Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -


2 ነገሥት 8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)


የሱ​ማ​ና​ዊቱ ሴት ከስ​ደት መመ​ለስ

1 ኤል​ሳ​ዕም ልጅ​ዋን ያስ​ነ​ሣ​ላ​ትን ሴት፥ “አንቺ ከቤተ ሰብሽ ጋር ተነ​ሥ​ተሽ ሂጂ፤ በም​ታ​ገ​ኚ​ውም ስፍራ ተቀ​መጪ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በም​ድር ራብን ጠር​ቶ​አ​ልና፤ ሰባት ዓመ​ትም በም​ድር ላይ ይቆ​ያል” ብሎ ተና​ገ​ራት።

2 ሴቲ​ቱም ተነ​ሥታ ኤል​ሳዕ እንደ ነገ​ራት አደ​ረ​ገች፤ ከቤተ ሰብ​ዋም ጋር ሄዳ በፍ​ል​ስ​ጥ​ኤም ሀገር ሰባት ዓመት ተቀ​መ​ጠች።

3 ሰባ​ቱም ዓመት ካለፈ በኋላ ያች ሴት ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤም ሀገር ተመ​ለ​ሰች፤ ሄዳም ስለ ቤቷና ስለ መሬቷ ልት​ጮህ ወደ ንጉሡ ወጣች።

4 ንጉ​ሡም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰው የኤ​ል​ሳዕ ሎሌ ግያ​ዝን፥ “ኤል​ሳዕ ያደ​ረ​ገ​ውን ታላ​ላቅ ተአ​ም​ራት ሁሉ ንገ​ረኝ” እያለ ይነ​ጋ​ገር ነበር።

5 እር​ሱም የሞ​ተ​ውን ሕፃን እንደ አስ​ነሣ ለን​ጉሡ ሲና​ገር፥ እነሆ፥ ልጅ​ዋን ያስ​ነ​ሣ​ላት ያች ሴት መጥታ ስለ ቤቷና ስለ መሬቷ ወደ ንጉሥ ጮኸች፥ ግያ​ዝም፥ “ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፥ ሴቲቱ ይህች ናት፤ ኤል​ሳ​ዕም ያስ​ነ​ሣው ልጅዋ ይህ ነው፤” አለ።

6 ንጉ​ሡም ሴቲ​ቱን ጠየ​ቃት፤ እር​ስ​ዋም ነገ​ረ​ችው። ንጉ​ሡም ከባ​ለ​ሟ​ሎቹ አን​ዱን ሰጣት፤ “እህ​ል​ዋ​ንና ገን​ዘ​ብ​ዋን ሁሉ ሀገ​ሩን ከተ​ወች ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ የሄደ ቦታ​ዋን ሁሉ መል​ስ​ላት” አለው።


ነቢዩ ኤል​ሳ​ዕና የሶ​ር​ያው ንጉሥ ወልደ አዴር

7 ኤል​ሳ​ዕም ወደ ደማ​ስቆ ሄደ፤ የሶ​ር​ያም ንጉሥ ወልደ አዴር ታምሞ ነበር፤ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰው ወደ​ዚህ መጥ​ቶ​አል” ብለ​ውም ነገ​ሩት።

8 ንጉ​ሡም አዛ​ሄ​ልን፥ “ገጸ በረ​ከት በእ​ጅህ ወስ​ደህ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሰው ተቀ​በ​ለው፤ ከዚ​ህም በሽታ እድን እንደ ሆነ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ጠይ​ቀው” አለው።

9 አዛ​ሄ​ልም ሊገ​ና​ኘው ሄደ፤ ከእ​ር​ሱም ጋር ከደ​ማ​ስቆ መል​ካ​ሙን ነገር ሁሉ የአ​ርባ ግመል ጭነት ገጸ በረ​ከት ወሰደ፤ መጥ​ቶም በፊቱ ቆመና፥ “ልጅህ የሶ​ርያ ንጉሥ ወልደ አዴር፦ ከዚህ በሽታ እድ​ና​ለ​ሁን? ሲል ወደ አንተ ልኮ​ኛል” አለው።

10 ኤል​ሳ​ዕም፥ “ሂድ፥ መዳ​ንስ ትድ​ና​ለህ በለው፤ ነገር ግን እን​ዲ​ሞት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አሳ​ይ​ቶ​ኛል” አለው።

11 እስ​ኪ​ያ​ፍ​ርም ድረስ ትኩር ብሎ ፊቱን ተመ​ለ​ከ​ተው፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሰው አለ​ቀሰ።

12 አዛ​ሄ​ልም፥ “ጌታ​ዬን ምን ያስ​ለ​ቅ​ሰ​ዋል?” አለ። ኤል​ሳ​ዕም፥ “በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ላይ የም​ታ​ደ​ር​ገ​ውን ክፋት ስለ​ማ​ውቅ ነው፤ ምሽ​ጎ​ቻ​ቸ​ውን በእ​ሳት ታቃ​ጥ​ላ​ለህ፤ ጐል​ማ​ሶ​ቻ​ቸ​ው​ንም በሰ​ይፍ ትገ​ድ​ላ​ለህ፤ ሕፃ​ና​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም ትፈ​ጠ​ፍ​ጣ​ለህ፤ እር​ጉ​ዞ​ቻ​ቸ​ው​ንም ትሰ​ነ​ጥ​ቃ​ለህ፤” አለው።

13 አዛ​ሄ​ልም፥ “ይህን ታላቅ ነገር አደ​ርግ ዘንድ እኔ የሞተ ውሻ አገ​ል​ጋ​ይህ ምን​ድን ነኝ?” አለ። ኤል​ሳ​ዕም፥ “አንተ በሶ​ርያ ላይ ንጉሥ እን​ድ​ት​ሆን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አሳ​ይ​ቶ​ኛል” አለው።

14 ከኤ​ል​ሳ​ዕም ወጥቶ ወደ ጌታው መጣ፤ እር​ሱም፥ “ኤል​ሳዕ ምን አለህ?” አለው፤ እር​ሱም አለው፥ “መዳ​ንን ትድ​ና​ለህ በለው አለኝ።”

15 ከዚ​ህም በኋላ በነ​ጋው ለሐፍ ወስዶ በውኃ ነከ​ረው፤ በፊ​ቱም ላይ ሸፈ​ነው፥ ሞተም። አዛ​ሄ​ልም በፋ​ን​ታው ነገሠ።

16 በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ በአ​ክ​ዓብ ልጅ በኢ​ዮ​ራም በአ​ም​ስ​ተ​ኛው ዓመት የይ​ሁዳ ንጉሥ የኢ​ዮ​ሣ​ፍጥ ልጅ ኢዮ​ራም በይ​ሁዳ ነገሠ።

17 መን​ገ​ሥም በጀ​መረ ጊዜ የሠ​ላሳ ሁለት ዓመት ጐል​ማሳ ነበረ፥ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ስም​ንት ዓመት ነገሠ።

18 የአ​ክ​ዓ​ብ​ንም ልጅ አግ​ብቶ ነበ​ርና የአ​ክ​ዓብ ቤት እን​ዳ​ደ​ረገ በእ​ስ​ራ​ኤል ነገ​ሥ​ታት መን​ገድ ሄደ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ክፉ አደ​ረገ።

19 ነገር ግን ለእ​ር​ሱና ለል​ጆቹ በዘ​መኑ ሁሉ መብ​ራት ይሰ​ጠው ዘንድ ተስፋ እንደ አደ​ረ​ገ​ለት፥ ስለ ባሪ​ያው ስለ ዳዊት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይሁ​ዳን ያጠፋ ዘንድ አል​ወ​ደ​ደም።

20 በእ​ር​ሱም ዘመን የኤ​ዶ​ም​ያስ ሰዎች ሸፍ​ተው የይ​ሁዳ ሰዎ​ችን ከዱ​አ​ቸው፤ በላ​ያ​ቸ​ውም ንጉሥ አነ​ገሡ።

21 ኢዮ​ራ​ምም ከሰ​ረ​ገ​ሎቹ ሁሉ ጋር ወደ ሲሆር አለፈ፤ ተነ​ሥ​ቶም እር​ሱ​ንና የሰ​ረ​ገ​ሎ​ችን አለ​ቆች ከብ​በው የነ​በ​ሩ​ትን የኤ​ዶ​ም​ያ​ስን ሰዎች አጠ​ፋ​ቸው፤ ሕዝቡ ግን ወደ እየ​ቤቱ ሸሸ።

22 ኤዶ​ም​ያስ ግን ለይ​ሁዳ እን​ዳ​ይ​ገ​ብር እስከ ዛሬ ድረስ በይ​ሁዳ ላይ ሸፈተ። በዚ​ያም ዘመን ደግሞ የሎ​ምና ሰዎች ሸፈቱ።

23 የተ​ረ​ፈ​ውም የኢ​ዮ​ራም ነገር ያደ​ረ​ገ​ውም ሁሉ፥ በይ​ሁዳ ነገ​ሥ​ታት የታ​ሪክ መጽ​ሐፍ የተ​ጻፈ አይ​ደ​ለ​ምን?

24 ኢዮ​ራ​ምም ከአ​ባ​ቶቹ ጋር አን​ቀ​ላፋ፥ በአ​ባ​ቱም በዳ​ዊት ከተማ ከአ​ባ​ቶቹ ጋር ተቀ​በረ፤ በፋ​ን​ታ​ውም ልጁ አካ​ዝ​ያስ ነገሠ።


አካ​ዝ​ያስ በይ​ሁዳ እንደ ነገሠ
( 2ዜ.መ. 22፥1-6 )

25 በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ በአ​ክ​ዓብ ልጅ በኢ​ዮ​ራም በዐ​ሥራ ሁለ​ተ​ኛው ዓመት የይ​ሁዳ ንጉሥ የኢ​ዮ​ራም ልጅ አካ​ዝ​ያስ ነገሠ።

26 መን​ገ​ሥም በጀ​መረ ጊዜ አካ​ዝ​ያስ የሃያ ሁለት ዓመት ጐል​ማሳ ነበረ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም አንድ ዓመት ነገሠ። እና​ቱም ጎቶ​ልያ የተ​ባ​ለች የእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ የዘ​ን​በሪ ልጅ ነበ​ረች።

27 በአ​ክ​ዓ​ብም ቤት መን​ገድ ሄደ፤ እንደ አክ​ዓ​ብም ቤት በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ክፉ አደ​ረገ።

28 ከአ​ክ​ዓ​ብም ልጅ ከኢ​ዮ​ራም ጋር የሶ​ር​ያን ንጉሥ አዛ​ሄ​ልን በሬ​ማት ዘገ​ለ​ዓድ ሊጋ​ጠም ሄደ፤ ሶር​ያ​ው​ያ​ንም ኢዮ​ራ​ምን አቈ​ሰ​ሉት።

29 ንጉ​ሡም ኢዮ​ራም ከሶ​ርያ ንጉሥ ከአ​ዛ​ሄል ጋር በተ​ዋጋ ጊዜ ሶር​ያ​ው​ያን በሬ​ማት ያቈ​ሰ​ሉ​ትን ቍስል ይታ​ከም ዘንድ ወደ ኢይ​ዝ​ራ​ኤል ተመ​ለሰ። የአ​ክ​ዓ​ብም ልጅ ኢዮ​ራም ታምሞ ነበ​ርና የኢ​ዮ​ራም ልጅ አካ​ዝ​ያስ ሊያ​የው ወደ ኢይ​ዝ​ራ​ኤል ወረደ።

Síguenos en:



Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos