ሀገሪቱም ሁላ በታላቅ ድምፅ አለቀሰች። ሕዝቡም ሁሉ በቄድሮን ወንዝ ተሻገሩ፤ ንጉሡም ደግሞ የቄድሮንን ወንዝ ተሻገረ፤ ንጉሡና ሕዝቡም ሁሉ ወደ ምድረ በዳ በሚወስደው መንገድ ተሻገሩ።
2 ነገሥት 23:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ንጉሡም የካህናቱን አለቃ ኬልቅያስን በሁለተኛውም መዓርግ ያሉትን ካህናት በረኞቹንም፥ ለበዓልና ለማምለኪያ ዐፀድ ለሰማይም ሠራዊት ሁሉ የተሠሩትን ዕቃዎች ሁሉ ከእግዚአብሔር መቅደስ ያወጡ ዘንድ አዘዛቸው፤ ከኢየሩሳሌምም ውጭ በቄድሮን ሜዳ አቃጠሉት፤ አመዱንም ወደ ቤቴል ወሰዱት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ንጉሡም ለበኣል፣ ለአሼራና ለሰማይ ከዋክብት ሰራዊት ሁሉ የተሠሩትን የመገልገያ ዕቃዎች በሙሉ፣ ከእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ እንዲያወጡ ሊቀ ካህናቱን ኬልቅያስን በሁለተኛ ማዕርግ ያሉትን ካህናትና የቤተ መቅደሱን በር ጠባቂዎች አዘዘ። ዕቃዎቹንም ከኢየሩሳሌም ውጭ በቄድሮን ሸለቆ ሜዳ ላይ አቃጠላቸው፤ ዐመዱንም ወደ ቤቴል ወሰደው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚህም በኋላ ኢዮስያስ ሊቀ ካህናቱን ሒልቅያን፥ ረዳቶቹ የሆኑትን ካህናትና የቤተ መቅደሱን መግቢያ በር ዘብ የሚጠብቁ ተረኞችን ጠርቶ ለበዓልና አሼራ ተብላ ለምትጠራው ሴት አምላክ፥ እንዲሁም ለከዋክብት ማምለኪያ ያገለግሉ የነበሩትን ዕቃዎች ሁሉ ከቤተ መቅደስ ያወጡ ዘንድ አዘዛቸው፤ ንጉሡም እነዚያን ዕቃዎች ሁሉ ከኢየሩሳሌም ውጪ ባለው በቄድሮን ሸለቆ በእሳት አቃጥሎ ዐመዱን ወደ ቤትኤል ወሰደው፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህም በኋላ ኢዮስያስ ሊቀ ካህናቱን ሒልቅያን፥ ረዳቶቹ የሆኑትን ካህናትና የቤተ መቅደሱን መግቢያ በር ዘብ የሚጠብቁ ተረኞችን ጠርቶ ለባዓልና አሼራ ተብላ ለምትጠራው ሴት አምላክ፥ እንዲሁም ለከዋክብት ማምለኪያ ያገለግሉ የነበሩትን ዕቃዎች ሁሉ ከቤተ መቅደስ ያወጡ ዘንድ አዘዛቸው፤ ንጉሡም እነዚያን ዕቃዎች ሁሉ ከኢየሩሳሌም ውጪ ባለው በቄድሮን ሸለቆ በእሳት አቃጥሎ ዐመዱን ወደ ቤትኤል ወሰደው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ንጉሡም የካህናቱን አለቃ ኬልቅያስን በሁለተኛውም መዓርግ ያሉትን ካህናትን በረኞቹንም ለባአልና ለማምለኪያ ዐፀድ ለሰማይም ሠራዊት ሁሉ የተሠሩትን ዕቃዎች ሁሉ ከእግዚአብሔር መቅደስ ያወጡ ዘንድ አዘዛቸው፤ ከኢየሩሳሌምም ውጭ በቄድሮን ሜዳ አቃጠላቸው፤ አመዱንም ወደ ቤቴል ወሰደው። |
ሀገሪቱም ሁላ በታላቅ ድምፅ አለቀሰች። ሕዝቡም ሁሉ በቄድሮን ወንዝ ተሻገሩ፤ ንጉሡም ደግሞ የቄድሮንን ወንዝ ተሻገረ፤ ንጉሡና ሕዝቡም ሁሉ ወደ ምድረ በዳ በሚወስደው መንገድ ተሻገሩ።
የማምለኪያ ዐፀድ ጣዖታትን ስለ ሠራች እናቱን ሐናን እቴጌ እንዳትሆን ሻራት፤ አሳም የማምለኪያ ዐፀዱን አስቈረጠው፥ በቄድሮንም ፈፋ አጠገብ በእሳት አቃጠለው።
በናባጥም ልጅ በኢዮርብዓም ኀጢአት መሄድ አልበቃውም፤ የሲዶናውያንንም ንጉሥ የኤያትባሔልን ልጅ ኤልዛቤልን አገባ፤ ሄዶም በዓልን አመለከ ሰገደለትም።
አሁንም ወደ እስራኤል ሁሉ ልከህ፥ አራት መቶ ሃምሳ ነቢያተ ሐሰትን፥ አራት መቶ የማምለኪያ ዐፀድ ነቢያትን ወደ እኔ ወደ ቀርሜሎስ ተራራ ሰብስብ” አለው።
የተሰጣቸውን ወይፈንም ወስደው አዘጋጁ፤ ከጥዋትም እስከ ቀትር ድረስ፥ “በዓል ሆይ፥ ስማን፥” እያሉ የበዓልን ስም ጠሩ። ድምፅም አልነበረም፤ የሚመልስም አልነበረም፤ የሠሩትንም መሠዊያ እያነከሱ ይዞሩ ነበር።
ኤልያስም ሕዝቡን፥ “የበዓልን ነቢያት ያዙ፤ ከእነርሱ አንድ ሰው እንኳን የሚያመልጥ አይኑር፤” አላቸው። ያዙአቸውም፤ ኤልያስም ወደ ቂሶን ወንዝ ወስዶ፥ በዚያ እየወጋ ጣላቸው።
እኔም ከእስራኤል ጕልበታቸውን ለበዓል ያላንበረከኩትን ሁሉ፥ በአፋቸውም ያልሳሙትን ሁሉ፥ ሰባት ሺህ ሰዎች ለእኔ አስቀራለሁ።”
በሣጥኑም ውስጥ የተገኘው ወርቅ ብዙ እንደ ሆነ ባዩ ጊዜ የንጉሡ ጸሓፊና የካህናቱ አለቃ ይመጡ ነበር፤ በእግዚአብሔርም ቤት የተገኘውን ገንዘብ ሁሉ ቈጥረው በከረጢት ውስጥ ያኖሩት ነበር።
የአምላካቸውንም የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ሁሉ ተዉ፤ ቀልጠው የተሠሩትንም የሁለቱን እንቦሶች ምስሎች አደረጉ፤ የማምለኪያ ዐፀድንም ተከሉ፤ ለሰማይም ሠራዊት ሁሉ ሰገዱ፤ በዓልንም አመለኩ።
አባቱም ሕዝቅያስ ያፈረሳቸውን የኮረብታውን መስገጃዎች መልሶ ሠራ፤ የእስራኤልም ንጉሥ አክዓብ እንዳደረገው ለበዓል መሠዊያን ሠራ፤ የማምለኪያ ዐፀድንም ተከለ፤ ለሰማይም ሠራዊት ሁሉ ሰገደ አመለካቸውም።
እግዚአብሔርም ለዳዊትና ለልጁ ለሰሎሞን፥ “በዚህ ቤት ከእስራኤልም ነገድ ሁሉ በመረጥኋት በኢየሩሳሌም ስሜን ለዘለዓለም አኖራለሁ፤
“ወደ ታላቁ ካህን ወደ ኬልቅዩ ወጥተህ ደጃፉን የሚጠብቁ ከሕዝቡ የሰበሰቡትን ወደ እግዚአብሔር ቤት የገባውን ወርቅ ቍጠር።
የይሁዳም ነገሥታት ያሠሩትን በአካዝ ቤት ሰገነት ላይ የነበሩትን መሠዊያዎች፥ ምናሴም ያሠራውን በእግዚአብሔር ቤት በሁለቱ ወለሎች ላይ የነበሩትን መሠዊያዎች ንጉሡ አስፈረሳቸው፤ ከዚያም አወረዳቸው፤ አደቀቃቸውም፥ ትቢያቸውንም በቄድሮን ፈፋ ጣለ።
ደግሞም በቤቴል ኮረብታ የነበረውን መሠዊያ፥ እስራኤልንም ያሳተ የናባጥ ልጅ ኢዮርብዓም ያሠራውን የኮረብታውን መስገጃ፥ ይህንም መሠዊያና መስገጃ አፈረሰ፤ ድንጋዮቹንም ሰባበረ፤ አድቅቆም ትቢያ አደረገው፤ የማምለኪያ ዐፀዱንም አቃጠለው።
ንጉሡም አሳ እናቱን መዓካን ለአስጣርቴስ ስለ ሰገደች ከእቴጌነቷ አወረዳት፤ አሳም ምስሉን ቈርጦ ቀጠቀጠው፤ በቄድሮንም ወንዝ አጠገብ አቃጠለው።
አባቱም ሕዝቅያስ ያፈረሳቸውን የኮረብታ መስገጃዎች መልሶ ሠራ፤ ለበዓሊምም መሠዊያ ሠራ፤ የማምለኪያ ዐፀዶችንም ተከለ፤ ለሰማይም ሠራዊት ሁሉ ሰገደ፤ አመለካቸውም።
እግዚአብሔርም ለዳዊትና ለልጁ ለሰሎሞን፥ “በዚህ ቤትና ከእስራኤል ነገድ ሁሉ በመረጥኋት በኢየሩሳሌም ስሜን ለዘለዓለም አኖራለሁ፤
ስለዚህም የማምለኪያ ዐፀዶችና የፀሐይ ምስሎች ዳግመኛ እንዳይነሡ የመሠዊያውን ድንጋይ ሁሉ እንደ ደቀቀ እንደ ኖራ ድንጋይ ባደረገ ጊዜ ፥ እንዲሁ የያዕቆብ በደል ይሰረያል፤ ይህም ኀጢአትን የማስወገድ ፍሬ ሁሉ ነው።
ብትገድሉም፥ ብታመነዝሩም፥ ብትሰርቁም፥ በሐሰትም ብትምሉ፥ ለበአልም ብታጥኑ፥ የማታውቋቸውንም እንግዶች አማልክት ብትከተሉ ክፉ ያገኛችኋል።
እርሱም፥ “የሰው ልጅ ሆይ! የሚያደርጉትን ከመቅደሴ ያርቁኝ ዘንድ የእስራኤል ቤት በዚህ የሚያደርጉትን፥ ታላቁን ርኵሰት ታያለህን? ደግሞም ተመልሰህ ከዚህ የበለጠ ታላቅ ርኵሰት ታያለህ” አለኝ።
እስራኤል ሆይ! አንተ አላዋቂ አትሁን፤ አንተም ይሁዳ! ወደ ጌልጌላ አትሂድ፤ ወደ ቤትአዊንም አትውጡ፤ በሕያው እግዚአብሔርም አትማሉ።
“ወደ ቤቴል ገብታችሁ ኀጢአትን ሠራችሁ፤ በጌልገላም ኀጢአትን አበዛችሁ፤ በየማለዳውም መሥዋዕታችሁን፥ በየሦስተኛውም ቀን ዐሥራታችሁን አቀረባችሁ፤
ጌታችን ኢየሱስም ይህን ተናግሮ አትክልት ወደ አለበት ስፍራ ወደ ቄድሮስ ወንዝ ማዶ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ወጣ፤ ከደቀ መዛሙርቱም ጋር ወደዚያ ገባ።