2 ነገሥት 8:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኤልሳዕም ልጅዋን ያስነሣላትን ሴት፥ “አንቺ ከቤተ ሰብሽ ጋር ተነሥተሽ ሂጂ፤ በምታገኚውም ስፍራ ተቀመጪ፤ እግዚአብሔር በምድር ራብን ጠርቶአልና፤ ሰባት ዓመትም በምድር ላይ ይቆያል” ብሎ ተናገራት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚህ ጊዜ ኤልሳዕ፣ ልጇ ከሞት ያስነሣላትን ሴት፣ “እግዚአብሔር በምድሪቱ ላይ የሰባት ዓመት ራብ ስለ ወሰነ፣ ተነሺና ለጊዜው መቈየት ወደምትችዪበት ቦታ ከቤተ ሰብሽ ጋራ ሂጂ” አላት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ልጇን ከሞት ያስነሣላትን፥ በሱነም ትኖር የነበረችውን ሴት እነሆ፥ ኤልሳዕ አስቀድሞ እንዲህ ሲል ነግሮአት ነበር፥ “እግዚአብሔር እስከ ሰባት ዓመት የሚቆይ ራብ በዚህች ምድር ላይ ልኮአል፤ ከቤተሰብሽ ጋር በሕይወት ለመትረፍ ከዚህ ተነሥተሽ ወደ ሌላ ስፍራ ሂጂ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ልጅዋን ከሞት ያስነሣላትን፥ በሱነም ትኖር የነበረችውን ሴት እነሆ፥ ኤልሳዕ አስቀድሞ እንዲህ ሲል ነግሮአት ነበር፥ “እግዚአብሔር እስከ ሰባት ዓመት የሚቈይ ራብ በዚህች ምድር ላይ ልኮአል፤ ከቤተሰብሽ ጋር በሕይወት ለመትረፍ ከዚህ ተነሥተሽ ወደ ሌላ ስፍራ ሂጂ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኤልሳዕም ልጅዋን ያስነሥላትን ሴት “አንቺ ከቤተ ሰብሽ ጋር ተነሥተሽ ሂጂ፤ በምታገኚውም ስፍራ ተቀመጪ፤ እግዚአብሔር ራብ ጠርቶአል፤ ሰባት ዓመትም በምድር ላይ ይመጣል፤” ብሎ ተናገራት። |
በምድርም ቀድሞ በአብርሃም ዘመን ከሆነው ራብ ሌላ ራብ ሆነ፤ ይስሐቅም ወደ ፍልስጥኤም ንጉሥ ወደ አቤሜሌክ ወደ ጌራራ ሄደ።
ሕልሙም ለፈርዖን ደጋግሞ መታየቱ ነገሩ ከእግዚአብሔር ዘንድ የተቈረጠ ስለሆነ ነው፤ እግዚአብሔርም ፈጥኖ ያደርገዋል።
ፈርዖንንም እንዲህ አሉት፥ “በምድር ልንቀመጥ በእንግድነት መጣን፤ የአገልጋዮችህ በጎች የሚሰማሩበት ስፍራ የለምና፤ ራብም በከነዓን ምድር እጅግ ጸንቶአልና፤ አሁንም አገልጋዮችህ በጌሤም ምድር እንቀመጥ።”
በዳዊትም ዘመን ሦስት ዓመት ያህል በተከታታይ ራብ ሆነ፤ ዳዊትም የእግዚአብሔርን ቃል ጠየቀ። እግዚአብሔርም አለ፥ “የገባዖንን ሰዎች ስለ ገደለ በሳኦልና በቤቱ ላይ ደም አለበት፥”
ጋድም ወደ ዳዊት መጥቶ፥ “የሦስት ዓመት ራብ በሀገርህ ላይ ይምጣብህን? ወይስ ጠላቶችህ እያሳደዱህ ሦስት ወር ከእነርሱ ትሸሽን? ወይስ የሦስት ቀን ቸነፈር በሀገርህ ላይ ይሁን? የሚሻልህን ምረጥ። አሁንም ለላከኝ ምን መልስ እንደምሰጥ አስብና መርምር” ብሎ ነገረው።
በገለዓድ ቴስባን የነበረው ቴስብያዊው ነቢዩ ኤልያስ አክዓብን፥ “በፊቱ የቆምሁት የኀያላን አምላክ የእስራኤል አምላክ ሕያው እግዚአብሔርን! ከአፌ ቃል በቀር በእነዚህ ዓመታት ዝናብም ጠልም አይወርድም” አለው።
ግያዝንም ጠርቶ፥ “ይህችን ሱማናዊት ጥራ” አለው። ጠራትም፤ ወደ እርሱም በገባች ጊዜ፥ “ልጅሽን አንሥተሽ ውሰጂ” አላት።
ኤልሳዕም ዳግመኛ ወደ ጌልጌላ ተመለሰ፤ በምድርም ላይ ራብ ነበረ፤ የነቢያትም ልጆች በፊቱ ተቀምጠው ነበር፤ ኤልሳዕም ሎሌውን፥ “ታላቁን ምንቸት ጣድ፤ ለነቢያትም ልጆች ቅጠላ ቅጠል አብስልላቸው” አለው።
እነሆ ስሜ የተጠራባትን ከተማ አስጨንቃት ዘንድ እጀምራለሁ፤ በውኑ እናንተ መንጻትን ትነጻላችሁን? በምድር በሚኖሩ ሁሉ ላይ ሰይፍን እጠራለሁና አትነጹም፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
በእህል ረሃብ ባስጨነክኋችሁ ጊዜ ዐሥር ሴቶች እንጀራ በአንድ ምጣድ ይጋግራሉ፤ በሚዛንም መዝነው እንጀራችሁን ይመልሱላችኋል፤ በበላችሁም ጊዜ አትጠግቡም።
“በከተማችሁ ሁሉ ጥርስን ማጥረስን፥ በስፍራችሁም ሁሉ እንጀራን ማጣትን ሰጠኋችሁ፤ እናንተ ግን ወደ እኔ አልተመለሳችሁም ይላል እግዚአብሔር።
እኔም በምድርና በተራሮች፥ በእህልና በወይንም፥ በዘይትና ምድርም በምታበቅለው ላይ፥ በሰዎችና በእንስሶችም ላይ፥ እጅም በሚደክምበት ሁሉ ላይ ድርቅን ጠርቻለሁ።
እውነት እላችኋለሁ፤ በነቢዩ በኤልያስ ዘመን በምድር ሁሉ ብርቱ ረኃብ እስኪሆን ድረስ ሰማይ ሦስት ዓመት ከስድስት ወር በተዘጋበት ጊዜ ብዙ መበለቶች በእስራኤል ውስጥ ነበሩ።
ከመካከላቸውም አጋቦስ የተባለ አንድ ሰው ተነሥቶ በዓለም ሁሉ ጽኑ ረኃብ እንደሚመጣ በመንፈስ ቅዱስ ተገልጦለት ተናገረ፤ ይህም በቄሣር ቀላውዴዎስ ዘመን ሆነ።
እንዲህም ሆነ፥ መሳፍንት ይፈርዱ በነበረ ጊዜ በአገሩ ላይ ራብ ሆነ። አንድ ሰውም ከሚስቱና ከሁለቱ ልጆቹ ጋር በሞዓብ ምድር ሊቀመጥ ከቤተ ልሔም ይሁዳ ተነሥቶ ሄደ።