Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ገላትያ 4:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ፥ እኔ ደግሞ እንደ እና​ንተ ሁኛ​ለሁ፤ እንደ እኔ ሁኑ ብዬ እማ​ል​ዳ​ች​ኋ​ለሁ፤ አን​ዳች አል​በ​ደ​ላ​ች​ሁ​ኝ​ምና።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 ወንድሞች ሆይ፤ እለምናችኋለሁ፤ እኔ እናንተን እንደ መሰልሁ፣ እናንተም እኔን ምሰሉ። እናንተ አንዳች አልበደላችሁኝም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 ወንድሞች ሆይ! እኔ እንደ እናንተ እንደሆንኩ “እንደ እኔ ሁኑ” ብዬ እለምናችኋለሁ። እናንተ አንዳችም አልበደላችሁኝም።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 ወንድሞች ሆይ! እኔ እንደ እናንተ ስለ ሆንኩ እናንተም እንደ እኔ ሁኑ ብዬ እለምናችኋለሁ፤ እናንተ ምንም አልበደላችሁኝም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 ወንድሞች ሆይ፥ እኔ ደግሞ እንደ እናንተ ሆኜአለሁና፦ እንደ እኔ ሁኑ ብዬ እለምናችኋለሁ። አንዳችም አልበደላችሁኝም።

Ver Capítulo Copiar




ገላትያ 4:12
13 Referencias Cruzadas  

ማንም ያሳ​ዘ​ነኝ ቢሆን፥ እኔን ብቻ ያሳ​ዘነ አይ​ደ​ለም። ከእ​ና​ንተ አንድ ሳይ​ቀር ሁላ​ች​ሁ​ንም አሳ​ዘነ እንጂ፤ አሁ​ንም ሥር​ዐት አላ​ጸ​ና​ባ​ች​ሁም።


የእ​ስ​ራ​ኤል ንጉ​ሥም ኢዮ​ሣ​ፍ​ጥን፥ “በሬ​ማት ዘገ​ለ​ዓድ እን​ዋጋ ዘንድ ከእኔ ጋር ትዘ​ም​ታ​ለ​ህን?” አለው። ኢዮ​ሣ​ፍ​ጥም ለእ​ስ​ራ​እል ንጉሥ፥ “እኔ እንደ አንተ፥ ሕዝ​ቤም እንደ ሕዝ​ብህ፥ ፈረ​ሶቼም እንደ ፈረ​ሶ​ችህ ናቸው” አለው።


እና​ን​ተም እንደ እኛ ወን​ዶ​ቻ​ች​ሁን ሁሉ ብት​ገ​ርዙ በዚህ ብቻ እን​መ​ስ​ላ​ች​ኋ​ለን፤ ከእ​ና​ን​ተም ጋር እን​ኖ​ራ​ለን፤


እኔ ግን በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ መስ​ቀል እንጂ በሌላ አል​መ​ካም፤ በእኔ ዘንድ ዓለሙ የሞተ ነው፥ እኔም በዓ​ለሙ ዘንድ የሞ​ትሁ ነኝ።


ነገር ግን ወደ እው​ነ​ተ​ኛው ወን​ጌል እግ​ራ​ቸ​ውን እን​ዳ​ላ​ቀኑ ባየሁ ጊዜ፥ በሰው ሁሉ ፊት ኬፋን እን​ዲህ አል​ሁት፥ “አንተ አይ​ሁ​ዳዊ ስት​ሆን በአ​ይ​ሁድ ሥር​ዐት ያይ​ደለ፥ በአ​ረ​ማ​ው​ያን ሥር​ዐት የም​ት​ኖር ከሆነ እን​ግ​ዲህ አይ​ሁድ እን​ዲ​ሆኑ አረ​ማ​ው​ያ​ንን ለምን ታስ​ገ​ድ​ዳ​ቸ​ዋ​ለህ?”


ልጆች እንደ መሆ​ና​ችሁ፥ ይህን እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ ከእ​ና​ንተ ላይ ስለ​ሚ​ገ​ባኝ ብድ​ራቴ እና​ንተ ፍቅ​ራ​ች​ሁን አስ​ፉ​ልኝ።


ነገር ግን የማ​ይ​ሆ​ነ​ውን እን​ደ​ም​ታ​ስ​ተ​ምር፥ የሙ​ሴ​ንም ሕግ እን​ደ​ም​ታ​ስ​ተ​ዋ​ቸው፥ በአ​ሕ​ዛብ መካ​ከል ያሉ ያመኑ አይ​ሁ​ድ​ንም ልጆ​ቻ​ቸ​ውን እን​ዳ​ይ​ገ​ርዙ፥ የኦ​ሪ​ት​ንም ሕግ እን​ዳ​ይ​ፈ​ጽሙ እን​ደ​ም​ት​ከ​ለ​ክ​ላ​ቸው ስለ አንተ ነግ​ረ​ዋ​ቸ​ዋል።


ወን​ድ​ሞች ሆይ፥ የጌ​ታ​ችን የኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ጸጋ ከእ​ና​ንተ ጋር ይሁን፤ አሜን። በሮሜ ተጽፋ በቲቶ እጅ ወደ ገላ​ትያ ሰዎች የተ​ላ​ከች መል​እ​ክት ተፈ​ጸ​መች። ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምስ​ጋና ይሁን፤ አሜን።


የቆ​ሮ​ን​ቶስ ሰዎች ሆይ፥ ለእ​ና​ንተ አፋ​ችን የተ​ከ​ፈተ ነው፤ ልባ​ች​ንም የሰፋ ነው።


ስለ እና​ንተ በከ​ንቱ ደክሜ እንደ ሆነ ብዬ እፈ​ራ​ች​ኋ​ለሁ።


መጀ​መ​ሪያ ወን​ጌ​ልን በሰ​በ​ክ​ሁ​ላ​ችሁ ጊዜ፥ ከሥጋ ድካም የተ​ነሣ እንደ ነበር ታው​ቃ​ላ​ችሁ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios