Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -


ዘኍል 3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)


አራቱ የአ​ሮን ወን​ዶች ልጆች

1 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሲና ተራራ ላይ ሙሴን በተ​ና​ገ​ረ​በት ቀን የአ​ሮ​ንና የሙሴ ትው​ልድ ይህ ነበረ።

2 የአ​ሮን ልጆች ስም ይህ ነው፤ በኵሩ ናዳብ፥ አብ​ዩድ፥ አል​ዓ​ዛር፥ ኢታ​ምር።

3 በክ​ህ​ነት ያገ​ለ​ግሉ ዘንድ የተ​ቀ​ቡና እጆ​ቻ​ቸ​ውን የተ​ቀ​ደሱ የአ​ሮን ልጆች ስም ይህ ነው።

4 ናዳ​ብና አብ​ዩድ በሲና ምድረ በዳ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ከሌላ እሳት ጭረው አም​ጥ​ተ​ዋ​ልና በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ሞቱ፤ ልጆ​ችም አል​ነ​በ​ሩ​አ​ቸ​ውም። አል​ዓ​ዛ​ርና ኢታ​ምር ከአ​ባ​ታ​ቸው ከአ​ሮን ጋር በክ​ህ​ነት ያገ​ለ​ግሉ ነበር።


የሌ​ዋ​ው​ያን ተግ​ባር

5 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፦

6 “የሌ​ዊን ነገድ አቅ​ር​በህ ያገ​ለ​ግ​ሉት ዘንድ በካ​ህኑ በአ​ሮን ፊት አቁ​ማ​ቸው።

7 የድ​ን​ኳ​ኑን ሥራ ይሠሩ ዘንድ ሕጉ​ንና የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ሕግ በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ፊት ይጠ​ብቁ።

8 እንደ ድን​ኳኑ ሥራ​ዎች ሁሉ የም​ስ​ክ​ሩን ድን​ኳን ዕቃና የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ሕግ ይጠ​ብቁ።

9 ሌዋ​ው​ያ​ን​ንም ወደ ወን​ድ​ምህ ወደ አሮ​ንና ወደ ልጆቹ ወደ ካህ​ናቱ ታገ​ባ​ቸ​ዋ​ለህ። ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ተለ​ይ​ተው ለእኔ ሀብት ሆነው ተሰ​ጥ​ተ​ዋ​ልና።

10 አሮ​ን​ንና ልጆ​ቹን በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ፊት አቁ​ማ​ቸው፤ ክህ​ነ​ታ​ቸ​ው​ንም፥ በመ​ሠ​ዊ​ያ​ውና በመ​ጋ​ረ​ጃው ውስጥ ያለ​ው​ንም ሁሉ ይጠ​ብቁ፤ ከሌላ ወገን የዳ​ሰሰ ቢኖር ይገ​ደል።”

11 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፦

12 “እነሆ፥ እኔ በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ዘንድ መጀ​መ​ሪያ በሚ​ወ​ለ​ደው በበ​ኵር ሁሉ ፋንታ ሌዋ​ው​ያ​ንን ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች መካ​ከል ለይች ወስ​ጃ​ለሁ፤ በእ​ነ​ርሱ ፋንታ ሌዋ​ው​ያን ለእኔ ይሁኑ፤

13 በኵር ሁሉ ለእኔ ነውና፤ በግ​ብፅ ምድር በኵ​ርን ሁሉ በመ​ታሁ ቀን ከእ​ስ​ራ​ኤል ዘንድ በኵ​ርን ሁሉ፥ ሰው​ንና እን​ስ​ሳን፥ ለእኔ ለይ​ች​አ​ለሁ፤ ለእኔ ይሁኑ። እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝና።”


የሌ​ዋ​ው​ያን ቈጠራ

14 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን በሲና ምድረ በዳ እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፦

15 “የሌ​ዊን ልጆች በየ​አ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ቤቶች፥ በየ​ወ​ገ​ና​ቸ​ውም ቍጠር፤ ወን​ዱን ሁሉ ከአ​ንድ ወር ጀምሮ ከዚ​ያም በላይ ያለ​ውን ቍጠ​ራ​ቸው።”

16 ሙሴና አሮ​ንም እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ አዘ​ዛ​ቸው ቈጠ​ሩ​አ​ቸው።

17 የሌዊ ልጆች በየ​ስ​ማ​ቸው እነ​ዚህ ናቸው፤ ጌድ​ሶን፥ ቀዓት፥ ሜራሪ።

18 የጌ​ድ​ሶ​ንም ልጆች ስሞች በየ​ወ​ገ​ና​ቸው እነ​ዚህ ናቸው፤ ሎቤን፥ ሰሜይ።

19 የቀ​ዓ​ትም ልጆች በየ​ወ​ገ​ና​ቸው እን​በ​ረም፥ ይሳ​ዓር፥ ኬብ​ሮን፥ አዛ​ሄል።

20 የሜ​ራ​ሪም ልጆች በየ​ወ​ገ​ና​ቸው፤ ሞሐሊ፥ ሙሲ። የሌ​ዋ​ው​ያን ወገ​ኖች በየ​አ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ቤቶች እነ​ዚህ ናቸው።

21 ለጌ​ድ​ሶን የሎ​ቤን ወገን፥ የሰ​ሜ​ይም ወገን ነበ​ሩት፤ የጌ​ድ​ሶን ወገ​ኖች እነ​ዚህ ናቸው።

22 ከእ​ነ​ርሱ የተ​ቈ​ጠ​ሩት የወ​ን​ዶች ሁሉ ቍጥር ከአ​ንድ ወር ጀምሮ ከዚ​ያም በላይ የተ​ቈ​ጠ​ሩት ሰባት ሺህ አም​ስት መቶ ነበሩ።

23 የጌ​ድ​ሶን ልጆች ከድ​ን​ኳን በኋላ በባ​ሕር በኩል ይሰ​ፍ​ራሉ።

24 የጌ​ድ​ሶን አባ​ቶች ቤት አለቃ የዳ​ሔል ልጅ ኤሊ​ሳፍ ይሆ​ናል።

25 የጌ​ድ​ሶን ልጆች በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን የሚ​ጠ​ብ​ቁት ማደ​ሪ​ያ​ውና ድን​ኳኑ፥ መደ​ረ​ቢ​ያ​ውም፥ የም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ደጃፍ መጋ​ረጃ፥

26 የአ​ደ​ባ​ባዩ መጋ​ረጃ፥ በድ​ን​ኳኑ አደ​ባ​ባይ በር ያለው መጋ​ረ​ጃና የቀ​ረ​ውም ሥራዋ ሁሉ ይሆ​ናል።

27 ለቀ​ዓ​ትም የእ​ን​በ​ረም ወገን፥ የይ​ስ​ዓር ወገን፥ የኬ​ብ​ሮ​ንም ወገን፥ የአ​ዛ​ሔ​ልም ወገን ነበሩ፤ የቀ​ዓት ወገ​ኖች እነ​ዚህ ናቸው።

28 ወን​ዶች ሁሉ እንደ ቍጥ​ራ​ቸው ከአ​ንድ ወር ጀምሮ ከዚ​ያም በላይ ስም​ንት ሺህ ስድ​ስት መቶ ነበሩ፤ መቅ​ደ​ሱ​ንም ይጠ​ብቁ ነበር።

29 የቀ​ዓት ልጆች ወገ​ኖች በድ​ን​ኳኑ አጠ​ገብ በአ​ዜብ በኩል ይሰ​ፍ​ራሉ።

30 የቀ​ዓት ወገ​ኖች አባ​ቶች ቤት አለቃ የአ​ዛ​ሔል ልጅ ኤሊ​ሳፋ ይሆ​ናል።

31 ታቦ​ቱ​ንም፥ ገበ​ታ​ው​ንም፥ መቅ​ረ​ዙ​ንም፥ መሠ​ዊ​ያ​ዎ​ቹ​ንም፥ የሚ​ያ​ገ​ለ​ግ​ሉ​በ​ት​ንም የመ​ቅ​ደ​ሱን ዕቃ፥ መጋ​ረ​ጃ​ው​ንም፥ ማገ​ል​ገ​ያ​ው​ንም ሁሉ ይጠ​ብ​ቃሉ።

32 የሌ​ዋ​ው​ያ​ንም አለ​ቆች አለቃ የተ​ቀ​ደሱ ነገ​ሮ​ችን ይጠ​ብቅ ዘንድ የተ​ሾ​መው የካ​ህኑ የአ​ሮን ልጅ አል​ዓ​ዛር ነው።

33 ለሜ​ራሪ የሞ​ሖሊ ወገን የሙሲ ወገን ነበሩ፤ የሜ​ራሪ ወገ​ኖች እነ​ዚህ ናቸው።

34 ከእ​ነ​ር​ሱም ወን​ዶች ሁሉ እንደ ቍጥ​ራ​ቸው ከአ​ንድ ወር ጀምሮ ከዚ​ያም በላይ የተ​ቈ​ጠ​ሩት ስድ​ስት ሽህ አምሳ ነበሩ።

35 የሜ​ራ​ሪም ወገ​ኖች አባ​ቶች ቤት አለቃ የአ​ቢ​ኪያ ልጅ ሱራ​ሔል ነበረ፤ በድ​ን​ኳኑ አጠ​ገብ በሰ​ሜን በኩል ይሰ​ፍ​ራሉ።

36 የሜ​ራ​ሪም ልጆች የሚ​ጠ​ብ​ቁት የድ​ን​ኳኑ ምሰ​ሶ​ዎች፥ ኩላ​ቦች፥ መወ​ር​ወ​ሪ​ያ​ዎ​ችም፥ ተራ​ዳ​ዎ​ችም፥ እግ​ሮ​ቹም፥

37 ዕቃ​ውም ሁሉ፥ ማገ​ል​ገ​ያ​ውም ሁሉ፥ በዙ​ሪ​ያ​ውም የሚ​ቆሙ የአ​ደ​ባ​ባይ ምሰ​ሶ​ዎች፥ እግ​ሮ​ቹም፥ ካስ​ማ​ዎ​ቹም፥ አው​ታ​ሮ​ቹም ይሆ​ናሉ።

38 በም​ሥ​ራቅ በኩል በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ፊት የሚ​ሰ​ፍ​ሩት ሙሴና አሮን ልጆ​ቹም ይሆ​ናሉ፥ እንደ እስ​ራ​ኤል ልጆች ሕግም የመ​ቅ​ደ​ሱን ሕግ ይጠ​ብ​ቃሉ፥ ከሌላ ወገን የዳ​ሰሰ ቢኖር ይገ​ደል።

39 በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትእ​ዛዝ ሙሴና አሮን የቈ​ጠ​ሩ​አ​ቸው፥ ከሌ​ዋ​ው​ያን ወን​ዶች ሁሉ ከአ​ንድ ወር ጀምሮ ከዚ​ያም በላይ በየ​ወ​ገ​ና​ቸው የተ​ቈ​ጠ​ሩት ሁሉ ሃያ ሁለት ሺህ ነበሩ።


የሌ​ዋ​ው​ያን በእ​ስ​ራ​ኤል የበ​ኵር ልጆች መተ​ካት

40 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን፥ “የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ወን​ዱን በኵር ሁሉ ከአ​ንድ ወር ጀምሮ ከዚ​ያም በላይ ያሉ​ትን ቍጠር፤ ቍጥ​ራ​ቸ​ው​ንም በየ​ስ​ማ​ቸው ውሰድ፤

41 ሌዋ​ው​ያ​ን​ንም በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች በኵር ሁሉ ፋንታ፥ የሌ​ዋ​ው​ያ​ን​ንም እን​ስ​ሶች በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች እን​ስ​ሶች በኵር ሁሉ ፋንታ ለእኔ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አድ​ር​ጋ​ቸው” አለው።

42 ሙሴም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዳ​ዘ​ዘው የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች በኵር ሁሉ ቈጠረ።

43 ከእ​ነ​ር​ሱም የተ​ቈ​ጠሩ ወን​ዶች በኵ​ሮች ሁሉ በየ​ስ​ማ​ቸው ከአ​ንድ ወር ጀምሮ ከዚ​ያም በላይ ሃያ ሁለት ሺህ ሁለት መቶ ሰባ ሦስት ነበሩ።

44 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፦

45 “ሌዋ​ው​ያ​ንን በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች በኵር ሁሉ ፋንታ፥ የሌ​ዋ​ው​ያ​ን​ንም እን​ስ​ሶች በእ​ን​ስ​ሶ​ቻ​ቸው ፋንታ ውሰድ፤ ሌዋ​ው​ያ​ንም ለእኔ ይሁኑ፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝና።

46 በሌ​ዋ​ው​ያን ላይ ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች በኵር ስለ ተረ​ፉት ስለ ሁለት መቶ ሰባ ሦስት ቤዛ፥

47 በየ​ራሱ አም​ስት ዲድ​ር​ክም ውሰድ፤ እንደ መቅ​ደሱ ዲድ​ር​ክም ብዛት ትወ​ስ​ዳ​ለህ፤ ዲድ​ር​ክም ሃያ አቦሊ ነው።

48 ስለ ተረ​ፉ​ትም የመ​ቤ​ዣ​ውን ገን​ዘብ ለአ​ሮ​ንና ለል​ጆቹ ትሰ​ጣ​ቸ​ዋ​ለህ።”

49 ሙሴም በሌ​ዋ​ው​ያን ከተ​ቤ​ዡት በላይ ከተ​ረ​ፉት ዘንድ የመ​ቤ​ዣ​ውን ገን​ዘብ ወሰደ።

50 ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች በኵ​ሮች ገን​ዘ​ቡን ሺህ ሦስት መቶ ስድሳ አም​ስት ዲድ​ር​ክም እንደ መቅ​ደሱ ዲድ​ር​ክም ሚዛን ወሰደ።

51 እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሙሴን እን​ዳ​ዘ​ዘው ሙሴ የመ​ቤ​ዣ​ውን ገን​ዘብ ለአ​ሮ​ንና ለል​ጆቹ ሰጠ።

Síguenos en:



Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos