Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኢዮብ 3:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 ጨለ​ማና የሞት ጥላ ያግ​ኙ​አት፤ ጭጋ​ግም ይም​ጣ​ባት፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 ጨለማና የሞት ጥላ ይውረሱት፤ ደመናም በላዩ ላይ ይረፍ፤ ብርሃኑን ጽልመት ይዋጠው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 ጨለማና የሞት ጥላ የራሳቸው ገንዘብ ያድርጉት፥ ዳመናም ይረፍበት፥ የቀን ጨለማ ያሸብረው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 በጭጋግና በድቅድቅ ጨለማ የተሸፈነ ይሁን፤ ደመና ረቦበት ጨለማ ብርሃኑን ይዋጠው፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 ጨለማና የሞት ጥላ የራሳቸው ገንዘብ ያድርጉት፥ ዳመናም ይረፍበት፥ የቀን ጨለማ ሁሉ ያስፈራው።

Ver Capítulo Copiar




ኢዮብ 3:5
25 Referencias Cruzadas  

በቍ​ር​በቴ ላይ ማቅ ሰፉ፤ መከ​ራዬ በመ​ሬት ላይ በዛች።


የጥ​ዋት ብር​ሃን ለእ​ነ​ርሱ ሁሉ እንደ ሞት ጥላ ነው፤ የሚ​ሆ​ነ​ውን ድን​ጋጤ ያው​ቃ​ሉና። ሞት​ንም ይጠ​ራ​ጠ​ራ​ሉና።


ለጨ​ለማ ወሰ​ንን ያደ​ር​ጋል፤ እርሱ ሁሉን ይመ​ረ​ም​ራል፥ የጨ​ለ​ማ​ንና የሞት ጥላ ድን​ጋ​ይ​ንም ይመ​ረ​ም​ራል።


ያች ቀን ጨለማ ትሁን፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከላይ አይ​መ​ል​ከ​ታት፥ ብር​ሃ​ንም አይ​ብ​ራ​ባት።


ያች ቀንም የተ​ረ​ገ​መች ትሁን። ያችም ሌሊት ጨለማ ይም​ጣ​ባት፤ በዓ​መቱ ቀኖች መካ​ከል አት​ኑር፤ በወ​ሮች ቀኖች ውስ​ጥም ገብታ አት​ቈ​ጠር።


ኀጢ​አ​ትን የሚ​ሠሩ የሚ​ሰ​ወ​ሩ​በት ቦታ የለም።


ከግ​ር​ማ​ህስ የተ​ነሣ የሞት በሮች ተከ​ፍ​ተ​ው​ል​ሃ​ልን? የሲ​ኦል በረ​ኞ​ችስ አን​ተን አይ​ተው ይደ​ነ​ግ​ጣ​ሉን?


ወደ ጽኑ ከተማ ማን ይወ​ስ​ደ​ኛል? ማንስ እስከ ኤዶ​ም​ያስ ይመ​ራ​ኛል?


ልቡ ንጹሕ የሆነ፥ እጆ​ቹም የነጹ፥ በነ​ፍሱ ላይ ከን​ቱን ያል​ወ​ሰደ፥ ለባ​ል​ን​ጀ​ራ​ውም በሽ​ን​ገላ ያል​ማለ።


በጨ​ለማ የሄደ ሕዝብ ታላቅ ብር​ሃን አየ፤ በሞት ጥላና በጨ​ለማ ሀገ​ርም ለነ​በሩ ብር​ሃን ወጣ​ላ​ቸው።


ሳይ​ጨ​ል​ም​ባ​ችሁ፥ ጨለ​ማም ባለ​ባ​ቸው ተራ​ሮች እግ​ሮ​ቻ​ችሁ ሳይ​ሰ​ነ​ካ​ከሉ ለአ​ም​ላ​ካ​ችሁ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ክብ​ርን ስጡ፤ በዚ​ያም የሞት ጥላ አለና በጨ​ለ​ማ​ውም ውስጥ ያኖ​ራ​ች​ኋ​ልና ብር​ሃ​ንን ተስፋ ታደ​ር​ጋ​ላ​ችሁ።


እነ​ር​ሱም፥ “ከግ​ብፅ ምድር ያወ​ጣን፥ በም​ድረ በዳና በባ​ድማ፥ ዕን​ጨ​ትና ውኃ፥ የእ​ን​ጨት ፍሬም በሌ​ለ​በት ምድር፥ ሰው በማ​ያ​ል​ፍ​በ​ትና የሰው ልጅም በማ​ይ​ቀ​መ​ጥ​በት ምድር የመ​ራን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወዴት አለ? አላ​ሉም።


ስለ​ዚህ ምድር ታለ​ቅ​ሳ​ለች፤ በላ​ይም ሰማይ ይጠ​ቍ​ራል፤ ተና​ግ​ሬ​አ​ለ​ሁና፤ አል​ጸ​ጸ​ትም ወደ​ፊት እሮ​ጣ​ለሁ፤ ከእ​ር​ስ​ዋም አል​መ​ለ​ስም።


ቀኑ ቅርብ ነው፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቀን ቅርብ ነው፤ የደ​መና ቀን፥ የአ​ሕ​ዛብ ማለ​ቂያ ጊዜ ይሆ​ናል።


በደ​መ​ናና በጭ​ጋግ ቀን እረኛ ከበ​ጎቹ መካ​ከል የተ​ለ​የ​ውን እን​ደ​ሚ​ፈ​ልግ፥ እን​ደ​ዚሁ በጎ​ችን እፈ​ል​ጋ​ለሁ፤ በደ​መ​ናና በጭ​ጋግ ቀን ከተ​በ​ተ​ኑ​ባ​ቸው ሀገ​ሮች ሁሉ እሰ​በ​ስ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ።


የጨ​ለ​ማና የነ​ፋስ ቀን፥ የደ​መ​ናና የጉም ቀን ነው፤ ታላ​ቅና ብርቱ ሕዝብ በተ​ራ​ሮች ላይ እንደ ወገ​ግታ ተዘ​ር​ግ​ቶ​አል፤ ከዘ​ለ​ዓ​ለ​ምም ጀምሮ እንደ እርሱ ያለ አል​ነ​በ​ረም፤ ከእ​ር​ሱም በኋላ እስከ ልጅ ልጅ ድረስ እንደ እርሱ ያለ አይ​ሆ​ንም።


ሁሉን የሚ​ሠ​ራና የሚ​ያ​ቅ​ናና፥ ብር​ሃ​ኑን ወደ መስዕ የሚ​መ​ል​ሰው፥ ቀኑን እንደ ሌሊት የሚ​ያ​ጨ​ል​መው፥ የባ​ሕ​ሩ​ንም ውኃ ጠርቶ በም​ድር ፊት የሚ​ያ​ፈ​ስ​ሰው ስሙ ሁሉን የሚ​ችል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው።


ዓመት በዓ​ላ​ች​ሁ​ንም ወደ ልቅሶ፥ ዝማ​ሬ​ያ​ች​ሁ​ንም ወደ ዋይታ እለ​ው​ጣ​ለሁ፤ ማቅ​ንም በወ​ገብ ሁሉ ላይ፥ ቡሃ​ነ​ት​ንም በራስ ሁሉ ላይ ላይ አመ​ጣ​ለሁ፤ እንደ ወዳጅ ልቅሶ አደ​ር​ጋ​ች​ኋ​ለሁ፤ ከእ​ር​ሱም ጋር ያሉት እንደ መከራ ቀን ይሆ​ናሉ።


ቀመጠው ሕዝብ ታላቅ ብርሃን አየ፤ በሞት አገርና ጥላ ለተቀመጡትም ብርሃን ወጣላቸው።”


በጨ​ለ​ማና በሞት ጥላ ለነ​በ​ሩት ብር​ሃ​ኑን ያሳ​ያ​ቸው ዘንድ፥ እግ​ሮ​ቻ​ች​ን​ንም ወደ ሰላም ጎዳና ያቀና ዘንድ ወጣ።”


እና​ን​ተም ቀር​ባ​ችሁ ከተ​ራ​ራው በታች ቆማ​ችሁ ነበር፤ ተራ​ራ​ውም እስከ ሰማይ ድረስ በእ​ሳት ይነ​ድድ ነበር፤ ጨለ​ማና አውሎ ነፋስ፥ ድቅ​ድቅ ጨለ​ማም ነበረ።


ሊዳ​ሰስ ወደ​ሚ​ችል ወደ​ሚ​ቃ​ጠ​ልም እሳት ወደ ጭጋ​ግም፥ ወደ ጨለ​ማም ወደ ዐውሎ ነፋ​ስም፥


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos