Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




1 ዜና መዋዕል 2:55 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

55 በያ​ቤ​ጽም የተ​ቀ​መጡ የጸ​ሓ​ፊ​ዎች ወገ​ኖች፤ ቴር​ዓ​ው​ያን፥ ሹማ​ታ​ው​ያን፥ ሡካ​ታ​ው​ያን ነበሩ፤ እነ​ዚህ ከሬ​ካብ ቤት አባት ከሐ​ማት የወጡ ቄና​ው​ያን ናቸው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

55 በያቤጽ የሚኖሩ የጸሐፍት ጐሣዎች ቲርዓውያን፣ ሺምዓታውያን፣ ሡካታውያን። እነዚህ ከሬካብ ቤት አባት ከሐማት የመጡ ቄናውያን ናቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

55 በያቤጽም የተቀመጡ የጸሐፊዎች ወገኖች፤ ቲርዓውያን፥ ሺምዓታውያን፥ ሡካታውያን ነበሩ፤ እነዚህ ከሬካብ ቤት አባት ከሐማት የወጡ ቄናውያን ናቸው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

55 ቲርዓውያን፥ ሺምዓውያንና ሱካውያን የተባሉት ታሪክ በመጻፍና በመገልበጥ ጥበበኞች የነበሩት ጐሣዎች ያዕቤጽ ተብላ በምትጠራ ትንሽ ከተማ ይኖሩ ነበር፤ እነርሱም ከሬካባውያን አባት ከሐሜት የወጡ ቄናውያን ነበሩ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

55 በያቤጽም የተቀመጡ የጸሐፊዎች ወገኖች፤ ቲርዓውያን፥ ሺምዓታውያን፥ ሡካታውያን ነበሩ፤ እነዚህ ከሬካብ ቤት አባት ከሐማት የወጡ ቄናውያን ናቸው።

Ver Capítulo Copiar




1 ዜና መዋዕል 2:55
11 Referencias Cruzadas  

ከዚ​ያም በሄደ ጊዜ የሬ​ካ​ብን ልጅ ኢዮ​ና​ዳ​ብን በመ​ን​ገድ አገ​ኘው፤ ተቀ​ብ​ሎም መረ​ቀው፤ ኢዩም፥ “ልቤ ከል​ብህ ጋር ቅን እንደ ሆነ ያህል ልብህ ከልቤ ጋር በቅ​ን​ነት ነውን?” አለው። ኢዮ​ና​ዳ​ብም፥ “አዎን” አለው። ኢዩም፥ “እው​ነ​ት​ህስ ከሆነ እጅ​ህን ስጠኝ” አለ። እጁ​ንም ሰጠው፤ ወደ እር​ሱም ወደ ሰረ​ገ​ላው አወ​ጣው።


የሰ​ል​ሞ​ንም ልጆች ቤተ ልሔም፥ ነጦ​ፋ​ው​ያን፥ አጦ​ሮት ቤት​ዮ​አብ፥ የመ​ና​ሕ​ታ​ው​ያን እኩ​ሌታ፥ ሰራ​ዓ​ው​ያ​ንም ነበሩ።


በኬ​ብ​ሮን ለዳ​ዊት የተ​ወ​ለ​ዱ​ለት ልጆች እነ​ዚህ ናቸው። በኵሩ አም​ኖን ከኢ​ይ​ዝ​ራ​ኤ​ላ​ዊቱ ከአ​ኪ​ና​ሆም፥ ሁለ​ተ​ኛ​ውም ዶለ​ህያ ከቀ​ር​ሜ​ሎ​ሳ​ዊቱ ከአ​ቢ​ግያ፥


ይህም ዕዝራ ከባ​ቢ​ሎን ወጣ፤ እር​ሱም የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለሙሴ የሰ​ጠ​ውን ሕግ ዐዋቂ ነበረ፤ የአ​ም​ላ​ኩም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅ በእ​ርሱ ላይ ነበ​ረ​ችና ንጉሡ ያሻ​ውን ሁሉ ሰጠው።


ስለ​ዚህ በፊቴ የሚ​ቆም ሰው ከሬ​ካብ ልጅ ከኢ​ዮ​ና​ዳብ ወገን ለዘ​ለ​ዓ​ለም አይ​ታ​ጣም፥” ይላል የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


“እና​ን​ተስ፦ ጥበ​በ​ኞች ነን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሕግ ከእኛ ጋር ነው እን​ዴት ትላ​ላ​ችሁ? እነሆ ጸሓ​ፊ​ዎ​ቻ​ቸ​ውም ከንቱ ሆኑ፤ በሐ​ሰ​ትም ብርዕ ተጠ​ቀሙ።


የቄ​ና​ዊው የሙሴ አማት የዮ​ባብ ልጆ​ችም ከዘ​ን​ባባ ከተማ ተነ​ሥ​ተው ከዓ​ራድ በአ​ዜብ በኩል ወዳ​ለው ወደ ይሁዳ ምድረ በዳ ወደ ይሁዳ ልጆች ሄደው ከሕ​ዝቡ ጋር ተቀ​መጡ።


ቄና​ዊ​ውም ሔቤር ከሙሴ አማት ከኢ​ዮ​ባብ ልጆች ከቄ​ና​ው​ያን ተለ​ይቶ ድን​ኳ​ኑን በቃ​ዴስ አጠ​ገብ እስከ ነበ​ረው ታላቅ ዛፍ ድረስ ተከለ።


ሳኦ​ልም ቄኔ​ዎ​ና​ው​ያ​ንን፥ “ከእ​ነ​ርሱ ጋር እን​ዳ​ላ​ጠ​ፋ​ችሁ ከአ​ማ​ሌ​ቃ​ው​ያን መካ​ከል ተነ​ሥ​ታ​ችሁ ሂዱ፤ ከግ​ብፅ በወጡ ጊዜ ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ቸር​ነት አድ​ር​ጋ​ች​ኋ​ልና” አላ​ቸው። ቄኔ​ዎ​ና​ው​ያ​ንም ከአ​ማ​ሌ​ቃ​ው​ያን መካ​ከል ወጡ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos