Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




2 ነገሥት 21:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት በሁ​ለቱ ወለ​ሎች ላይ ለሰ​ማይ ሠራ​ዊት ሁሉ መሠ​ዊ​ያን ሠራ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 በሁለቱም የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ አደባባዮች ለሁሉም የሰማይ ከዋክብት ሰራዊት መሠዊያዎችን ሠራ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 በሁለቱም የቤተ መቅደሱ አደባባዮች የሰማይ ከዋክብት የሚመለኩባቸውን መሠዊያዎች ሠራ፤

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 በሁለቱም የቤተ መቅደሱ አደባባዮች የሰማይ ከዋክብት የሚመለኩባቸውን መሠዊያዎች ሠራ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 በእግዚአብሔርም ቤት በሁለቱ ወለሎች ላይ ለሰማይ ሠራዊት ሁሉ መሠዊያዎችን ሠራ።

Ver Capítulo Copiar




2 ነገሥት 21:5
17 Referencias Cruzadas  

የው​ስ​ጠ​ኛ​ው​ንም አደ​ባ​ባይ ቅጥር ሦስ​ቱን ተራ በተ​ጠ​ረበ ድን​ጋይ፥ አን​ዱ​ንም ተራ በዝ​ግባ ሣንቃ ሠራው፤ በመ​ቅ​ደሱ ፊት ለፊት ላለው ቤት ወለ​ልም መጋ​ረጃ ሠራ።


በታ​ላ​ቁም አደ​ባ​ባይ ዙሪያ የነ​በ​ረው ቅጥር እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት እንደ ውስ​ጠ​ኛው አደ​ባ​ባይ ቅጥ​ርና እንደ ቤቱ ወለል ሦስቱ ወገን በተ​ጠ​ረበ ድን​ጋይ አን​ዱም ወገን በዝ​ግባ ሳንቃ ተሠ​ርቶ ነበር።


የይ​ሁ​ዳም ነገ​ሥ​ታት ያሠ​ሩ​ትን በአ​ካዝ ቤት ሰገ​ነት ላይ የነ​በ​ሩ​ትን መሠ​ዊ​ያ​ዎች፥ ምና​ሴም ያሠ​ራ​ውን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት በሁ​ለቱ ወለ​ሎች ላይ የነ​በ​ሩ​ትን መሠ​ዊ​ያ​ዎች ንጉሡ አስ​ፈ​ረ​ሳ​ቸው፤ ከዚ​ያም አወ​ረ​ዳ​ቸው፤ አደ​ቀ​ቃ​ቸ​ውም፥ ትቢ​ያ​ቸ​ው​ንም በቄ​ድ​ሮን ፈፋ ጣለ።


ንጉ​ሡም የካ​ህ​ና​ቱን አለቃ ኬል​ቅ​ያ​ስን በሁ​ለ​ተ​ኛ​ውም መዓ​ርግ ያሉ​ትን ካህ​ናት በረ​ኞ​ቹ​ንም፥ ለበ​ዓ​ልና ለማ​ም​ለ​ኪያ ዐፀድ ለሰ​ማ​ይም ሠራ​ዊት ሁሉ የተ​ሠ​ሩ​ትን ዕቃ​ዎች ሁሉ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መቅ​ደስ ያወጡ ዘንድ አዘ​ዛ​ቸው፤ ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ውጭ በቄ​ድ​ሮን ሜዳ አቃ​ጠ​ሉት፤ አመ​ዱ​ንም ወደ ቤቴል ወሰ​ዱት።


የይ​ሁዳ ነገ​ሥ​ታ​ትም በይ​ሁዳ ከተ​ሞች በነ​በ​ሩት በኮ​ረ​ብ​ታው መስ​ገ​ጃ​ዎች፥ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ዙሪያ ባሉ መስ​ገ​ጃ​ዎች ያጥኑ ዘንድ ያኖ​ሩ​አ​ቸ​ውን የጣ​ዖ​ቱን ካህ​ናት፥ ለበ​ዓ​ልና ለፀ​ሐይ፥ ለጨ​ረ​ቃና ለከ​ዋ​ክ​ብት ለሰ​ማ​ይም ሠራ​ዊት ሁሉ ያጥኑ የነ​በ​ሩ​ትን አቃ​ጠ​ላ​ቸው።


የማ​ም​ለ​ኪያ ዐፀ​ድ​ንም ጣዖት ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ውጭ ወደ ቄድ​ሮን ፈፋ አወ​ጣው፤ በቄ​ድ​ሮ​ንም ፈፋ አጠ​ገብ አቃ​ጠ​ለው፤ አድ​ቅ​ቆም ትቢያ አደ​ረ​ገው፥ ትቢ​ያ​ው​ንም በሕ​ዝብ መቃ​ብር ላይ ጨመ​ረው።


በቃ​ልህ ትእ​ዛዝ ባሕ​ርን የገ​ሠ​ጽ​ሃት፥ ቀላ​ዮ​ችን የዘ​ጋህ፥ የሚ​ያ​ስ​ፈ​ራ​ው​ንም የወ​ሰ​ንህ፥


በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት በሁ​ለቱ አደ​ባ​ባ​ዮች ላይ ለሰ​ማይ ሠራ​ዊት ሁሉ መሠ​ዊ​ያ​ዎ​ችን ሠራ።


ደግ​ሞም የካ​ህ​ና​ቱን አደ​ባ​ባይ ፥ ታላ​ቁ​ንም አደ​ባ​ባይ፥ የአ​ደ​ባ​ባ​ዩ​ንም ደጆች ሠራ፤ ደጆ​ቻ​ቸ​ው​ንም በናስ ለበጠ።


በደ​ቡ​ብም በር በኩል ወደ ውስ​ጠ​ኛው አደ​ባ​ባይ አገ​ባኝ፤ እን​ደ​ዚ​ያ​ውም መጠን አድ​ርጎ የደ​ቡ​ብን በር ለካ፤


በው​ስ​ጠ​ኛ​ውም አደ​ባ​ባይ በም​ሥ​ራቅ በኩል አገ​ባኝ፤ በሩ​ንም ለካ፤ መጠ​ኑም እንደ እነ​ዚያ ነበረ።


የግ​ን​ቡም አዕ​ማድ ወደ ውጭው አደ​ባ​ባይ ይመ​ለ​ከቱ ነበር፤ በግ​ን​ቡም አዕ​ማድ ላይ በዚ​ህና በዚያ ወገን የዘ​ን​ባባ ዛፍ ተቀ​ርጾ ነበር፤ ወደ እር​ሱም የሚ​ያ​ወጡ ስም​ንት ደረ​ጃ​ዎች ነበ​ሩት።


አደ​ባ​ባ​ዩ​ንም በአ​ራት ማዕ​ዘኑ ርዝ​መ​ቱን መቶ ክንድ፥ ወር​ዱ​ንም መቶ ክንድ አድ​ርጎ ለካ፤ መሠ​ዊ​ያ​ውም በቤቱ ፊት ነበረ።


በው​ስ​ጠ​ኛ​ውም አደ​ባ​ባይ በሃ​ያው ክንድ አን​ጻር፥ በው​ጭ​ውም አደ​ባ​ባይ በወ​ለሉ አን​ጻር በሦ​ስት ደርብ በት​ይዩ የተ​ሠራ መተ​ላ​ለ​ፊያ ነበረ።


መን​ፈ​ስም አነ​ሣኝ፤ ወደ ውስ​ጠ​ኛ​ውም አደ​ባ​ባይ አገ​ባኝ፤ እነ​ሆም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ክብር መቅ​ደ​ሱን መል​ቶት ነበር።


ወደ ውጭ​ውም አደ​ባ​ባይ ወደ ሕዝብ በወጡ ጊዜ ያገ​ለ​ገ​ሉ​በ​ትን ልብ​ሳ​ቸ​ውን ያው​ልቁ፤ በተ​ቀ​ደ​ሰ​ውም ዕቃ ቤት ውስጥ ያኑ​ሩት፤ ሕዝ​ቡ​ንም በል​ብ​ሳ​ቸው እን​ዳ​ይ​ቀ​ድሱ ሌላ​ውን ልብስ ይል​በሱ።


ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ወደ ውስ​ጠ​ኛው አደ​ባ​ባይ አመ​ጣኝ፤ እነ​ሆም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መቅ​ደስ መግ​ቢያ ፊት በወ​ለ​ሉና በመ​ሠ​ዊ​ያው መካ​ከል ሃያ አም​ስት የሚ​ያ​ህሉ ሰዎች ነበሩ፤ ጀር​ባ​ቸ​ውም ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መቅ​ደስ፥ ፊታ​ቸ​ውም ወደ ምሥ​ራቅ ነበረ፤ እነ​ር​ሱም ወደ ምሥ​ራቅ ለፀ​ሐይ ይሰ​ግዱ ነበር።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos