ልጄ ሲሞት አላየውም ብላ ቀስት ተወርውሮ የሚደርስበትን ያህል ርቃ በአንጻሩ እየተመለከተች፥ ፊት ለፊት ተቀመጠች፤ ቃልዋንም አሰምታ አለቀሰች።
አሞጽ 8:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዓመት በዓላችሁንም ወደ ልቅሶ፥ ዝማሬያችሁንም ወደ ዋይታ እለውጣለሁ፤ ማቅንም በወገብ ሁሉ ላይ፥ ቡሃነትንም በራስ ሁሉ ላይ ላይ አመጣለሁ፤ እንደ ወዳጅ ልቅሶ አደርጋችኋለሁ፤ ከእርሱም ጋር ያሉት እንደ መከራ ቀን ይሆናሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዓመት በዓላችሁን ወደ ልቅሶ፣ ዝማሬአችሁንም ሁሉ ወደ ዋይታ እለውጣለሁ፤ ሁላችሁም ማቅ እንድትለብሱ፣ ጠጕራችሁንም እንድትላጩ አደርጋለሁ፤ ያን ጊዜ ለአንድያ ልጅ ሞት እንደሚለቀስበት፣ ፍጻሜውንም እንደ መራራ ቀን አደርገዋለሁ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዓመት በዓላችሁንም ወደ ልቅሶ፥ ዝማሬአችሁንም ወደ ዋይታ እለውጣለሁ፤ ማቅንም በወገብ ሁሉ፥ ጸጉር መላጨትንም በሁሉ ላይ አመጣለሁ፤ እንደ አንድያ ልጅም ልቅሶ፥ ፍጻሜውንም እንደ መራራ ቀን አደርገዋለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የዓመት በዓል ደስታችሁን ወደ ሐዘን፥ ዘፈናችሁንም ወደ ለቅሶ እለውጠዋለሁ፤ አንድ ብቻ የሆነ ልጃቸው ሞቶባቸው እንደሚያለቅሱ ወላጆች ጠጒራችሁን ተላጭታችሁ ማቅ እንድትለብሱ አደርጋለሁ፤ የዚያ ቀን ፍጻሜ የመረረ ይሆናል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዓመት በዓላችሁንም ወደ ልቅሶ፥ ዝማሬአችሁንም ወደ ዋይታ እለውጣለሁ፥ ማቅንም በወገብ ሁሉ፥ ራስ መንጨትንም በሁሉ ላይ አመጣለሁ፥ እንደ አንድያ ልጅም ልቅሶ፥ ፍጻሜውንም እንደ መራራ ቀን አደርገዋለሁ። |
ልጄ ሲሞት አላየውም ብላ ቀስት ተወርውሮ የሚደርስበትን ያህል ርቃ በአንጻሩ እየተመለከተች፥ ፊት ለፊት ተቀመጠች፤ ቃልዋንም አሰምታ አለቀሰች።
እንዲህም ይሆናል፤ ስለ ሥራሽ ክፋት በሽቱ ፋንታ ትቢያ ይሁንብሽ፤ በወርቅ መታጠቂያሽም ፋንታ ገመድ ታጠቂ፤ በራስ ወርቅ ቀጸላሽም ፋንታ ቡሃነት ይውጣብሽ፤ በሐር መጐናጸፊያሽ ፋንታ ማቅ ልበሽ።
ክፋትሽ ይገሥጽሻል፤ ክዳትሽም ይዘልፍሻል፤ እኔን መተውሽም ክፉና መራራ ነገር መሆኑን ታውቂያለሽ፤ ትረጂማለሽ” ይላል አምላክሽ እግዚአብሔር፤ “መፈራቴም በአንቺ ዘንድ የለም፤ ይህም ደስ አላሰኘኝም” ይላል አምላክሽ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
በሰው ሁሉ ራስ ላይ ቡሃነት አለ፤ ጽሕማቸውን ሁሉ ይላጫሉ፤ እጆች ሁሉ ይንቀጠቀጣሉ፤ ሁሉም በወገባቸው ማቅን ይታጠቃሉ።
የሕዝቤ ልጅ ሆይ፥ ማቅ ልበሺ፤ በራስሺም ላይ አመድ ነስንሺ፥ አጥፊ በላያችን በድንገት ይመጣብናልና ለተወዳጅ ልጅ እንደሚደረግ ልቅሶ መራራ ልቅሶ አልቅሺ።
ማቅም ትታጠቃላችሁ፤ ድንጋጤም ይሸፍናችኋል፤ በፊትም ሁሉ ላይ ሐፍረት ይሆናል፤ በራሳችሁም ሁሉ ላይ ቡሃነት ይሆናል።
“አንተ የሰው ልጅ ሆይ! ጌታ እግዚአብሔር ለእስራኤል ምድር እንዲህ ይላል፦ ፍጻሜ በእስራኤል ምድር ላይ መጣ፤ በምድሪቱ በአራቱም ማዕዘን ፍጻሜ መጣ።
እኔን ረስታ ወዳጆችዋን እየተከተለች፥ በጕትቾችዋና በጌጥዋም እያጌጠች ለበኣሊም የሠዋችበትን ወራት እበቀልባታለሁ፥” ይላል እግዚአብሔር።
ያንጊዜም በመቅደሶቻቸው ዋይ ዋይ ይላሉ” ይላል ጌታ እግዚአብሔር፤ በየስፍራው የሚወድቀው ሬሳ ይበዛልና፤ እነርሱም ይጠፋሉና።
በዳዊትም ቤት ላይ፥ በኢየሩሳሌምም በሚኖሩት ላይ፥ የሞገስንና የልመናን መንፈስ አፈስሳለሁ፣ ወደ እርሱም ወደ ወጉት ይመለከታሉ፣ ሰውም ለአንድያ ልጁ እንደሚያለቅስ ያለቅሱለታል፥ ሰውም ለበኵር ልጁ እንደሚያዝን በመራራ ኅዘን ያዝኑለታል።
አንተም፥ ወንድ ልጅህና ሴት ልጅህ፥ ወንድ ባሪያህና ሴት ባሪያህ፥ በሀገርህም ውስጥ ያለ ሌዋዊና መጻተኛ፥ ድሃ-አደግና መበለትም በበዓልህ ደስ ይበላችሁ።