Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘፍጥረት 47:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 ፈር​ዖ​ን​ንም እን​ዲህ አሉት፥ “በም​ድር ልን​ቀ​መጥ በእ​ን​ግ​ድ​ነት መጣን፤ የአ​ገ​ል​ጋ​ዮ​ችህ በጎች የሚ​ሰ​ማ​ሩ​በት ስፍራ የለ​ምና፤ ራብም በከ​ነ​ዓን ምድር እጅግ ጸን​ቶ​አ​ልና፤ አሁ​ንም አገ​ል​ጋ​ዮ​ችህ በጌ​ሤም ምድር እን​ቀ​መጥ።”

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 ደግሞም፣ “በከነዓን ምድር ራቡ እጅግ የጸና በመሆኑ በጎችና ፍየሎች የሚሰማሩበት በማጣታቸው፣ ለጊዜው እዚህ ለመኖር መጥተናል፤ አሁንም ባሮችህ በጌሤም ምድር እንድንኖር እንድትፈቅድልን እንለምንሃለን” አሉት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 “በምድር ልንቀመጥ በእንግድነት መጣን፥ ራብ በከነዓን ምድር እጅግ ጸንቶአልና፥ የአገልጋዮችህ በጎች የሚሰማሩበት ስፍራ የለም፥ አሁንም አገልጋዮችህ በጌሤም ምድር እንድንቀመጥ እንለምንሃለን።” አሉት ፈርዖንን።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 በከነዓን ምድር ራብ እጅግ ከመበርታቱ የተነሣ ለእንስሶቻችን ግጦሽ ስላጣን ለጊዜው በዚህች አገር ለመኖር መጥተናል፤ ስለዚህ አገልጋዮችህ በጌሴም ምድር እንድንኖር ፍቀድልን።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 ፈርዖንንም እንዲህ አሉት፦ በምድር ልንቀመጥ በእንግድነት መጣን የባርያዎችህ በጎች የሚስማሩበት ስፍራ የለምና ራብ በከነዓን ምድር እጅግ ጸንቶቸልና አሁንም ባርያዎችህ በጌሤም ምድር እንድንቀመጥ እንለምንሃለን።

Ver Capítulo Copiar




ዘፍጥረት 47:4
11 Referencias Cruzadas  

በም​ድ​ርም ራብ ሆነ፤ አብ​ራ​ምም በዚያ በእ​ን​ግ​ድ​ነት ይቀ​መጥ ዘንድ ወደ ግብፅ ወረደ፤ በም​ድር ራብ ጠንቶ ነበ​ረና።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አብ​ራ​ምን አለው፥ “ዘርህ ለእ​ነ​ርሱ ባል​ሆ​ነች ምድር ስደ​ተ​ኞች እን​ዲ​ሆኑ በእ​ር​ግጥ ዕወቅ፤ አራት መቶ ዓመ​ታ​ትም ባሪ​ያ​ዎች አድ​ር​ገው ይገ​ዙ​አ​ቸ​ዋል፤ ያሠ​ቃ​ዩ​አ​ቸ​ዋል፤ ያስ​ጨ​ን​ቋ​ቸ​ዋ​ልም።


ከዚ​ህም በኋላ ራብ በሀ​ገር ላይ ጸና።


በዐ​ረብ በኩል በጌ​ሤም ምድ​ርም ትቀ​መ​ጣ​ለህ፤ ወደ እኔም ትቀ​ር​ባ​ለህ። አን​ተና ልጆ​ችህ የል​ጆ​ች​ህም ልጆች፥ በጎ​ች​ህና ላሞ​ችህ፥ የአ​ንተ የሆ​ነው ሁሉ፥


በግ ጠባቂ ሁሉ ለግ​ብፅ ሰዎች ርኩስ ነውና በዐ​ረብ በኩል በጌ​ሤም እን​ድ​ት​ቀ​መጡ እኛ አገ​ል​ጋ​ዮ​ችህ ከብ​ላ​ቴ​ን​ነ​ታ​ችን ጀም​ረን እስከ አሁን ድረስ እኛም አባ​ቶ​ቻ​ች​ንም እን​ስሳ አር​ቢ​ዎች ነን” በሉት።


ፈር​ዖ​ንም ዮሴ​ፍን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፥ “አባ​ት​ህና ወን​ድ​ሞ​ችህ መጥ​ተ​ው​ል​ሃል፤ እነሆ፥ የግ​ብፅ ምድር በፊ​ትህ ናት፤


እን​ዳ​ያ​ጠ​ፋ​ቸው የቍ​ጣ​ውን መቅ​ሠ​ፍት ይመ​ልስ ዘንድ የተ​መ​ረ​ጠው ሙሴ በመ​ቅ​ሠ​ፍት ጊዜ በፊቱ ባይ​ቆም ኖሮ፥ ባጠ​ፋ​ቸው ነበር አለ።


ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ሕዝቤ አስ​ቀ​ድሞ ወደ ግብፅ ወረዱ፤ በዚ​ያም በስ​ደት ኖሩ፤ ከዚ​ያም ወደ አሦር በግድ ተወ​ሰዱ።


በግ​ብ​ፅና በከ​ነ​ዓን ሀገር ሁሉ ረኃ​ብና ታላቅ ጭንቅ መጣ፤ አባ​ቶ​ቻ​ች​ንም የሚ​በ​ሉት አጡ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እን​ዲህ አለው፦ ‘ዘርህ በባ​ዕድ ሀገር መጻ​ተ​ኞች ሆነው ይኖ​ራሉ፤ አራት መቶ ዓመ​ትም ባሮች አድ​ር​ገው ይገ​ዙ​አ​ቸ​ዋል፤ መከ​ራም ያጸ​ኑ​ባ​ቸ​ዋል።


በአ​ም​ላ​ክ​ህም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት እን​ዲህ ብለህ ተና​ገር፦ አባቴ ከሶ​ርያ ወጥቶ ወደ ግብፅ ወረደ፤ በዚ​ያም በቍ​ጥር ጥቂት ሆኖ ኖረ፤ በዚ​ያም ታላ​ቅና የበ​ረታ፥ ብዙም ሕዝብ ሆነ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos