Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




1 ዜና መዋዕል 9:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 እስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ ስለ ኀጢ​አ​ታ​ቸው ወደ ባቢ​ሎን ከተ​ማ​ረኩ በኋላ፥ በየ​ት​ው​ል​ዳ​ቸው ተቈ​ጠሩ፤ እነ​ሆም በእ​ስ​ራ​ኤ​ልና በይ​ሁዳ ነገ​ሥ​ታት መጽ​ሐፍ ተጽ​ፈ​ዋል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 እስራኤል ሁሉ በየትውልድ ሐረጋቸው ተቈጥረው ስማቸው በእስራኤል ነገሥታት መዝገብ ላይ ሰፈረ። የይሁዳ ሕዝብ ከፈጸሙት በደል የተነሣ ተማርከው ወደ ባቢሎን ተወሰዱ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 እስራኤልም ሁሉ በየትውልዳቸው ተቈጠሩ፤ እነሆም፥ በእስራኤል ነገሥታት መጽሐፍ ተጻፉ። ይሁዳም ስለ ኃጢአታቸው ወደ ባቢሎን ተማረኩ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 የእስራኤል ሕዝብ በየቤተሰቡ ተመዝግቦ ነበር፤ ይህም ታሪክ በእስራኤል ነገሥታት መጽሐፍ ሰፍሮ ይገኛል። የይሁዳ ሕዝብ በሠራው ኃጢአት ምክንያት በመቀጣት ተማርኮ ወደ ባቢሎን ተወስዶ ነበር፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 እስራኤልም ሁሉ በየትውልዳቸው ተቈጠሩ፤ እነሆም፥ በእስራኤል ነገሥታት መጽሐፍ ተጽፈዋል። ይሁዳም ስለ ኀጢአታቸው ወደ ባቢሎን ተማረኩ።

Ver Capítulo Copiar




1 ዜና መዋዕል 9:1
22 Referencias Cruzadas  

እነ​ዚህ በት​ው​ልድ መጽ​ሐፍ ትው​ል​ዳ​ቸ​ውን ፈለጉ፤ ነገር ግን አል​ተ​ገ​ኘም፤ ከክ​ህ​ነ​ትም ተከ​ለ​ከሉ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ታላ​ላ​ቆ​ቹ​ንና ሹሞ​ቹን፥ ሕዝ​ቡ​ንም ሰብ​ስቤ በየ​ት​ው​ል​ዳ​ቸው እቈ​ጥ​ራ​ቸው ዘንድ ልቤን አነ​ሣሣ፤ አስ​ቀ​ድ​መው የመ​ጡ​ት​ንም ሰዎች የት​ው​ልድ መጽ​ሐ​ፋ​ቸ​ውን አገ​ኘሁ፤ በእ​ር​ሱም እን​ደ​ዚህ ተጽፎ አገ​ኘሁ።


ከቲ​ል​ሜላ፥ ከቴ​ላ​ርሳ፥ ከክ​ሩብ፥ ከሐ​ዳን፥ ከኤ​ሜር የወጡ እነ​ዚህ ነበሩ፤ ነገር ግን የአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን ቤቶ​ችና ዘራ​ቸ​ውን ወይም ከእ​ስ​ራ​ኤል ወገን መሆ​ና​ቸ​ውን ያስ​ታ​ውቁ ዘንድ አል​ቻ​ሉም፤


የአ​ዛ​ዦች አለቃ ናቡ​ዛ​ር​ዳ​ንም በከ​ተ​ማ​ዪቱ የቀ​ሩ​ትን ሕዝብ፥ ኰብ​ል​ለ​ውም ወደ እርሱ የገ​ቡ​ትን ሰዎ​ችና የቀ​ረ​ው​ንም የሕ​ዝ​ቡን ቅሬታ ወደ ባቢ​ሎን ማረ​ካ​ቸው።


ስለ​ዚ​ህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የአ​ሦ​ርን ንጉሥ ሠራ​ዊት አለ​ቆች አመ​ጣ​ባ​ቸው፤ ምና​ሴ​ንም በዛ​ን​ጅር ያዙት፤ በሰ​ን​ሰ​ለ​ትም አስ​ረው ወደ ባቢ​ሎን ወሰ​ዱት።


የኡ​ላም ልጆች ጽኑ​ዓን ኀያ​ላ​ንና ቀስ​ተ​ኞች ነበሩ፤ ለእ​ነ​ር​ሱም መቶ አምሳ የሚ​ያ​ህሉ ብዙ ልጆ​ችና የልጅ ልጆች ነበ​ሩ​አ​ቸው፤ እነ​ዚህ ሁሉ የብ​ን​ያም ልጆች ነበሩ።


የቀ​ረ​ውም የኢ​ዮ​ር​ብ​ዓም ነገር፥ እን​ዴት እንደ ተዋጋ፥ እን​ዴ​ትም እንደ ነገሠ፥ እነሆ፥ በእ​ስ​ራ​ኤል ነገ​ሥ​ታት የታ​ሪክ መጽ​ሐፍ ተጽ​ፎ​አል።


ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ም​ንም አጠ​ፋት፥ አለ​ቆ​ቹ​ንም ሁሉ፥ ጽኑ​ዓ​ኑ​ንና ኀያ​ላ​ኑን ሁሉ፥ ጠራ​ቢ​ዎ​ቹ​ንም ሁሉ፥ ብረት ሠራ​ተ​ኞ​ቹ​ንም ሁሉ ዐሥር ሺህ ምር​ኮ​ኞ​ችን ሁሉ አፈ​ለሰ፤ ከሀ​ገሩ ድሆች በቀር ማንም አል​ቀ​ረም።


ዮአ​ኪ​ን​ንም ወደ ባቢ​ሎን አፈ​ለሰ፤ የን​ጉ​ሡ​ንም እናት፥ የን​ጉ​ሡ​ንም ሚስ​ቶች፥ ጃን​ደ​ረ​ቦ​ቹ​ንም፥ የሀ​ገ​ሩ​ንም ታላ​ላ​ቆች ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ወደ ባቢ​ሎን ማረከ።


የባ​ቢ​ሎ​ንም ንጉሥ ሰባት ሺህ ያህል፥ ብር​ቱ​ዎ​ች​ንና ሰልፍ የሚ​ች​ሉ​ትን ሁሉ፥ ኀያ​ላ​ኑን ሁሉ አንድ ሺህ የሚ​ሆኑ ጠራ​ቢ​ዎ​ች​ንና ብረት ሠራ​ተ​ኞ​ች​ንም ወደ ባቢ​ሎን ማረከ።


የባ​ቢ​ሎ​ንም ንጉሥ ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር ወደ ባቢ​ሎን ከማ​ረ​ካ​ቸው ምር​ኮ​ኞች ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምና ወደ ይሁዳ፥ ወደ እየ​ከ​ተ​ማ​ቸው የተ​መ​ለ​ሱት የሀ​ገር ልጆች እነ​ዚህ ናቸው።


የሕ​ዝ​ቡም አለ​ቆች በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ተቀ​መጡ፤ ከቀ​ሩ​ትም ሕዝብ ከዐ​ሥሩ ክፍል አንዱ በቅ​ድ​ስ​ቲቱ ከተማ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም፥ ዘጠ​ኙም በሌ​ሎች ከተ​ሞች ይቀ​መጡ ዘንድ ዕጣ ተጣ​ጣሉ።


ኀያ​ሉ​ንም፥ ተዋ​ጊ​ው​ንም፥ ፈራ​ጁ​ንም፥ ነቢ​ዩ​ንም፥ ዐዋ​ቂ​ው​ንም፥ ሽማ​ግ​ሌ​ው​ንም፥


የደ​ቡብ ከተ​ሞች ተዘ​ግ​ተ​ዋል፤ የሚ​ከ​ፍ​ታ​ቸ​ውም የለም፤ ይሁዳ ሁሉ ተሰ​ድ​ዶ​አል፤ ፈጽ​ሞም ተሰ​ድ​ዶ​አል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios