Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




1 ነገሥት 18:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 አሁ​ንም ወደ እስ​ራ​ኤል ሁሉ ልከህ፥ አራት መቶ ሃምሳ ነቢ​ያተ ሐሰ​ትን፥ አራት መቶ የማ​ም​ለ​ኪያ ዐፀድ ነቢ​ያ​ትን ወደ እኔ ወደ ቀር​ሜ​ሎስ ተራራ ሰብ​ስብ” አለው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 አሁንም ሕዝቡ በቀርሜሎስ ተራራ እንዲገናኘኝ ለመላው እስራኤል ጥሪ አድርግ። ከኤልዛቤል ማእድ የሚቀለቡትን አራት መቶ ዐምሳውን የበኣል ነቢያት፣ አራት መቶውንም የአሼራ ነቢያት አምጣቸው።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 ይልቅስ አሁን እስራኤላውያንን ሁሉ እንዳገኛቸው በቀርሜሎስ ተራራ ሰብስብልኝ፤ በንግሥት ኤልዛቤል ማእድ የሚቀለቡትን አራት መቶ ኀምሳ የባዓል ነቢያትንና አራት መቶ የአሼራ ነቢያትን ጭምር ይዘህ ና።”

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 ይልቅስ አሁን እስራኤላውያንን ሁሉ እንዳገኛቸው በቀርሜሎስ ተራራ ሰብስብልኝ፤ በንግሥት ኤልዛቤል ማእድ የሚቀለቡትን አራት መቶ ኀምሳ የባዓል ነቢያትንና አራት መቶ የአሼራ ነቢያትን ጭምር ይዘህ ና።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 አሁንም ልከህ እስራኤልን ሁሉ፥ በኤልዛቤልም ማዕድ የሚበሉትን አራት መቶ አምሳ የበኣልን ነቢያት፥ አራት መቶም የማምለኪያ ዐፀድን ነቢያት ወደ እኔ ወደ ቀርሜሎስ ተራራ ሰብስብ፤” አለ።

Ver Capítulo Copiar




1 ነገሥት 18:19
23 Referencias Cruzadas  

የማ​ም​ለ​ኪያ ዐፀድ ጣዖ​ታ​ትን ስለ ሠራች እና​ቱን ሐናን እቴጌ እን​ዳ​ት​ሆን ሻራት፤ አሳም የማ​ም​ለ​ኪያ ዐፀ​ዱን አስ​ቈ​ረ​ጠው፥ በቄ​ድ​ሮ​ንም ፈፋ አጠ​ገብ በእ​ሳት አቃ​ጠ​ለው።


አክ​ዓ​ብም የማ​ም​ለ​ኪያ ዐፀ​ድን አሠራ፤ አክ​ዓ​ብም ሰው​ነቱ እን​ድ​ት​ጠፋ ከእ​ርሱ በፊት ከነ​በ​ሩት ከእ​ስ​ራ​ኤል ነገ​ሥ​ታት ሁሉ ይልቅ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሚ​ያ​ስ​ቈ​ጣ​ውን ነገር አበዛ።


አክ​ዓ​ብም ወደ እስ​ራ​ኤል ልጆች ሁሉ ልኮ ነቢ​ያ​ቱን ሁሉ ወደ ቀር​ሜ​ሎስ ተራራ ሰበ​ሰ​ባ​ቸው።


ኤል​ያ​ስም ሕዝ​ቡን አለ፥ “ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነቢ​ያት አንድ እኔ ብቻ ቀር​ቻ​ለሁ፤ የበ​ዓል ነቢ​ያት ግን አራት መቶ ሃምሳ ሰዎች ናቸው። የማ​ም​ለ​ኪያ ዐፀድ ነቢ​ያ​ትም አራት መቶ ናቸው።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ ነቢ​ያ​ቱን አራት መቶ የሚ​ያ​ህ​ሉ​ትን ሰዎች ሰበ​ሰበ፤ የእ​ስ​ራ​ኤል ንጉ​ሥም፥ “ወደ ሬማት ዘገ​ለ​ዓድ ለሰ​ልፍ ልሂ​ድን? ወይስ ልቅር?” አላ​ቸው። እነ​ር​ሱም፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በን​ጉሥ እጅ አሳ​ልፎ ይሰ​ጣ​ታ​ልና ውጣ” አሉት።


አሁ​ንም የበ​ዓ​ልን ነቢ​ያት ሁሉ፥ አገ​ል​ጋ​ዮ​ቹ​ንም ሁሉ፥ ካህ​ና​ቱ​ንም ሁሉ ወደ እኔ ጥሩ፤ ማንም እን​ዳ​ይ​ቀር፤ ለበ​ዓል ታላቅ መሥ​ዋ​ዕት አቀ​ር​ባ​ለሁ፤ የቀ​ረ​ውም ሁሉ በሕ​ይ​ወት አይ​ኖ​ርም” አላ​ቸው። ኢዩ ግን የበ​ዓ​ልን አገ​ል​ጋ​ዮች ያጠፋ ዘንድ በተ​ን​ኮል ይህን አደ​ረገ።


ነገር ግን በእ​ር​ስዋ ሄዱ እንጂ እስ​ራ​ኤ​ልን ካሳ​ተ​በት ከኢ​ዮ​ር​ብ​ዓም ቤት ኀጢ​አት አል​ራ​ቁም፤ ደግ​ሞም የማ​ም​ለ​ኪያ ዐፀድ በሰ​ማ​ርያ ቆሞ ነበረ።


ከዚ​ያም ወደ ቀር​ሜ​ሎስ ተራራ ሄደ፤ ከዚ​ያም ወደ ሰማ​ርያ ተመ​ለሰ።


ኤል​ሳ​ዕም የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ንጉሥ፥ “እኔ ከአ​ንተ ጋር ምን አለኝ? ወደ አባ​ትህ ነቢ​ያ​ትና ወደ እና​ትህ ነቢ​ያት ሂድ፥” አለው። የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ፥ “አይ​ደ​ለም፤ በሞ​ዓብ እጅ ይጥ​ላ​ቸው ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እነ​ዚ​ህን ሦስት ነገ​ሥ​ታት ጠር​ቶ​አ​ልን?” አለው።


ኢዮ​ራ​ምም ኢዩን ባየ ጊዜ “ኢዩ ሆይ፥ ሰላም ነውን?” አለ። እር​ሱም፥ “የእ​ና​ትህ የኤ​ል​ዛ​ቤል ግል​ሙ​ት​ና​ዋና መተቷ ሲበዛ ምን ሰላም አለ?” ብሎ መለሰ።


ደግ​ሞም በዙ​ሪ​ያ​ችን ካሉት አሕ​ዛብ ወደ እኛ ከመ​ጡት ሌላ ከአ​ይ​ሁ​ድና ከሹ​ሞቹ መቶ አምሳ ሰዎች በገ​በ​ታዬ ነበሩ።


በራ​ስሽ ላይ ያለው ጠጕ​ርሽ እንደ ቀር​ሜ​ሎስ ተራራ ነው፤ የጠ​ጕ​ር​ሽም ሹርባ እንደ ሐም​ራዊ ሐር ነው፥ ንጉ​ሡም በሹ​ር​ባው ታስ​ሯል።


በበ​ዓል ትን​ቢት የተ​ና​ገ​ሩ​በ​ትን የሰ​ማ​ር​ያን ነቢ​ያት ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ውን አይ​ቻ​ለሁ፤ ሕዝ​ቤን እስ​ራ​ኤ​ል​ንም አሳ​ት​ዋ​ቸው።


እኔ ሕያው ነኝና በተ​ራ​ሮች መካ​ከል እን​ዳለ እንደ አጤ​ቤ​ር​ዮን፥ በባ​ሕ​ርም አጠ​ገብ እን​ዳለ እንደ ቀር​ሜ​ሎስ፥ እን​ዲሁ በእ​ው​ነት ይመ​ጣል፥ ይላል ስሙ የሠ​ራ​ዊት ጌታ የሆነ ንጉሥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


እን​ዲ​ህም አለ፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከጽ​ዮን ሆኖ ድም​ፁን ከፍ አድ​ርጎ ይና​ገ​ራል፤ ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ሆኖ ቃሉን ይሰ​ጣል፤ የእ​ረ​ኞ​ችም ማሰ​ማ​ሪ​ያ​ዎች ያለ​ቅ​ሳሉ፤ የቀ​ር​ሜ​ሎ​ስም ራስ ይደ​ር​ቃል።”


በቀ​ር​ሜ​ሎስ ራስ ውስጥ ቢሸ​ሸጉ ፈልጌ ከዚያ አወ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ በባ​ሕ​ሩም ጥልቅ ውስጥ ከዐ​ይኔ ቢደ​በቁ በዚያ እባ​ቡን አዝ​ዛ​ለሁ፤ እር​ሱም ይነ​ድ​ፋ​ቸ​ዋል፤


አሊ​ሜ​ሌክ፥ አሜ​ሕል፥ ማሕሳ ነበር፤ በባ​ሕ​ርም በኩል ወደ ቀር​ሜ​ሎስ፥ ወደ ሴዎ​ንና ሊበ​ናት ይደ​ር​ሳል፤


ነገር ግን ሐሰተኞች ነቢያት ደግሞ በሕዝቡ መካከል ነበሩ፤ እንዲሁም በመካከላችሁ ደግሞ ሐሰተኞች አስተማሪዎች ይሆናሉ፤ እነርሱም የዋጃቸውን ጌታ እንኳ ክደው የሚፈጥንን ጥፋት በራሳቸው ላይ እየሳቡ የሚያጠፋ ኑፋቄን አሹልከው ያገባሉ፤


አውሬውም ተያዘ፤ በእርሱም ፊት ተአምራትን እያደረገ የአውሬውን ምልክት የተቀበሉትን ለምስሉም የሰገዱትን ያሳተ ሐሰተኛው ነቢይ ከእርሱ ጋር ተያዘ፤ ሁለቱም በሕይወት ሳሉ በዲን ወደሚቃጠል ወደ እሳት ባሕር ተጣሉ።


ዳሩ ግን ‘ነቢይ ነኝ’ የምትለውን ባሪያዎቼንም እንዲሴስኑና ለጣዖት የታረደውን እንዲበሉ የምታስተምረውንና የምታስተውን ያችን ሴት ኤልዛቤልን ስለምትተዋት የምነቅፍብህ ነገር አለኝ፤


ሳሙ​ኤ​ልም እስ​ራ​ኤ​ልን ለመ​ገ​ና​ኘት በጥ​ዋት ገሥ​ግሦ ሄደ። ለሳ​ሙ​ኤ​ልም፥ “ሳኦል ወደ ቀር​ሜ​ሎስ መጣ፤ እነ​ሆም፥ ለራሱ የመ​ታ​ሰ​ቢያ ዐምድ አቆመ” ብለው ነገ​ሩት። ሳሙ​ኤ​ልም ሰረ​ገ​ላ​ውን መልሶ ወደ ጌል​ጌላ ወደ ሳኦል ወረደ፤ ከአ​ማ​ሌቅ ዘንድ ከአ​መ​ጣ​ውም ከአ​ማ​ረው ከም​ር​ኮው መንጋ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት ሲሠዋ አገ​ኘው፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos