Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -


ዘፍጥረት 26 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)


ይስ​ሐቅ ወደ ጌራራ መሄዱ

1 በም​ድ​ርም ቀድሞ በአ​ብ​ር​ሃም ዘመን ከሆ​ነው ራብ ሌላ ራብ ሆነ፤ ይስ​ሐ​ቅም ወደ ፍል​ስ​ጥ​ኤም ንጉሥ ወደ አቤ​ሜ​ሌክ ወደ ጌራራ ሄደ።

2 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ተገ​ለ​ጠ​ለት፤ እን​ዲ​ህም አለው፥ “ወደ ግብፅ አት​ው​ረድ፤ እኔ በም​ልህ ምድር ተቀ​መጥ።

3 በዚ​ህች ምድር ተቀ​መጥ፤ ከአ​ንተ ጋርም እሆ​ና​ለሁ፤ እባ​ር​ክ​ሃ​ለ​ሁም፤ ይህ​ችን ምድር ሁሉ ለአ​ን​ተም፥ ለዘ​ር​ህም እሰ​ጣ​ለ​ሁና፥ ለአ​ባ​ት​ህም ለአ​ብ​ር​ሃም የማ​ል​ሁ​ለ​ትን መሐላ ከአ​ንተ ጋር አጸ​ና​ለሁ።

4 ዘር​ህ​ንም እንደ ሰማይ ከዋ​ክ​ብት አበ​ዛ​ዋ​ለሁ፤ ይህ​ች​ንም ምድር ሁሉ ለዘ​ርህ እሰ​ጣ​ለሁ፤ የም​ድ​ርም ሕዝ​ቦች ሁሉ በዘ​ርህ ይባ​ረ​ካሉ፤

5 አባ​ትህ አብ​ር​ሃም ቃሌን ሰም​ቶ​አ​ልና፤ ትእ​ዛ​ዜ​ንና ፍር​ዴን፥ ሥር​ዐ​ቴ​ንና ሕጌ​ንም ጠብ​ቆ​አ​ልና።”

6 ይስ​ሐ​ቅም በጌ​ራራ ተቀ​መጠ። የዚ​ያም ስፍራ ሰዎች ስለ ሚስቱ ስለ ርብቃ ጠየ​ቁት፤ እር​ሱም፥ “እኅቴ ናት” አላ​ቸው፤

7 የዚህ ስፍራ ሰዎች ለር​ብቃ ሲሉ እን​ዳ​ይ​ገ​ድ​ሉኝ ብሎ ሚስቴ ናት ማለ​ትን ፈር​ቶ​አ​ልና፤ እር​ስ​ዋም ውብ ነበ​ረ​ችና።

8 በዚ​ያም ብዙ ቀን ተቀ​መጠ። የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤም ንጉሥ አቤ​ሜ​ሌ​ክም በመ​ስ​ኮት ሆኖ በተ​መ​ለ​ከተ ጊዜ ይስ​ሐ​ቅን ከሚ​ስቱ ከር​ብቃ ጋር ሲጫ​ወት አየው።

9 አቤ​ሜ​ሌ​ክም ይስ​ሐ​ቅን ጠራ፤ እን​ዲ​ህም አለው፥ “እነሆ፥ ሚስ​ትህ ናት፤ እን​ዴ​ትስ እር​ስ​ዋን፦ ‘እኅቴ ናት’ አልህ?” ይስ​ሐ​ቅም፥ “በእ​ር​ስዋ ምክ​ን​ያት እን​ዳ​ል​ሞት ብዬ ነው” አለው።

10 አቤ​ሜ​ሌ​ክም አለ፥ “ይህ ያደ​ረ​ግ​ህ​ብን ምን​ድን ነው? ከሕ​ዝቡ አንዱ ባለ​ማ​ወቅ ከሚ​ስ​ትህ ጋር ሊተኛ ጥቂት በቀ​ረው ነበር፤ ኀጢ​አ​ት​ንም ልታ​መ​ጣ​ብን ነበር።”

11 አቤ​ሜ​ሌ​ክም ሕዝ​ቡን ሁሉ፥ “ይህን ሰው፥ ሚስ​ቱ​ንም የሚ​ነካ ፍርዱ ክፉ ሞት ነው” ብሎ አዘዘ።

12 ይስ​ሐ​ቅም በዚ​ያች ምድር ዘርን ዘራ፤ በዚ​ያች ዓመ​ትም መቶ እጥፍ ገብስ አገኘ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ባረ​ከው።

13 ከፍ ከፍም አለ፤ እጅ​ግም ታላቅ እስ​ኪ​ሆን ድረስ እየ​ጨ​መረ ይበዛ ነበር፤

14 ወን​ዶ​ችና ሴቶች አገ​ል​ጋ​ዮ​ችን፥ ብዙ በጎ​ች​ንና ላሞ​ችን፥ የእ​ርሻ መሬ​ት​ንም ገዛ፤ የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤም ሰዎ​ችም ቀኑ​በት።

15 በአ​ባቱ በአ​ብ​ር​ሃም ዘመን የአ​ባቱ ሎሌ​ዎች የማ​ሱ​አ​ቸ​ውን ጕድ​ጓ​ዶች ሁሉ የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤም ሰዎች ደፈ​ኑ​አ​ቸው፤ አፈ​ር​ንም ሞሉ​ባ​ቸው።

16 አቤ​ሜ​ሌ​ክም ይስ​ሐ​ቅን፥ “ከእኛ ተለ​ይ​ተህ ሂድ፤ ከእኛ ይልቅ እጅግ በር​ት​ተ​ሃ​ልና” አለው።

17 ይስ​ሐ​ቅም ከዚያ ሄደ፤ በጌ​ራ​ራም ሸለቆ ሰፈረ፤ በዚ​ያም ተቀ​መጠ።

18 ይስ​ሐ​ቅም የአ​ባቱ የአ​ብ​ር​ሃም አገ​ል​ጋ​ዮች ቈፍ​ረ​ዋ​ቸው የነ​በ​ሩ​ትን የውኃ ጕድ​ጓ​ዶች ደግሞ አስ​ቈ​ፈረ፤ አባቱ አብ​ር​ሃም ከሞተ በኋላ የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤም ሰዎች ደፍ​ነ​ዋ​ቸው ነበ​ርና፤ አባ​ቱም አብ​ር​ሃም ይጠ​ራ​ቸው በነ​በ​ረው ስም ጠራ​ቸው።

19 የይ​ስ​ሐቅ ሎሌ​ዎ​ችም በጌ​ራራ ሸለቆ ውስጥ ጕድ​ጓድ ቈፈሩ፤ በዚ​ያም ጣፋጭ የውኃ ምንጭ አገኙ።

20 የጌ​ራራ እረ​ኞች ከይ​ስ​ሐቅ እረ​ኞች ጋር፥ “ውኃው የእኛ ነው” ሲሉ ተጣሉ፤ የዚ​ያ​ች​ንም ጕድ​ጓድ ስም “ዐዘ​ቅተ ዐመፃ” ብሎ ጠራት፤ እነ​ርሱ በድ​ለ​ው​ታ​ልና።

21 ይስ​ሐ​ቅም ከዚያ ሄደ በዚ​ያም ሌላ ጕድ​ጓድ ማሰ፥ ስለ እር​ስ​ዋም ደግሞ ተጣ​ሉት፤ ስም​ዋ​ንም “ጽልእ” ብሎ ጠራት።

22 ከዚ​ያም እልፍ ብሎ ሌላ ጕድ​ጓድ ቈፈረ፤ ስለ እር​ስ​ዋም አል​ተ​ጣ​ሉ​ትም፤ ስም​ዋ​ንም “መር​ኅብ” ብሎ ጠራት፤ እን​ዲህ ሲል፥ “አሁን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አሰ​ፋ​ልን፤ በም​ድ​ርም አበ​ዛን።”

23 ከዚ​ያም ወደ ዐዘ​ቅተ መሐላ ሄደ።

24 በዚ​ያ​ችም ሌሊት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተገ​ለ​ጠ​ለት፤ እን​ዲ​ህም አለው፥ “እኔ የአ​ባ​ትህ የአ​ብ​ር​ሃም አም​ላክ ነኝ፤ አት​ፍራ፤ እኔ ከአ​ንተ ጋር ነኝና፤ እባ​ር​ክ​ሃ​ለሁ፤ ስለ አባ​ትህ ስለ አብ​ር​ሃም ዘር​ህን አበ​ዛ​ዋ​ለሁ።”

25 በዚ​ያም ለአ​ም​ላኩ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሠ​ው​ያን ሠራ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ስም ጠራ፤ በዚ​ያም ድን​ኳን ተከለ፤ የይ​ስ​ሐ​ቅም ሎሌ​ዎች በዚያ ጕድ​ጓድ ማሱ።


በይ​ስ​ሐ​ቅና በአ​ቤ​ሜ​ሌክ መካ​ከል የተ​ደ​ረገ ስም​ም​ነት

26 አቤ​ሜ​ሌ​ክና ሚዜው አኮ​ዘት፥ የሠ​ራ​ዊ​ቱም አለቃ ፋኮል ከጌ​ራራ ወደ እርሱ ሄዱ።

27 ይስ​ሐ​ቅም፥ “ለምን ወደ እኔ መጣ​ችሁ? እና​ንተ ጠል​ታ​ች​ሁ​ኛል፤ ከእ​ና​ን​ተም ለይ​ታ​ችሁ አሳ​ድ​ዳ​ች​ሁ​ኛ​ልና” አላ​ቸው።

28 እነ​ር​ሱም አሉት፥ “እኛ የጠ​ላ​ንህ አይ​ደ​ለም፤ በመ​ል​ካም አኑ​ረን፥ በመ​ል​ካም አሰ​ና​በ​ት​ንህ እንጂ፥ አሁ​ንም አንተ ለአ​ም​ላ​ክህ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቡሩክ ነህ።

29 አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከአ​ንተ ጋር እንደ አለ በአ​የን ጊዜ በአ​ን​ተና በእኛ መካ​ከል መሐላ ይሁን፤ አንተ በእኛ ላይ ክፉ እን​ዳ​ታ​ደ​ርግ፤ እኛም በአ​ንተ ላይ ክፉ እን​ዳ​ና​ደ​ርግ እን​ማ​ማ​ላ​ለን።”

30 ይስ​ሐ​ቅም ማዕድ አቀ​ረ​በ​ላ​ቸው፤ በሉም፤ ጠጡም።

31 ማል​ደ​ውም ተነሡ፤ እርስ በር​ሳ​ቸ​ውም ተማ​ማሉ፤ ይስ​ሐ​ቅም አሰ​ና​በ​ታ​ቸው፤ ከእ​ር​ሱም በደ​ኅና ሄዱ።

32 በዚ​ያም ቀን የይ​ስ​ሐቅ ሎሌ​ዎች መጡ፤ ስለ ቈፈ​ሩ​አ​ትም ጕድ​ጓድ፥ ውኃ አገ​ኘን ብለው ነገ​ሩት።

33 ስም​ዋ​ንም “መሐላ” ብሎ ጠራት፤ ስለ​ዚ​ህም የከ​ተ​ማ​ዪቱ ስም እስከ ዛሬ ድረስ “ዐዘ​ቅተ መሐላ” ይባ​ላል።


ዔሳው ከከ​ነ​ዓን ሚስ​ቶ​ችን እንደ አገባ

34 ዔሳ​ውም አርባ ዓመት ሲሆ​ነው የኬ​ጢ​ያ​ዊው የብ​ኤ​ልን ልጅ ዮዲ​ትን፥ የኬ​ጢ​ያ​ዊው የኤ​ሎ​ንን ልጅ ቤሴ​ሞ​ት​ንም ሚስ​ቶች አድ​ርጎ አገባ፤

35 እነ​ር​ሱም ይስ​ሐ​ቅ​ንና ርብ​ቃን ያሳ​ዝኑ ነበር።

Síguenos en:



Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos