ራእይ 5:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አዲስ መዝሙርም እንዲህ እያሉ ዘመሩ፦ “በደምህ ከየነገዱ፥ ከየቋንቋው፥ ከየወገኑ፥ ከየሕዝቡ ሰዎችን ለእግዚአብሔር ለመዋጀት፥ አንተ ስለ ታረድህ የብራናውን ጥቅል መጽሐፍ ለመውሰድና ማኅተሞቹን ለመክፈት የተገባህ ሆነሃል፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንዲህም እያሉ አዲስ መዝሙር ዘመሩ፤ “መጽሐፉን ልትወስድ፣ ማኅተሞቹንም ልትፈታ ይገባሃል፤ ምክንያቱም ታርደሃል፤ በደምህም ከነገድ ሁሉ፣ ከቋንቋ ሁሉ፣ ከወገን ሁሉ፣ ከሕዝብ ሁሉ ሰዎችን ለእግዚአብሔር ዋጅተሃል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “መጽሐፉን ትወስድ ዘንድ ማኅተሞቹንም ትፈታ ዘንድ ይገባሃል ታርደሃልና፤ በደምህም ለእግዚአብሔር ከነገድ ሁሉ ከቋንቋም ሁሉ ከወገንም ሁሉ ከሕዝብም ሁሉ ሰዎችን ዋጅተህ፥ ለአምላካችን መንግሥትና ካህናት ይሆኑ ዘንድ አደረግሃቸው፤ በምድርም ላይ ይነግሣሉ፤” እያሉ አዲስን ቅኔ ይዘምራሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “መጽሐፉን ትወስድ ዘንድ ማኅተሞቹንም ትፈታ ዘንድ ይገባሃል ታርደሃልና፤ በደምህም ለእግዚአብሔር ከነገድ ሁሉ ከቋንቋም ሁሉ ከወገንም ሁሉ ከሕዝብም ሁሉ ሰዎችን ዋጅተህ፥ ለአምላካችን መንግሥትና ካህናት ይሆኑ ዘንድ አደረግሃቸው፤ በምድርም ላይ ይነግሣሉ፤” እያሉ አዲስን ቅኔ ይዘምራሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) መጽሐፉን ትወስድ ዘንድ ማኅተሞቹንም ትፈታ ዘንድ ይገባሃል፥ ታርደሃልና፥ በደምህም ለእግዚአብሔር ከነገድ ሁሉ ከቋንቋም ሁሉ ከወገንም ሁሉ ከሕዝብም ሁሉ ሰዎችን ዋጅተህ ለአምላካችን መንግሥትና ካህናት ይሆኑ ዘንድ አደረግሃቸው፥ በምድርም ላይ ይነግሣሉ እያሉ አዲስን ቅኔ ይዘምራሉ። |
ለእግዚአብሔር አዲስ መዝሙር ዘምሩ! የዓለም ሕዝቦች ሁሉ የምስጋና መዝሙር አቅርቡ! በባሕሩ ውስጥ ያሉት ሁሉ፥ የጠረፍ አገሮችና በእነርሱም የሚኖሩ ሁሉ ያመስግኑ!
በዚያን ጊዜ አንድ ዐዋጅ ነጋሪ ድምፁን ከፍ አድርጎ እንዲህ አለ፦ “እናንተ ከልዩ ልዩ ሀገር የመጣችሁ ሕዝቦችና ልዩ ልዩ ቋንቋ የምትናገሩ ነገዶች ሆይ!
ንጉሡ ናቡከደነፆር በዓለም ሁሉ ለሚኖሩ ሕዝቦችና ልዩ ልዩ ቋንቋ ለሚናገሩ ነገዶች የሚከተለውን መልእክት አስተላለፈ፦ “ሰላም ለእናንተ ይሁን!
ከገናናነቱም የተነሣ በልዩ ልዩ አገሮች የሚኖሩ ሕዝቦችና ልዩ ልዩ ቋንቋ የሚናገሩ ነገዶች ሁሉ በፊቱ በፍርሃት ይንቀጠቀጡ ነበር፤ የፈለገውን መግደልና የፈለገውን ማዳን፥ የፈለገውን መሾምና ያልፈለገውን መሻር ይችል ነበር።
ከዚህ በኋላ ንጉሥ ዳርዮስ በየአገሩ ለሚኖሩ ሕዝቦችና ልዩ ልዩ ቋንቋ ለሚናገሩ ነገዶች በጽሑፍ እንዲህ የሚል መልእክት አስተላለፈ፥ “ሰላም ለእናንተ ይሁን!
መንፈስ ቅዱስ እናንተን ኤጲስ ቆጶሳት አድርጎ ሾሞአችኋል፤ እንግዲህ ለራሳችሁና ለመንጋው ተጠንቀቁ፤ እግዚአብሔር በገዛ ልጁ ደም የዋጃትን ቤተ ክርስቲያን ጠብቁ።
ይህም የሚሆነው ተመሥርታችሁና ተደላድላችሁ በወንጌሉ ከተገኘው ተስፋ ሳትናወጡ በእምነት ጸንታችሁ ስትኖሩ ብቻ ነው፤ ይህም ወንጌል እናንተ የሰማችሁትና በዓለም ላይ ላሉት ሰዎች ሁሉ የተሰበከ ነው፤ እኔ ጳውሎስም አገልጋይ የሆንኩት ለዚሁ ወንጌል ነው።
ክርስቶስ ከዐመፃ ሁሉ ሊያድነንና መልካም ሥራ ለመሥራት ትጉሆችና ለእርሱ የተለየን ንጹሕ ሕዝብ እንድንሆን ያነጻን ዘንድ ስለ እኛ ራሱን አሳልፎ ሰጠ።
ነገር ግን በቀድሞ ዘመን በሕዝቡ መካከል ሐሰተኞች ነቢያት እንደ ነበሩ፥ እንዲሁም በእናንተ መካከል ሐሰተኞች መምህራን ይኖራሉ፤ እነርሱ ጥፋትን የሚያስከትል ሐሰተኛ ትምህርት በስውር እንዲሠራጭ ያደርጋሉ፤ የዋጃቸውንም ጌታ ክደው ፈጣን ጥፋትን በራሳቸው ላይ ያመጣሉ።
ነገር ግን እርሱ በብርሃን እንዳለ እኛም በብርሃን ብንኖር እርስ በርሳችን አንድነት ይኖረናል። ደግሞም የልጁ የኢየሱስ ደም ከኃጢአት ሁሉ ያነጻናል።
ከዚህ በኋላ “ስለ ብዙ ወገኖች፥ ሕዝቦች፥ ልዩ ልዩ ቋንቋ ስለሚናገሩ ሰዎችና ስለ ነገሥታት እንደ ገና ትንቢት መናገር አለብህ” ተብሎ ተነገረኝ።
ቅዱሳንን እንዲዋጋና ድል እንዲነሣቸው ሥልጣን ተሰጠው፤ በነገድና በወገን፥ በልዩ ልዩ ቋንቋዎች በሚናገሩና በሕዝብ ሁሉ ላይ ሥልጣን ተሰጠው።
ከዚህ በኋላ በምድር ላይ ለሚኖሩ ሕዝብ፥ ነገድ፥ ልዩ ልዩ ቋንቋዎችን ለሚናገሩና ለተለያዩ ወገኖች ሁሉ ለማብሠር ዘለዓለማዊውን ወንጌል የያዘ ሌላ መልአክ በሰማይ መካከል ሲበር አየሁ።
የእግዚአብሔርን አገልጋይ የሙሴን መዝሙርና የበጉን መዝሙር እንዲህ እያሉ ይዘምሩ ነበር፥ “ሁሉን የምትችል ጌታ አምላክ ሆይ! ሥራህ ታላቅና አስደናቂ ነው፤ የሕዝቦች ንጉሥ ሆይ! መንገድህ ትክክልና እውነት ነው፤
“ጌታችንና አምላካችን ሆይ፥ ሁሉን ነገር ስለ ፈጠርክ ሁሉም ነገር የተፈጠረውና የሚኖረው (ሕይወትን ያገኘው) በአንተ ፈቃድ ስለ ሆነ ገናናነት፥ ክብርና ኀይልም ለአንተ ይገባል” ይሉ ነበር።
ከዚህ በኋላ በዙፋኑና በአራቱ እንስሶች መካከል፥ በሽማግሌዎችም መካከል የታረደ የሚመስል በግ ቆሞ አየሁ፤ ይህ በግ ሰባት ቀንዶችና ሰባት ዐይኖች ነበሩት፤ እነርሱ ወደ ዓለም ሁሉ የተላኩ ሰባቱ የእግዚአብሔር መንፈሶች ናቸው።