የባቢሎንም ንጉሥ ሰባት ሺህ ያህል፥ ብርቱዎችንና ሰልፍ የሚችሉትን ሁሉ፥ ኀያላኑን ሁሉ አንድ ሺህ የሚሆኑ ጠራቢዎችንና ብረት ሠራተኞችንም ወደ ባቢሎን ማረከ።
2 ነገሥት 24:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኢየሩሳሌምንም አጠፋት፥ አለቆቹንም ሁሉ፥ ጽኑዓኑንና ኀያላኑን ሁሉ፥ ጠራቢዎቹንም ሁሉ፥ ብረት ሠራተኞቹንም ሁሉ ዐሥር ሺህ ምርኮኞችን ሁሉ አፈለሰ፤ ከሀገሩ ድሆች በቀር ማንም አልቀረም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ደግሞም የኢየሩሳሌምን ሕዝብ እንዳለ የጦር አለቆቹንና ተዋጊዎቹን በሙሉ፣ የእጅ ጥበብ ባለሙያዎችና ቀጥቃጮችን ሁሉ ጨምሮ በአጠቃላይ ዐሥር ሺሕ ሰው በምርኮ ወደ አገሩ ወሰደ። በዚያ የቀሩት የመጨረሻዎቹ ያገሪቱ ድኾች ብቻ ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ናቡከደነፆር የኢየሩሳሌምን ሕዝብ፥ ልዑላን መሳፍንቱን ሁሉና ሌሎችንም ታላላቅ ሰዎችን ጭምር በድምሩ ዐሥር ሺህ ሰዎች ማርኮ ወሰደ፤ ከእነርሱም ጋር የእጅ ጥበብ ዐዋቂዎችንና የብረት አንጣሪዎችን ሁሉ ወሰደ፤ በይሁዳ እንዲቀሩ ያደረገው የመጨረሻዎችን ድኾች ብቻ ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ናቡከደነፆር የኢየሩሳሌምን ሕዝብ፥ ልዑላን መሳፍንቱን ሁሉና ሌሎችንም ታላላቅ ሰዎችን ጭምር በድምሩ ዐሥር ሺህ ሰዎች ማርኮ ወሰደ፤ ከእነርሱም ጋር የእጅ ጥበብ ዐዋቂዎችንና የብረት አንጣሪዎችን ሁሉ ወሰደ፤ በይሁዳ እንዲቀሩ ያደረገው የመጨረሻዎችን ድኾች ብቻ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢየሩሳሌምንም ሁሉ፥ አለቆቹንም ሁሉ፥ ጽኑዓን ኀያላኑንም ሁሉ፥ ጠራቢዎቹንም ሁሉ፥ ብረት ሠራተኞቹን ሁሉ ዐሥር ሺህ ምርኮኞች አፈለሰ፤ ከድሆች ከአገሩ ሕዝብ በቀር ማንም አልቀረም። |
የባቢሎንም ንጉሥ ሰባት ሺህ ያህል፥ ብርቱዎችንና ሰልፍ የሚችሉትን ሁሉ፥ ኀያላኑን ሁሉ አንድ ሺህ የሚሆኑ ጠራቢዎችንና ብረት ሠራተኞችንም ወደ ባቢሎን ማረከ።
እስራኤልም ሁሉ ስለ ኀጢአታቸው ወደ ባቢሎን ከተማረኩ በኋላ፥ በየትውልዳቸው ተቈጠሩ፤ እነሆም በእስራኤልና በይሁዳ ነገሥታት መጽሐፍ ተጽፈዋል።
የባቢሎንም ንጉሥ ናቡከደነፆር ወደ ባቢሎን ከማረካቸው ምርኮኞች ወደ ኢየሩሳሌምና ወደ ይሁዳ፥ ወደ እየከተማቸው የተመለሱት የሀገር ልጆች እነዚህ ናቸው።
ከወንድሞች አንዱ ሐናኒ፥ ከእርሱም ጋር ሌሎች ሰዎች ከይሁዳ መጡ፤ እኔም የዳኑትን፥ ከምርኮም የተረፉትን የአይሁድን ነገር፥ የኢየሩሳሌምንም ነገር ጠየቅኋቸው።
“የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር የይሁዳን ንጉሥ የኢዮአቄምን ልጅ ኢኮንያንንና የይሁዳንና የኢየሩሳሌምን አለቆች ሁሉ ማርኮ ከኢየሩሳሌም ወደ ባቢሎን ባፈለሳቸው ጊዜ፥
ወደ ባቢሎንም የሄዱትን የይሁዳን ንጉሥ የኢዮአቄምን ልጅ ኢኮንያንንና የይሁዳን ምርኮ ሁሉ ወደዚች ስፍራ እመልሳቸዋለሁ፤ የባቢሎንን ንጉሥ ቀንበር እሰብራለሁና።”
ይህም የሆነው ንጉሡ ኢኮንያንና እቴጌዪቱ፥ ጃንደረቦቹም፥ የይሁዳና የኢየሩሳሌምም አለቆች ነጻዎችና እሥረኞች፥ ብልሃተኞችና ብረት ሠራተኞችም ከኢየሩሳሌም ከወጡ በኋላ ነው።
የአዛዦች አለቃ ናቡዛርዳን ግን አንዳች ከሌላቸው ከሕዝቡ ድሆች ከፊሎቹን በይሁዳ ሀገር ተዋቸው፤ የወይኑን ቦታና እርሻውንም በዚያ ጊዜ ሰጣቸው።
በየሜዳው የነበሩት የጭፍራ አለቆችና ሰዎቻቸው ሁሉ የባቢሎን ንጉሥ የአኪቃምን ልጅ ጎዶልያስን በሀገሩ ላይ እንደ ሾመ፥ ወንዶችንና ሴቶችን ልጆችንም፥ ወደ ባቢሎን ያልተማረኩትንም የምድርን ድሆች እንዳስጠበቀ በሰሙ ጊዜ፥
ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ታላቅ ክንፍ፥ ረጅምም ጽፍር ያለው፥ ላባንም የተሞላ፥ መልከ ዝንጉርጉር የሆነ ታላቅ ንስር ወደ ሊባኖስ መጣ፤ የዝግባንም ጫፍ ወሰደ።
እንግዲህ ትውልድ ሁሉ ከአብርሃም እስከ ዳዊት አሥራ አራት ትውልድ፥ ከዳዊትም እስከ ባቢሎን ምርኮ አሥራ አራት ትውልድ፥ ከባቢሎንም ምርኮ እስከ ክርስቶስ አሥራ አራት ትውልድ ነው።
“እግዚአብሔርም አንተን፥ በአንተም ላይ የምትሾማቸውን አለቆችህን አንተና አባቶችህ ወዳላወቃችኋቸው ሕዝብ ይወስድሃል፤ በዚያም ሌሎችን የእንጨትና የድንጋይ አማልክትን ታመልካለህ።
ፍልስጥኤማውያንም፥ “ዕብራውያን ሰይፍና ጦር እንዳይሠሩ” ብለው ነበርና በእስራኤል ምድር ሁሉ ብረት ሠሪ አልተገኘም።