2 ነገሥት 10:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከዚያም በሄደ ጊዜ የሬካብን ልጅ ኢዮናዳብን በመንገድ አገኘው፤ ተቀብሎም መረቀው፤ ኢዩም፥ “ልቤ ከልብህ ጋር ቅን እንደ ሆነ ያህል ልብህ ከልቤ ጋር በቅንነት ነውን?” አለው። ኢዮናዳብም፥ “አዎን” አለው። ኢዩም፥ “እውነትህስ ከሆነ እጅህን ስጠኝ” አለ። እጁንም ሰጠው፤ ወደ እርሱም ወደ ሰረገላው አወጣው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ተነሥቶ ሲሄድ የሬካብ ልጅ ኢዮናዳብ ወደ እርሱ ሲመጣ መንገድ ላይ አገኘው። ኢዩም ሰላምታ ሰጥቶት “ልቤ ለልብህ ታማኝ የሆነውን ያህል የአንተስ ልብ ለልቤ እንዲሁ ታማኝ ነውን?” ሲል ጠየቀው። ኢዮናዳብም፣ “አዎን፤ ነው!” ብሎ መለሰ። ኢዩም፣ “እንግዲያውስ እጅህን ስጠኝ” አለው። እጁንም ሰጠው፤ ከዚያም ኢዩ ደግፎ ወደ ሠረገላው አወጣው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኢዩ ተነሥቶ እንደገና ጉዞ ቀጠለ፤ በመንገድ ሳለም የሬካብን ልጅ ኢዮናዳብን አገኘ፤ ኢዩም ሰላምታ ከሰጠው በኋላ “እኔና አንተ በሐሳብ አንድ ነን፤ ታዲያ ከእኔ ጋር ትተባበራለህን?” ሲል ጠየቀው። ኢዮናዳብም “አዎ እተባበርሃለሁ” ሲል መለሰ። ኢዩም “እንግዲያውስ ጨብጠኝ” ሲል መለሰለት፤ እጅ ለእጅ ተያይዘው ኢዩ ደግፎት በሠረገላው ላይ አስቀመጠውና፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢዩ ተነሥቶ እንደገና ጒዞ ቀጠለ፤ በመንገድ ሳለም የሬካብን ልጅ ኢዮናዳብን አገኘ፤ ኢዩም ሰላምታ ከሰጠው በኋላ “እኔና አንተ በሐሳብ አንድ ነን፤ ታዲያ ከእኔ ጋር ትተባበራለህን?” ሲል ጠየቀው። ኢዮናዳብም “አዎ እተባበርሃለሁ” ሲል መለሰ። ኢዩም “እንግዲያውስ ጨብጠኝ” ሲል መለሰለት፤ እጅ ለእጅ ተያይዘው ኢዩ ደግፎት በሠረገላው ላይ አስቀመጠውና፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከዚያም በሄደ ጊዜ የሬካብን ልጅ ኢዮናዳብን ተገናኘው፤ ደኅንነቱንም ጠይቆ “ልቤ ከልብህ ጋር እንደ ሆነ ያህል ልብህ ከልቤ ጋር በቅንነት ነውን?” አለው፤ ኢዮናዳብም “እንዲሁ ነው፤” አለው። ኢዩም “እንዲሁ እንደ ሆነስ እጅህን ስጠኝ፤” አለ። እጁንም ሰጠው፤ ወደ ሠረገላውም አውጥቶ ከእርሱ ጋር አስቀመጠውና |
ኢዩ ከይሁዳ ንጉሥ ከአካዝያስ ወንድሞች ጋር ተገናኝቶ፥ “እናንተ እነማን ናችሁ?” አለ፤ እነርሱም፥ “እኛ የይሁዳ ንጉሥ የአካዝያስ ወንድሞች ነን፤ የንጉሡንና የእቴጌዪቱን ልጆች ደኅንነት እንነግረው ዘንድ ወረድን” አሉት።
እርሱም፥ “በሕይወታቸው ያዙአቸው” ብሎ አዘዘ። በበግ ጠባቂዎች ቤትም አጠገብ አርባ ሁለቱን ሰዎች ገደሉአቸው፤ ከእነርሱም አንድ ሰው እንኳ አላስቀረም።
ኢዮራምም፥ “ሰረገላ አዘጋጁ” አለ፤ ሰረገላውንም አዘጋጁለት። የእስራኤልም ንጉሥ ኢዮራምና የይሁዳ ንጉሥ አካዝያስ ሁለቱም በሰረገሎቻቸው ተቀምጠው ወጡ፤ ኢዩንም ሊገናኙት ሄዱ፤ በኢይዝራኤላዊውም በናቡቴ እርሻ ውስጥ አገኙት።
በያቤጽም የተቀመጡ የጸሓፊዎች ወገኖች፤ ቴርዓውያን፥ ሹማታውያን፥ ሡካታውያን ነበሩ፤ እነዚህ ከሬካብ ቤት አባት ከሐማት የወጡ ቄናውያን ናቸው።
የቤትሐካሪምም ግዛት ገዢ የሬካብ ልጅ መልክያ ከወንድሞቹና ከልጆቹ ጋር የጕድፍ መጣያውን በር ሠራ፤ ከደነው፤ ሳንቃዎቹንም አቆመ፤ ቍልፎቹንና መወርወሪያዎቹንም አደረገ።
“ወደ ሬካባውያን ቤት ሄደህ ተናገራቸው፤ ወደ እግዚአብሔርም ቤት አምጥተህ ከክፍሎቹ ወደ አንዲቱ አግባቸው፤ የወይን ጠጅም አጠጣቸው።”
ቃል ኪዳኑንም በማፍረስ መሐላውን ንቆአል፤ እነሆም እጁን አሳልፌ ሰጠሁ፤ ይህንም ሁሉ አድርጎአል፤ ስለዚህም አያመልጥም።
ጃንደረባውም፥ “ያስተማረኝ ሳይኖር በምን አውቀዋለሁ?” አለው፤ ወደ ሰረገላውም ወጥቶ አብሮት ይቀመጥ ዘንድ ፊልጶስን ለመነው።
የሰጠኝንም ጸጋ ዐውቀው አዕማድ የሚሏቸው ያዕቆብና ኬፋ፥ ዮሐንስም እኛ ወደ አሕዛብ፥ እነርሱም ወደ አይሁድ እንድንሄድ ለእኔና ለበርናባስ ቀኝ እጃቸውን ሰጡን።
ወንድሞቻችን ሆይ፥ እኔ ደግሞ እንደ እናንተ ሁኛለሁ፤ እንደ እኔ ሁኑ ብዬ እማልዳችኋለሁ፤ አንዳች አልበደላችሁኝምና።