Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




1 ነገሥት 18:26 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

26 የተ​ሰ​ጣ​ቸ​ውን ወይ​ፈ​ንም ወስ​ደው አዘ​ጋጁ፤ ከጥ​ዋ​ትም እስከ ቀትር ድረስ፥ “በዓል ሆይ፥ ስማን፥” እያሉ የበ​ዓ​ልን ስም ጠሩ። ድም​ፅም አል​ነ​በ​ረም፤ የሚ​መ​ል​ስም አል​ነ​በ​ረም፤ የሠ​ሩ​ት​ንም መሠ​ዊያ እያ​ነ​ከሱ ይዞሩ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

26 ስለዚህ የተሰጣቸውን ወይፈን ወስደው አዘጋጁት። ከዚያም ከጧት እስከ እኩለ ቀን የበኣልን ስም ጠሩ፤ “በኣል ሆይ ስማን” እያሉ ጮኹ፤ ድምፅ ግን የለም፤ የሚመልስ አልነበረም፤ በሠሩት መሠዊያ ዙሪያም እየዘለሉ ያሸበሽቡ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

26 እነርሱም የመጣላቸውን ኰርማ ወስደው ለመሥዋዕት አዘጋጅተው እስከ እኩለ ቀን ድረስ ወደ ባዓል ጸለዩ። “ባዓል ሆይ! እባክህ ስማን!” እያሉም ጮኹ። በሠሩትም መሠዊያ እየዘለሉ ዞሩ፤ ነገር ግን ምንም መልስ አላገኙም።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

26 እነርሱም የመጣላቸውን ኰርማ ወስደው ለመሥዋዕት አዘጋጅተው እስከ እኩለ ቀን ድረስ ወደ ባዓል ጸለዩ። “ባዓል ሆይ! እባክህ ስማን!” እያሉም ጮኹ። በሠሩትም መሠዊያ እየዘለሉ ዞሩ፤ ነገር ግን ምንም መልስ አላገኙም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

26 ወይፈኑንም ወስደው አዘጋጁ፤ ከጥዋትም እስከ ቀትር ድረስ “በኣል ሆይ! ስማን፤” እያሉ የበኣልን ስም ጠሩ። ድምፅም አልነበረም፤ የሚመልስም አልነበረም፤ በሠሩትም መሠዊያ ዙሪያ እያነከሱ ያሸበሽቡ ነበር።

Ver Capítulo Copiar




1 ነገሥት 18:26
21 Referencias Cruzadas  

እና​ን​ተም የአ​ም​ላ​ካ​ች​ሁን ስም ጥሩ፤ እኔም የፈ​ጣ​ሪ​ዬን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ስም እጠ​ራ​ለሁ፤ ሰም​ቶም በእ​ሳት የሚ​መ​ልስ አም​ላክ፥ እርሱ አም​ላክ ይሁን።” ሕዝ​ቡም ሁሉ፥ “ይህ ነገር መል​ካም ነው” ብለው መለሱ።


ኤል​ያ​ስም የበ​ዓ​ልን ነቢ​ያት፥ “እና​ንተ ብዙ​ዎች ናች​ሁና አስ​ቀ​ድ​ማ​ችሁ አንድ ወይ​ፈን ምረ​ጡና አዘ​ጋጁ፤ የአ​ም​ላ​ካ​ች​ሁ​ንም ስም ጥሩ፤ በበ​ታ​ቹም እሳት አት​ጨ​ምሩ” አላ​ቸው።


በቀ​ት​ርም ጊዜ ቴስ​ብ​ያ​ዊው ኤል​ያስ፥ “አም​ላክ ነውና በታ​ላቅ ቃል ጩኹ፤ ምና​ል​ባት ይጫ​ወት ይሆ​ናል፥ ወይም አሳብ ይዞት ይሆ​ናል፥ ወይም ተኝቶ እንደ ሆነ መቀ​ስ​ቀስ ያስ​ፈ​ል​ገ​ዋል” እያለ ይዘ​ባ​በ​ት​ባ​ቸው ጀመር።


እንደ ክም​ርም አድ​ር​ገው ሰበ​ሰ​ቡ​አ​ቸው፤ ምድ​ርም ገማች።


በአ​ም​ላ​ኩም በና​ሳ​ራክ ቤት ሲሰ​ግድ ልጆቹ አድ​ራ​ሜ​ሌ​ክና ሳራ​ሳር በሰ​ይፍ ገደ​ሉት፤ ወደ አራ​ራ​ትም ሀገር ኰበ​ለሉ። ልጁም አስ​ራ​ዶን በእ​ርሱ ፋንታ ነገሠ።


የቀ​ረ​ው​ንም እን​ጨት ጣዖት አድ​ርጎ ምስል ይቀ​ር​ጽ​በ​ታል፤ በፊ​ቱም ተጐ​ን​ብሶ ይሰ​ግ​ዳል፤ ወደ እር​ሱም እየ​ጸ​ለየ፥ “አም​ላኬ ነህና አድ​ነኝ” ይላል።


እና​ንተ ከአ​ሕ​ዛብ ወገን ሆና​ችሁ ያመ​ለ​ጣ​ችሁ፥ ተሰ​ብ​ስ​ባ​ችሁ ኑ፤ በአ​ን​ድ​ነ​ትም ተማ​ከሩ፤ የተ​ቀ​ረ​ጸ​ውን የም​ስ​ላ​ቸ​ውን እን​ጨት የሚ​ሸ​ከ​ሙና ያድን ዘንድ ወደ​ማ​ይ​ችል አም​ላክ የሚ​ጸ​ልዩ ዕው​ቀት የላ​ቸ​ውም።


በጫ​ን​ቃ​ቸው ላይ ተሸ​ክ​መ​ውት ይሄ​ዳሉ፤ በስ​ፍ​ራ​ውም በአ​ኖ​ሩት ጊዜ በዚያ ይቆ​ማል፤ ከስ​ፍ​ራ​ውም ፈቀቅ አይ​ልም፤ ሰውም ወደ እርሱ ቢጮህ አይ​ሰ​ማ​ውም፤ ከክ​ፉም አያ​ድ​ነ​ውም።


እንደ ተቀ​ረጸ ብር ናቸው፤ እነ​ር​ሱም አይ​ና​ገ​ሩም፤ መራ​መ​ድም አይ​ቻ​ላ​ቸ​ው​ምና ይሸ​ከ​ሙ​አ​ቸ​ዋል። ክፉ መሥ​ራ​ትም አይ​ቻ​ላ​ቸ​ው​ምና፥ ደግ​ሞም መል​ካም ይሠሩ ዘንድ አይ​ች​ሉ​ምና አት​ፍ​ሩ​አ​ቸው።”


መር​ከ​በ​ኞ​ቹም ፈሩ፤ እያ​ን​ዳ​ን​ዱም ወደ አም​ላኩ ጮኸ፤ መር​ከ​ቢ​ቱም እን​ድ​ት​ቀ​ል​ል​ላ​ቸው በው​ስ​ጥዋ የነ​በ​ረ​ውን ዕቃ ወደ ባሕር ጣሉት፤ ዮናስ ግን ወደ መር​ከቡ ውስ​ጠ​ኛው ክፍል ወርዶ ነበር፥ ተኝ​ቶም ያን​ኳ​ርፍ ነበር።


የተቀረጸውን ምስል ሠሪው የቀረጸው ለምን ጥቅም ነው? ዲዳንም ጣዖት ይሠራ ዘንድ ሠሪው የታመነበቱ፥ ሐሰትን የሚያስተምር ቀልጦ የተሠራ ምን ይጠቅማል?


እንጨቱን፦ ንቃ፥ ዲዳውንም ድንጋይ፦ ተነሣ ለሚለው ወዮለት! በውኑ ይህ ያስተምራልን? እነሆ፥ በወርቅና በብር ተለብጦአል፥ ምንም እስትንፋስ የለበትም።


በዚያም ቀን በመድረኩ ላይ የሚዘልሉትን፥ የጌታቸውን ቤት ዓመፃንና ሽንገላን የሚሞሉትን እቀጣለሁ።


“አሕዛብም በመናገራቸው ብዛት እንዲሰሙ ይመስላቸዋልና ስትጸልዩ እንደ እነርሱ በከንቱ አትድገሙ።


ቀድ​ሞም እና​ንተ አሕ​ዛብ በነ​በ​ራ​ችሁ ጊዜ ዲዳ​ዎች ጣዖ​ታ​ትን ታመ​ልኩ እንደ ነበር፥ ጣዖ​ትም በማ​ም​ለክ ረክ​ሳ​ችሁ እንደ ነበር፥ ወደ ወሰ​ዱ​አ​ች​ሁም ትሄዱ እንደ ነበር ታው​ቃ​ላ​ችሁ።


ለጣ​ዖ​ታት የተ​ሠ​ዋ​ውን ስለ​መ​ብ​ላት ግን ጣዖት ሁሉ በዓ​ለም ከንቱ እን​ደ​ሆነ፥ ከአ​ንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በቀር ሌላ አም​ላክ እን​ደ​ሌለ እና​ው​ቃ​ለን።


በነ​ጋ​ውም የአ​ዛ​ጦን ሰዎች ማለዱ፤ ወደ ዳጎ​ንም ቤት ገቡ፤ እነ​ሆም፥ ዳጎን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታቦት ፊት በም​ድር ላይ በግ​ን​ባሩ ወድቆ አገ​ኙት፤ ዳጎ​ን​ንም አን​ሥ​ተው በስ​ፍ​ራው አቆ​ሙት።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos