቶ አል​በ​ላ​ሁም፤ ርኵ​ስም ሥጋ በአፌ ውስጥ አል​ገ​ባም” አልሁ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios