Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘኍል 18:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 ከሰው እስከ እን​ስሳ ቢሆን፥ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከሚ​ያ​ቀ​ር​ቡት ሥጋ ሁሉ፥ መጀ​መ​ሪያ የሚ​ወ​ለድ ሁሉ ለአ​ንተ ይሆ​ናል፤ ነገር ግን የሰ​ውን በኵ​ራት ፈጽሞ ትቤ​ዠ​ዋ​ለህ፤ ያል​ነ​ጹ​ት​ንም እን​ስ​ሳት በኵ​ራት ትቤ​ዣ​ለህ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 ማሕፀን የሚከፍትና ለእግዚአብሔር የተሰጠ ሰውም ሆነ እንስሳ የአንተ ነው፤ ነገር ግን ማንኛውም በኵር ሆኖ የተወለደውን ወንድ ልጅና ንጹሕ ካልሆነ እንስሳ በኵር ሆኖ የተወለደውን ተባዕት ሁሉ ዋጀው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 ለጌታ ከሚያቀርቡት ከሰው ወይም ከእንስሳ ማናቸውም ማኅፀን የሚከፍት ሥጋ ለባሽ የሆነ ሁሉ ለአንተ ይሆናል፤ ነገር ግን የሰውን በኵራት ፈጽሞ ትዋጀዋለህ፥ ያልነጻውንም እንስሳ በኵራት ትዋጀዋለህ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 “እስራኤላውያን ለእኔ የሚያቀርቡት የሰውም ሆነ የእንስሳ በኲር ሁሉ የእናንተ ይሆናል፤ ነገር ግን የሰውን የበኲር ልጅ ለመዋጀት ዋጋውን በጥሬ ገንዘብ መቀበል አለባችሁ፤ እንዲሁም ንጹሕ ስላልሆነው የእንስሳ በኲር ምትክ ዋጋውን በጥሬ ገንዘብ መቀበል ትችላላችሁ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 ለእግዚአብሔር ከሚያቀርቡት ሥጋ ሁሉ ማኅፀን የሚከፍት ሁሉ ለአንተ ይሆናል፤ ነገር ግን የሰውን በኵራት ፈጽሞ ትቤዠዋለህ፥ ያልነጻውንም እንስሳ በኵራት ትቤዠዋለህ።

Ver Capítulo Copiar




ዘኍል 18:15
12 Referencias Cruzadas  

የአ​ህ​ያ​ው​ንም በኵር በበግ ትዋ​ጀ​ዋ​ለህ፤ ባት​ዋ​ጀው ግን ዋጋ​ውን ትሰ​ጣ​ለህ። የል​ጆ​ች​ህ​ንም በኵር ሁሉ ትዋ​ጃ​ለህ። በፊ​ቴም ባዶ እጅ​ህን አት​ታይ።


“በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ዘንድ ከሰ​ውም፥ ከእ​ን​ስ​ሳም መጀ​መ​ሪያ የተ​ወ​ለ​ደ​ውን ማሕ​ፀ​ንን የሚ​ከ​ፍት በኵር ሁሉ ለእኔ ለይ​ልኝ፤ የእኔ ነው።”


በሌ​ዋ​ው​ያን ላይ ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች በኵር ስለ ተረ​ፉት ስለ ሁለት መቶ ሰባ ሦስት ቤዛ፥


በኵር ሁሉ ለእኔ ነውና፤ በግ​ብፅ ምድር በኵ​ርን ሁሉ በመ​ታሁ ቀን ከእ​ስ​ራ​ኤል ዘንድ በኵ​ርን ሁሉ፥ ሰው​ንና እን​ስ​ሳን፥ ለእኔ ለይ​ች​አ​ለሁ፤ ለእኔ ይሁኑ። እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝና።”


የአ​ው​ድ​ማ​ህ​ንና የወ​ይ​ን​ህ​ንም መጀ​መ​ሪያ ለማ​ቅ​ረብ አት​ዘ​ግይ፤ የል​ጆ​ች​ህ​ንም በኵር ትሰ​ጠ​ኛ​ለህ።


ፈር​ዖ​ንም እኛን ለመ​ል​ቀቅ እንቢ ባለ ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከሰው በኵር ጀምሮ እስከ እን​ስሳ በኵር ድረስ በግ​ብፅ ምድር ያለ​ውን በኵር ሁሉ ገደለ፤ ስለ​ዚህ ወንድ ሆኖ ማሕ​ፀ​ንን የከ​ፈ​ተ​ውን ሁሉ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እሠ​ዋ​ለሁ፤ ነገር ግን የል​ጆ​ችን በኵር ሁሉ እዋ​ጃ​ለሁ።’


አንድ ወር የሆ​ነው ልጅ ዋጋው በቤተ መቅ​ደስ ሚዛን አም​ስት ሰቅል ነው። ይኸ​ውም ሃያ አቦሊ ነው።


“ላም​ህና በግህ የወ​ለ​ዱ​ትን ተባት የሆ​ነ​ውን በኵ​ራት ለአ​ም​ላ​ክህ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትቀ​ድ​ሳ​ለህ፤ በበ​ሬህ በኵ​ራት አት​ሥ​ራ​በት፤ የበ​ግ​ህ​ንም በኵ​ራት አት​ሸ​ልት።


እያ​ን​ዳ​ንዱ ሰው ከሚ​ያ​መ​ጣው ካህ​ናቱ ለራ​ሳ​ቸው ይው​ሰዱ፤ በመ​ቅ​ደ​ስም ውስጥ የተ​ና​ዱ​ትን ይጠ​ግ​ኑ​በት” አላ​ቸው።


የእ​ህ​ላ​ች​ን​ንም ቀዳ​ም​ያት፥ የዛ​ፉን ሁሉ ፍሬ፥ የወ​ይ​ኑ​ንና የዘ​ይ​ቱ​ንም ፍሬ ወደ ካህ​ናቱ ወደ አም​ላ​ካ​ችን ቤት ጓዳ​ዎች እና​መጣ ዘንድ፥ ሌዋ​ው​ያ​ኑም ከከ​ተ​ሞ​ቻ​ችን እርሻ ሁሉ ዐሥ​ራት ይቀ​በ​ላ​ሉና የመ​ሬ​ታ​ች​ንን ዐሥ​ራት ወደ ሌዋ​ው​ያን እና​መጣ ዘንድ ማልን።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios