Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -


1 ሳሙኤል 8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)


እስ​ራ​ኤል ንጉሥ እን​ዲ​ያ​ነ​ግ​ሥ​ላ​ቸው ሳሙ​ኤ​ልን እንደ ጠየቁ

1 እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ሳሙ​ኤል በሸ​መ​ገለ ጊዜ ልጆ​ቹን በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ፈራ​ጆች አድ​ርጎ ሾማ​ቸው።

2 የል​ጆ​ቹም ስሞች እነ​ዚህ ነበሩ። የበ​ኵር ልጁ ስም ኢዩ​ኤል፥ የሁ​ለ​ተ​ኛ​ውም ስም አብያ ነበረ። እነ​ር​ሱም በቤ​ር​ሳ​ቤህ ፈራ​ጆች ነበሩ።

3 ልጆ​ቹም በመ​ን​ገዱ አል​ሄ​ዱም፤ ነገር ግን ረብ ለማ​ግ​ኘት ፈቀቅ አሉ፤ መማ​ለጃ በሉ፤ ፍርድ አደሉ።

4 የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሰዎች ሁሉ በአ​ን​ድ​ነት ተሰ​ብ​ስ​በው ወደ ሳሙ​ኤል ወደ አር​ማ​ቴም መጡ፤

5 እን​ዲ​ህም አሉት፥ “እነሆ፥ አንተ ሸም​ግ​ለ​ሃል፤ ልጆ​ች​ህም በመ​ን​ገ​ድህ አይ​ሄ​ዱም፤ አሁ​ንም እንደ ሌሎች አሕ​ዛብ ሁሉ የሚ​ፈ​ር​ድ​ልን ንጉሥ አን​ግ​ሥ​ልን።”

6 “የሚ​ፈ​ር​ድ​ልን ንጉሥ ስጠን” ባሉት ጊዜም ነገሩ ሳሙ​ኤ​ልን አስ​ከ​ፋው፤ ሳሙ​ኤ​ልም ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸለየ።

7 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሳሙ​ኤ​ልን አለው፥ “በእ​ነ​ርሱ ላይ እን​ዳ​ል​ነ​ግሥ እኔን ናቁ እንጂ አን​ተን አል​ና​ቁ​ምና በሚ​ሉህ ነገር ሁሉ የሕ​ዝ​ቡን ቃል ስማ።

8 ከግ​ብፅ ካወ​ጣ​ኋ​ቸው ቀን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ እኔን ትተው እን​ግ​ዶች አማ​ል​ክ​ትን በማ​ም​ለ​ካ​ቸው እንደ ሠሩት ሥራ ሁሉ እን​ዲሁ በአ​ንተ ደግሞ ያደ​ር​ጉ​ብ​ሃል።

9 አሁ​ንም ቃላ​ቸ​ውን ስማ፤ ነገር ግን ጽኑ ምስ​ክር መስ​ክ​ር​ባ​ቸው፤ በእ​ነ​ር​ሱም ላይ የሚ​ነ​ግ​ሠ​ውን የን​ጉ​ሡን ሥር​ዐት ንገ​ራ​ቸው።”

10 ሳሙ​ኤ​ልም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ሁሉ ንጉ​ሥን ለፈ​ለጉ ሕዝብ ነገ​ራ​ቸው።

11 እን​ዲ​ህም አለ፥ “በእ​ና​ንተ ላይ የሚ​ነ​ግ​ሠው የን​ጉሡ ሥር​ዐት ይህ ነው፤ ወን​ዶች ልጆ​ቻ​ች​ሁን ወስዶ ሰረ​ገላ ነጂ​ዎ​ችና ፈረ​ሰ​ኞች ያደ​ር​ጋ​ቸ​ዋል፤ በሰ​ረ​ገ​ሎ​ችም ፊት ይሮ​ጣሉ፤

