Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘፀአት 22:29 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

29 የአ​ው​ድ​ማ​ህ​ንና የወ​ይ​ን​ህ​ንም መጀ​መ​ሪያ ለማ​ቅ​ረብ አት​ዘ​ግይ፤ የል​ጆ​ች​ህ​ንም በኵር ትሰ​ጠ​ኛ​ለህ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

29 “የእህልህን ወይም የወይን ጠጅህን በኵራት ለእኔ ከማቅረብ ወደ ኋላ አትበል። “የወንድ ልጆችህን በኵር ለእኔ ስጠኝ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

29 ከበሬህና ከበግህም እንዲሁ አድግር፤ ሰባት ቀን ከእናቱ ጋር ይቀመጥ፥ በስምንተኛውም ቀን ለእኔ ትሰጠዋለህ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

29 “የእህልህን፥ የወይን ጠጅህንና የወይራ ዘይትህን በኲራት ለእኔ አቅርብ፤ “በኲር ሆነው የተወለዱትን ወንዶች ልጆችህን ለእኔ አቅርብ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

29 ነዶህንም የወይንህንም ጭማቂ ለማቅረብ አትዘግይ፤ የልጆችህንም በኵር ትሰጠኛለህ።

Ver Capítulo Copiar




ዘፀአት 22:29
19 Referencias Cruzadas  

በፊቴ ባዶ እጅ​ህን አት​ታይ። በእ​ር​ሻም የም​ት​ዘ​ራ​ትን የፍ​ሬ​ህን በኵ​ራት የመ​ከር በዓል፥ ዓመ​ቱም ሲያ​ልቅ ፍሬ​ህን ከእ​ርሻ ባከ​ማ​ቸህ ጊዜ የመ​ክ​ተ​ቻ​ውን በዓል ጠብቅ።


“በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ዘንድ ከሰ​ውም፥ ከእ​ን​ስ​ሳም መጀ​መ​ሪያ የተ​ወ​ለ​ደ​ውን ማሕ​ፀ​ንን የሚ​ከ​ፍት በኵር ሁሉ ለእኔ ለይ​ልኝ፤ የእኔ ነው።”


ለፍጥረቱ የበኵራት ዐይነት እንድንሆን በእውነት ቃል አስቦ ወለደን።


የም​ድ​ር​ህን ፍሬ በኵ​ራት ወደ አም​ላ​ክህ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት አምጣ። ጠቦ​ትን በእ​ናቱ ወተት አት​ቀ​ቅል።


ነገር ግን የሚ​ተ​ክዝ ዓለም ብቻ አይ​ደ​ለም፤ የመ​ን​ፈስ ቅዱ​ስን ፈለማ የተ​ቀ​በ​ል​ነው እናም ደግሞ እና​ዝ​ና​ለን እንጂ፤ የነ​ፍ​ሳ​ች​ንን ድኅ​ነት እና​ገኝ ዘንድ የል​ጅ​ነ​ትን ክብር ተስፋ እና​ደ​ር​ጋ​ለ​ንና፤ በእ​ም​ነ​ትም ድነ​ና​ልና።


ነገር ግን አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ፥ ይህም ሁሉ ይጨመርላችኋል።


የዛፍ ፍሬና የወይን ፍሬ ከተለቀሙ በኋላ እንደ ቀረው ቃርሚያ ሆኛለሁና ወዮልኝ! መብል የሚሆን ዘለላ፥ ነፍሴም የተመኘችው በመጀመሪያ የበሰለው በለስ የለም።


መጀ​መ​ሪያ የሚ​ወ​ለድ ተባት ሁሉ የእኔ ነው፤ የላ​ም​ህም በኵር፥ የበ​ግ​ህም በኵር፥ የበ​ሬ​ህም በኵር ሁሉ የእኔ ነው።


ማሕ​ፀ​ንን የሚ​ከ​ፍ​ተ​ውን ሁሉ ለይ፤ ከመ​ን​ጋ​ህና ከከ​ብ​ት​ህም መጀ​መ​ሪያ የሚ​ወ​ለ​ደው ተባት ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይሆ​ናል።


“በቅ​ዱሱ ተራ​ራዬ፥ ከፍ ባለው በእ​ስ​ራ​ኤል ተራራ ላይ፥ ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ በዚያ የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ሁሉ ሁላ​ቸው ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይገ​ዙ​ል​ኛል፤ በዚ​ያም እቀ​በ​ላ​ች​ኋ​ለሁ፤ በዚ​ያም ቀዳ​ም​ያ​ታ​ች​ሁን፥ በኵ​ራ​ታ​ች​ሁ​ንም፥ የቀ​ደ​ሳ​ች​ሁ​ት​ንም ነገር ሁሉ እጐ​በ​ኛ​ለሁ።


ይህ​ንም ነገር እን​ዳ​ዘዘ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች የእ​ህ​ሉ​ንና የወ​ይ​ኑን፥ የዘ​ይ​ቱ​ንና የማ​ሩ​ንም፥ የእ​ር​ሻ​ው​ንም ፍሬ መጀ​መ​ሪያ ሁሉ ሰጡ፤ የሁ​ሉ​ንም ዐሥ​ራት አብ​ዝ​ተው አቀ​ረቡ።


አንድ ሰውም ከቤ​ት​ሣ​ሪሳ ከእ​ህሉ ቀዳ​ም​ያት፥ ሃያ የገ​ብስ እን​ጀራ፥ የእ​ህ​ልም እሸት በአ​ቁ​ማዳ ይዞ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰው መጣ፤ ኤል​ሳ​ዕም አገ​ል​ጋ​ዩን፥ “ይበሉ ዘንድ ለሕ​ዝቡ ስጣ​ቸው” አለ።


የቂ​ጣ​ውን በዓል ጠብቁ፤ በአ​ዲስ ወር ከግ​ብፅ ምድር ወጥ​ታ​ች​ኋ​ልና በዚህ ወር እን​ዳ​ዘ​ዝ​ኋ​ችሁ ሰባት ቀን ቂጣ ትበ​ላ​ላ​ችሁ።


የአ​ህ​ያ​ው​ንም በኵር በበግ ትዋ​ጀ​ዋ​ለህ፤ ባት​ዋ​ጀው ግን ዋጋ​ውን ትሰ​ጣ​ለህ። የል​ጆ​ች​ህ​ንም በኵር ሁሉ ትዋ​ጃ​ለህ። በፊ​ቴም ባዶ እጅ​ህን አት​ታይ።


ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ያ​መ​ጡት በም​ድ​ራ​ቸው ያለው የፍሬ መጀ​መ​ሪያ ሁሉ ለአ​ንተ ይሆ​ናል፤ በቤ​ትህ ውስጥ ንጹሕ የሆነ ሁሉ ይብ​ላው፤


“ላም፥ ወይም በግ፥ ወይም ፍየል ሲወ​ለድ ሰባት ቀን ከእ​ናቱ ጋር ይቀ​መጥ፤ በስ​ም​ን​ተ​ኛ​ውም ቀን፥ ከዚ​ያም በላይ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የእ​ሳት ቍር​ባን የሠ​መረ ይሆ​ናል።


“ላም​ህና በግህ የወ​ለ​ዱ​ትን ተባት የሆ​ነ​ውን በኵ​ራት ለአ​ም​ላ​ክህ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትቀ​ድ​ሳ​ለህ፤ በበ​ሬህ በኵ​ራት አት​ሥ​ራ​በት፤ የበ​ግ​ህ​ንም በኵ​ራት አት​ሸ​ልት።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios