አሞጽ 5:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነገር ግን ጌልገላ ፈጽሞ ትማረካለችና፥ ቤቴልም እንዳልነበረች ትሆናለችና ቤቴልን አትፈልጉ፤ ወደ ጌልገላም አትሂዱ፤ ወደ ቤርሳቤህም አትለፉ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቤቴልን አትፈልጉ፤ ወደ ጌልገላ አትሂዱ፤ ወደ ቤርሳቤህም አትሻገሩ፤ ጌልገላ በርግጥ ትማረካለች፤ ቤቴልም እንዳልነበረች ትሆናለችና።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነገር ግን ጌልገላ ፈጽሞ ትማረካለችና፥ ቤቴልም ከንቱ ትሆናለችና ቤቴልን አትፈልጉ፥ ወደ ጌልገላም አትግቡ፥ ወደ ቤርሳቤህም አትለፉ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወደ ቤርሳቤህ አትሂዱ፤ ቤቴል ፈራርሳ እንዳልነበረች ስለምትሆን በጌልገላ የሚኖሩ ሕዝቦችም ስደት ስለ ተፈረደባቸው ወደ ቤቴልም ሆነ ወደ ጌልጌላ አትሂዱ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገር ግን ጌልገላ ፈጽሞ ትማረካለችና፥ ቤቴልም ከንቱ ትሆናለችና ቤቴልን አትፈልጉ፥ ወደ ጌልገላም አትግቡ፥ ወደ ቤርሳቤህም አትለፉ። |
አብርሃምም በዐዘቅተ መሐላ አጠገብ የተምር ዛፍን ተከለ፤ በዚያም የዘለዓለሙን አምላክ የእግዚአብሔርን ስም ጠራ።
ንጉሡም ተማከረ፤ ሁለትም የወርቅ ጥጆች ሠርቶ፥ “እስራኤል ሆይ፥ ወደ ኢየሩሳሌም መውጣት ይበቃችኋል፤ ከግብፅ ምድር ያወጡአችሁ አማልክቶቻችሁ እነሆ” አላቸው።
ካህናቱንም ሁሉ ከይሁዳ ከተሞች አወጣቸው፤ ከጌባልም ጀምሮ እስከ ቤርሳቤህ ድረስ ካህናት ያጥኑበት የነበረውን የኮረብታ መስገጃ ሁሉ ርኩስ አደረገው። በከተማዪቱም በር በግራ በኩል በነበረው በከተማዪቱ ሹም በኢያሱ በር መግቢያ አጠገብ የነበሩትን የበሮቹን መስገጃዎች አፈረሰ።
ምክርን ብትመክሩም እግዚአብሔር ምክራችሁን ይለውጣል፤ የተናገራችሁትም ነገር አይሆንላችሁም። እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነውና።
የእስራኤል ኀጢአት የሆኑት የአዎን የኮረብታው መስገጃዎች ይፈርሳሉ፤ እሾህና አሜከላም በመሠዊያዎቻቸው ላይ ይበቅላሉ፤ ተራሮችንም፥ “ክደኑን፤ ኮረብቶችንም፦ ውደቁብን” ይሉአቸዋል።
እስራኤል ሆይ! አንተ አላዋቂ አትሁን፤ አንተም ይሁዳ! ወደ ጌልጌላ አትሂድ፤ ወደ ቤትአዊንም አትውጡ፤ በሕያው እግዚአብሔርም አትማሉ።
ክፋታቸውም ሁሉ በጌልገላ አለ፤ በዚያ ጠልቻቸዋለሁ፤ ስለ ሠሩት ክፋት ከቤቴ አሳድዳቸዋለሁ፤ ከእንግዲህ ወዲያ አልወድዳቸውም፤ አለቆቻቸው ሁሉ ዐመፀኞች ናቸውና።
የደማስቆንም ቍልፎች እሰብራለሁ፤ በአዎን ሸለቆ የሚኖሩትንም ሰዎች አጠፋለሁ፤ የካራን ሰዎች ወገኖችንም እቈራርጣለሁ፤ የሶርያ ሕዝብም ወደ ቂር ይማረካሉ፤” ይላል እግዚአብሔር።
እስራኤልን ስለ ኀጢአቱ በምበቀልበት ቀን የቤቴልን መሠዊያዎች ደግሞ እበቀላለሁ፤ የመሠዊያው ቀንዶች ይሰበራሉ፤ ወደ ምድርም ይወድቃሉ።
“ወደ ቤቴል ገብታችሁ ኀጢአትን ሠራችሁ፤ በጌልገላም ኀጢአትን አበዛችሁ፤ በየማለዳውም መሥዋዕታችሁን፥ በየሦስተኛውም ቀን ዐሥራታችሁን አቀረባችሁ፤
የቤቴልም ካህን አሜስያስ ወደ እስራኤል ንጉሥ ወደ ኢዮርብዓም ልኮ፥ “አሞጽ በእስራኤል ቤት መካከል ዐምፆብሃል፤ ምድሪቱም ቃሉን ሁሉ ልትሸከም አትችልም” አለ።
ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ሚስትህ በከተማይቱ ውስጥ አመንዝራ ትሆናለች፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆችህም በሰይፍ ይወድቃሉ፤ ምድርህም በገመድ ትከፈላለች፤ አንተም በረከሰች ምድር ትሞታለህ፤ እስራኤልም ከምድሩ ተማርኮ ይሄዳል።”
መሳቂያ የሆኑ የኮረብታው መስገጃዎች ይፈርሳሉ፤ የእስራኤልም መቅደሶች ባድማ ይሆናሉ፤ በኢዮርብዓምም ቤት ላይ በሰይፍ እነሣለሁ” አለ።
ዳን ሆይ፥ ሕያው አምላክህን! ደግሞም፦ ሕያው የቤርሳቤህን አምላክ ብለው በሰማርያ መማፀኛ የሚምሉ፥ እነርሱ ይወድቃሉ፥ ደግሞም አይነሡም።”
ለዐዋቆች ጥበብን እንነግራቸዋለን፤ ነገር ግን የዚህን ዓለም ጥበብ ወይም ያልፉ ዘንድ ያላቸውን የዚህን ዓለም ሹሞች ጥበብ አይደለም።
እግዚአብሔርም ኢያሱን፥ “ዛሬ የግብፅን ተግዳሮት ከእናንተ ላይ አስወግጃለሁ” አለው፤ ስለዚህ የዚያ ስፍራ ስም እስከ ዛሬ ድረስ ጌልገላ ተብሎ ተጠራ።
በየዓመቱም ወደ ቤቴል፥ ወደ ጌልጌላና ወደ መሴፋ ይዞር ነበር፤ በእነዚያም በተቀደሱ ስፍራዎች ሁሉ በእስራኤል ላይ ይፈርድ ነበር።
የልጆቹም ስሞች እነዚህ ነበሩ። የበኵር ልጁ ስም ኢዩኤል፥ የሁለተኛውም ስም አብያ ነበረ። እነርሱም በቤርሳቤህ ፈራጆች ነበሩ።