12 ለራ​ሱም የሻ​ለ​ቆ​ችና የመቶ አለ​ቆች የአ​ምሳ አለ​ቆ​ችም ያደ​ር​ጋ​ቸ​ዋል፤ እር​ሻ​ው​ንም የሚ​ያ​ርሱ፥ እህ​ሉ​ንም የሚ​ያ​ጭዱ፥ ፍሬ​ው​ንም የሚ​ለ​ቅሙ፥ የጦር መሣ​ሪ​ያ​ው​ንና የሰ​ረ​ገ​ሎ​ቹ​ንም ዕቃ የሚ​ሠሩ ያደ​ር​ጋ​ቸ​ዋል።

13 ሴቶች ልጆ​ቻ​ች​ሁ​ንም ወስዶ ሽቱ ቀማ​ሚ​ዎ​ችና ወጥ ቤቶች፥ አበ​ዛ​ዎ​ችም ያደ​ር​ጋ​ቸ​ዋል።

14 እር​ሻ​ች​ሁ​ንና ወይ​ና​ች​ሁ​ንም፥ መል​ካም መል​ካ​ሙ​ንም የዘ​ይት ቦታ​ች​ሁን ወስዶ ለሎ​ሌ​ዎቹ ይሰ​ጣ​ቸ​ዋል።

15 ከዘ​ራ​ች​ሁና ከወ​ይ​ና​ች​ሁም ዐሥ​ራት ወስዶ ለጃ​ን​ደ​ረ​ቦ​ቹና ለሎ​ሌ​ዎቹ ይሰ​ጣ​ቸ​ዋል።

16 ሎሌ​ዎ​ቻ​ች​ሁ​ንና ገረ​ዶ​ቻ​ች​ሁን፥ ከከ​ብ​ቶ​ቻ​ች​ሁና ከአ​ህ​ዮ​ቻ​ች​ሁም መል​ካም መል​ካ​ሙን ወስዶ ያሠ​ራ​ቸ​ዋል።

17 ከላ​ሞ​ቻ​ችሁ፥ ከበ​ጎ​ቻ​ች​ሁና ከፍ​የ​ሎ​ች​ቻ​ች​ሁም ዐሥ​ራት ይወ​ስ​ዳል፤ እና​ን​ተም ባሪ​ያ​ዎች ትሆ​ኑ​ታ​ላ​ችሁ።

18 በዚ​ያም ቀን ለእ​ና​ንተ ከመ​ረ​ጣ​ች​ሁት ከን​ጉ​ሣ​ችሁ የተ​ነሣ ትጮ​ኻ​ላ​ችሁ፤ በእ​ነ​ዚ​ያም ወራት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አይ​ሰ​ማ​ች​ሁም። ለራ​ሳ​ችሁ ንጉሥ መር​ጣ​ች​ኋ​ልና።”

19 ሕዝቡ ግን የሳ​ሙ​ኤ​ልን ነገር ይሰሙ ዘንድ እንቢ አሉ፥ “እን​ዲህ አይ​ሁን፤ ነገር ግን ንጉሥ አን​ግ​ሥ​ልን፤

20 እኛም ደግሞ እንደ አሕ​ዛብ ሁሉ እን​ሆ​ና​ለን፤ ንጉ​ሣ​ች​ንም ይፈ​ር​ድ​ል​ናል፤ በፊ​ታ​ች​ንም ወጥቶ ስለ እኛ ጠላ​ታ​ች​ንን ይዋ​ጋል” አሉት።

21 ሳሙ​ኤ​ልም የሕ​ዝ​ቡን ቃል ሁሉ ሰማ፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ተና​ገረ።

22 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሳሙ​ኤ​ልን፥ “ቃላ​ቸ​ውን ስማ፤ ንጉ​ሥም አን​ግ​ሥ​ላ​ቸው” አለው። ሳሙ​ኤ​ልም የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ሰዎች፥ “እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ችሁ ወደ ከተ​ማ​ችሁ ሂዱ” አላ​ቸው።

Síguenos en:



Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos