Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




2 ጴጥሮስ 2:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 ነገር ግን በቀድሞ ዘመን በሕዝቡ መካከል ሐሰተኞች ነቢያት እንደ ነበሩ፥ እንዲሁም በእናንተ መካከል ሐሰተኞች መምህራን ይኖራሉ፤ እነርሱ ጥፋትን የሚያስከትል ሐሰተኛ ትምህርት በስውር እንዲሠራጭ ያደርጋሉ፤ የዋጃቸውንም ጌታ ክደው ፈጣን ጥፋትን በራሳቸው ላይ ያመጣሉ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 ነገር ግን ሐሰተኞች ነቢያት በሕዝቡ መካከል እንደ ነበሩ፣ እንዲሁም በእናንተ መካከል ሐሰተኞች መምህራን ይነሣሉ፤ እነርሱም የዋጃቸውን ጌታ እንኳ ክደው፣ ጥፋት የሚያስከትል የስሕተት ትምህርት በስውር ያስገባሉ፤ በዚህም በራሳቸው ላይ ድንገተኛ ጥፋት ያመጣሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 ነገር ግን ሐሰተኞች ነቢያት ደግሞ በሕዝቡ መካከል እንደ ነበሩ፤ እንዲሁም በመካከላችሁ ሐሰተኞች አስተማሪዎች ይኖራሉ፤ እነርሱም ጥፋትን የሚያስከትሉ ትምህርቶች አስርገው በማስገባት የዋጃቸውን ጌታ እንኳ ክደው፥ በራሳቸው ላይ ፈጣን ጥፋትን ያመጣሉ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 ነገር ግን ሐሰተኞች ነቢያት ደግሞ በሕዝቡ መካከል ነበሩ፤ እንዲሁም በመካከላችሁ ደግሞ ሐሰተኞች አስተማሪዎች ይሆናሉ፤ እነርሱም የዋጃቸውን ጌታ እንኳ ክደው የሚፈጥንን ጥፋት በራሳቸው ላይ እየሳቡ የሚያጠፋ ኑፋቄን አሹልከው ያገባሉ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 ነገር ግን ሐሰተኞች ነቢያት ደግሞ በሕዝቡ መካከል ነበሩ እንዲሁም በመካከላችሁ ደግሞ ሐሰተኞች አስተማሪዎች ይሆናሉ፤ እነርሱም የዋጃቸውን ጌታ እንኳ ክደው የሚፈጥንን ጥፋት በራሳቸው ላይ እየሳቡ የሚያጠፋ ኑፋቄን አሹልከው ያገባሉ፤

Ver Capítulo Copiar




2 ጴጥሮስ 2:1
73 Referencias Cruzadas  

“የበግ ለምድ ለብሰው ከሚመጡባችሁ፥ በውስጣቸው ግን እንደ ነጣቂ ተኲላዎች ከሆኑት ከሐሰተኞች ነቢያት ተጠንቀቁ፤


የሚፈረድባቸው መሆኑ ከብዙ ጊዜ በፊት የተጻፈባቸው አንዳንድ ሰዎች ወደ እናንተ ሾልከው ገብተዋል፤ እነርሱ የአምላካችንን ጸጋ በስድነት የሚለውጡ እግዚአብሔርን የማያመልኩ ናቸው፤ እርሱ ብቻ ገዢአችንና ጌታችን የሆነን ኢየሱስ ክርስቶስንም ይክዳሉ።


እነዚህ ሐሰተኞች መምህራን ለገንዘብ ከመስገብገባቸው የተነሣ ራሳቸው ያዘጋጁትን ታሪክ እያወሩ ይበዘብዙአችኋል። ከብዙ ዘመን በፊት ጀምሮ ፍርድ ተዘጋጅቶላቸዋል፤ ጥፋትም በእርግጥ ይጠብቃቸዋል!


ሰዎች ሕይወት የሚገኝበትን ትምህርት ለመስማት የማይፈልጉበት ጊዜ ይመጣል፤ ነገር ግን ለወሬ በመጐምጀት እነርሱ ራሳቸው የሚወዱትን ነገር የሚነግሩአቸውን አስተማሪዎች ይሰበስባሉ።


ብዙ ሐሰተኞች ነቢያት ይነሣሉ፤ ብዙዎችንም ያሳስታሉ፤


ነገር ግን በመካከላችን ሾልከው በስውር የገቡ አንዳንድ ሐሰተኞች ወንድሞች እንዲገረዝ ፈልገው ነበር፤ እነዚህ ሰዎች ለስለላ በመካከላችን ሠርገው የገቡት በኢየሱስ ክርስቶስ ያለንን ነጻነት ነጥቀው ወደ ባሪያነት ሊመልሱን አስበው ነው።


ትክክል የሆኑት እነማን እንደ ሆኑ ተለይተው እንዲታወቁ በመካከላችሁ መለያየት መኖሩ ግድ ነው።


ወዳጆች ሆይ! በዓለም ላይ ብዙ ሐሰተኞች ነቢያት ስለ ተነሡ መንፈስን ሁሉ አትመኑ፤ ይልቅስ መንፈሶች የእግዚአብሔር መሆናቸውንና አለመሆናቸውን መርምሩ።


በክርስቶስ ላይ የተመሠረተ ሳይሆን በሰው ሠራሽ ወግና በዓለማዊ ተራ ሥርዓት ላይ በተመሠረተ በፍልስፍናና በከንቱ ሽንገላ ማንም እንዳያጠምዳችሁ ተጠንቀቁ።


መለያየትን የሚያመጣውን ሰው አንድ ጊዜ ወይም ሁለት ጊዜ ከመከርከው በኋላ ከእርሱ ራቅ።


እነዚህን ሰዎች ዝም ማሰኘት ይገባል፤ እነርሱ በሚያሳፍር ትርፍ ለማግኘት የማይገባውን ነገር እያስተማሩ ቤተሰቦችን በሙሉ ያናውጣሉ።


የእነርሱ አምላክ ሆዳቸው ነው፤ አሳፋሪ የሆነ ነገር ለእነርሱ ክብራቸው ነው፤ ሐሳባቸውም የሚያተኲረው በምድራዊ ነገር ላይ ነው፤ ስለዚህ የእነርሱ መጨረሻ ጥፋት ነው።


እርሱ በዋጋ ገዝቶአችኋል፤ ስለዚህ በሰውነታችሁ እግዚአብሔርን አክብሩ።


ሐሰተኞች መሲሖችና ሐሰተኞች ነቢያት ይመጣሉ፤ እነርሱ ቢቻላቸውስ የተመረጡትን እንኳ ለማሳሳት ተአምራትና ድንቅ ነገሮችን ያደርጋሉ።


አዲስ መዝሙርም እንዲህ እያሉ ዘመሩ፦ “በደምህ ከየነገዱ፥ ከየቋንቋው፥ ከየወገኑ፥ ከየሕዝቡ ሰዎችን ለእግዚአብሔር ለመዋጀት፥ አንተ ስለ ታረድህ የብራናውን ጥቅል መጽሐፍ ለመውሰድና ማኅተሞቹን ለመክፈት የተገባህ ሆነሃል፤


መከራህንና ድኽነትህን ዐውቃለሁ፤ ይሁን እንጂ ሀብታም ነህ፤ አይሁድ ሳይሆኑ አይሁድ ነን የሚሉ፥ የሰይጣን ማኅበር የሆኑ፥ ስምህን እንዳጠፉት ዐውቃለሁ፤


ታዲያ፥ የእግዚአብሔርን ልጅ የናቀ፥ የተቀደሰበትን የቃል ኪዳን ደም ያረከሰ፥ የጸጋን መንፈስ የሰደበ፥ እንዴት ያለ የባሰ ቅጣት የሚገባው ይመስላችኋል!


በአጉል ትሕትናና መላእክትን በማምለክ የሚመካ ማንም ሰው ያለ ዋጋ እንዳያስቀራችሁ ተጠንቀቁ፤ እንዲህ ዐይነቱ ሰው ስለሚያየው ራእይ እየተመጻደቀ ከንቱና ሥጋዊ በሆነ አስተሳሰብ ይታበያል።


ከእንግዲህ ወዲህ በሰዎች የተንኰል ሽንገላና አታላይነት በተዘጋጀ በአሳሳች የትምህርት ነፋስና ሞገድ ወዲያና ወዲህ ተገፍትረው እንደሚወሰዱ ሕፃናት አንሆንም።


ሐሰተኞች መሲሖችና ሐሰተኞች ነቢያት ይነሣሉ፤ እነርሱ ቢቻላቸውስ የእግዚአብሔርን ምርጦች እንኳ ለማሳሳት ታላላቅ ተአምራትንና ድንቅ ነገሮችን ያሳያሉ።


በሰው ፊት የሚክደኝን ሁሉ ግን እኔም በሰማይ አባቴ ፊት እክደዋለሁ።


በመጀመሪያው አውሬ ፊት እንዲያደርግ በተፈቀደለት ተአምራት ምክንያት በምድር ላይ የሚኖሩትን ሰዎች ያስት ነበር፤ በሰይፍ ቈስሎ ለዳነው ለአውሬው ክብር ምስል እንዲሠሩም በምድር ላይ የሚኖሩትን ሰዎች ያዛቸዋል።


አንተ የሰይጣን ዙፋን ባለበት ስፍራ መኖርህን ዐውቃለሁ፤ ይሁን እንጂ ስሜን አጥብቀህ ይዘሃል፤ በእኔ ላይ ያለህን እምነት አልካድክም፤ ታማኝ ምስክሬ የነበረው አንቲጳስ ሰይጣን በሚኖርበት በእናንተ ከተማ በተገደለ ጊዜ እንኳ በእኔ ማመንህን አልተውክም።


እነርሱ “በመጨረሻው ዘመን ከእግዚአብሔር ፈቃድ የራቁ የገዛ ራሳቸውን ክፉ ምኞት የሚከተሉ ፌዘኞች ይመጣሉ” ብለዋችሁ ነበር።


ስለሚያታልሉአችሁ ሰዎች ይህን ጻፍኩላችሁ፤


ኢየሱስ ክርስቶስን ያላያችሁት እንኳ ብትሆኑ ትወዱታላችሁ፤ አሁን እንኳ የማታዩት ብትሆኑ ታምኑበታላችሁ፤ በቃላት ሊገለጥ በማይቻልና በከበረ ደስታ ደስ ይላችኋል።


ከእግዚአብሔር ጸጋ ሙላት የተነሣ በልጁ ደም ተዋጅተን የኃጢአታችንን ይቅርታ አገኘን።


ጣዖትን ማምለክ፥ ሟርት፥ ጠላትነት፥ ንትርክ፥ ቅናት፥ ቊጣ፥ ራስ ወዳድነት፥ መለያየት፥ አድመኛነት፥


ሌሎች ሰዎች ስለ እናንተ በመጨነቅ ያስባሉ፤ ይሁን እንጂ ይህን የሚያደርጉት ለመልካም አይደለም፤ የእነርሱ ፍላጎት እናንተ ከእኛ እንድትለዩና ለእነርሱ በትጋት እንድታስቡ ነው።


እንደእነዚህ ዐይነቶቹ ሰዎች ራሳቸውን እንጂ ጌታችንን ክርስቶስን አያገለግሉም። በለዘቡና በሚያቈላምጡ ቃላት የየዋሆችን ልብ ያታልላሉ።


ኢየሱስ እንዲህ ሲል መለሰላቸው፦ “እንዳትሳሳቱ ተጠንቀቁ! ብዙዎች ‘እኔ ክርስቶስ ነኝ! እነሆ፥ ጊዜው ቀርቦአል!’ እያሉ በስሜ ይመጣሉ፤ እነርሱን አትከተሉአቸው።


“ሰዎች ሁሉ ስለ እናንተ መልካም ሲናገሩ ወዮላችሁ! አባቶቻቸውም ለሐሰተኞች ነቢያት እንዲሁ አድርገው ነበር።


ብዙዎች ‘እኔ መሲሕ ነኝ!’ እያሉ በስሜ ይመጣሉ፤ ብዙ ሰዎችንም ያሳስታሉ።


የሠራዊት አምላክ እንዲህ ይላል፦ “ለፍርድ ወደ እናንተ እቀርባለሁ፤ በአስማተኞች፥ በዘማውያን፥ በሐሰት መስካሪዎች፥ የቀን ሠራተኞችን ደመወዝ አታለው በሚያስቀሩ አሠሪዎች፥ ባሎቻቸው የሞቱባቸውን ሴቶች፥ እናትና አባት የሌላቸው ልጆችንና ስደተኞችን በሚጨቊኑና እኔን በማይፈሩ ሰዎች ላይ ፈጣን ፍርዴን አስተላልፋለሁ።


የከተማይቱም ሹማምንት የሚፈርዱት በጉቦ ነው፤ ካህናቱ ያለ ዋጋ አያስተምሩም፤ ነቢያቱም ያለ ገንዘብ ትንቢት አይናገሩም፤ ይህም ሁሉ ሆኖ “እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ስለ ሆነ ምንም ዐይነት ክፉ ነገር አይመጣብንም” በማለት በእግዚአብሔር ይመካሉ።


እግዚአብሔር ስለ ሐሰተኞች ነቢያት እንዲህ ይላል፦ “ጥቅም የሚያገኙበት ሲሆን ‘ሰላም ይወርድላችኋል’ እያሉ ይሰብካሉ፤ ጥቅም በማያገኙበት ጊዜ ‘ጦርነት ይመጣባችኋል’ እያሉ በማወጅ ሕዝቡን ያስታሉ፤


የእናንተ ነቢያት ሐሰተኛና አታላይ ራእይ አይተውላችኋል፤ ሐሰተኛና አሳሳች ትንቢት ተናገሩ እንጂ፥ ዕድል ፈንታችሁን ለመለወጥ በደላችሁን አላጋለጡም።


“በእንጨት ላይ ተሰቅሎ የሚሞት ሁሉ የተረገመ ነው” ተብሎ ስለ ተጻፈ ክርስቶስ ስለ እኛ እንደ ተረገመ ሰው ሆኖ ሕግ ከሚያስከትለው ርግማን ዋጀን።


እግዚአብሔር በዋጋ ስለ ገዛችሁ የሰው ባሪያዎች አትሁኑ።


“አንድ ሰው ባዶ ቃላትን በመደርደር ስለ ወይንና ስለ ጠንካራ መጠጥ አስተምራችኋለሁ ቢላችሁ የዚህ ሕዝብ ነቢይ የሚሆነው እርሱ ነው።


እግዚአብሔር ለእስራኤል ሕዝብ ነቢዩ ጠባቂ እንዲሆን አድርጎታል፤ ሆኖም በመንገዱ ሁሉ ወጥመድ ተዘርግቶበታል፤ በአምላኩም ቤተ መቅደስ ጥላቻ ይጠብቀዋል።


ለመሆኑ ‘የባቢሎን ንጉሥ በአንተም ሆነ በአገርህ ላይ አደጋ አይጥልም’ ብለው የነገሩህ ነቢያትህ አሁን የት አሉ?


ራስ የተባሉት ሽማግሌዎችና የተከበሩ አለቆች ናቸው፤ ጅራት የተባሉትም ሐሰትን የሚያስተምሩ ነቢያት ናቸው።


ስለዚህ አክዓብ አራት መቶ የሚሆኑትን ነቢያቱን ጠርቶ “ወደ ራሞት ሄጄ አደጋ ልጣልባት ወይስ ልተው?” ሲል ጠየቃቸው። እነርሱም “ሄደህ አደጋ ጣልባት፤ ጌታም ድልን ያቀዳጅሃል” ሲሉ መለሱለት።


ሥራህን ዐውቃለሁ፤ እነሆ፥ ማንም ሊዘጋው የማይችለውን የተከፈተ በር በፊትህ አድርጌልሃለሁ፤ ኀይልህ ትንሽ መሆኑን ዐውቃለሁ፤ ይሁን እንጂ ቃሌን ጠብቀሃል፤ ስሜንም አልካድክም።


በሰው ፊት የሚክደኝን እኔም ደግሞ በእግዚአብሔር መላእክት ፊት እክደዋለሁ።


እናንተ ሞኞችና ኅሊና ቢሶች፥ የእግዚአብሔርን ዋጋ የምትከፍሉ በዚህ ዐይነት ነውን? እርሱ የፈጠራችሁ አባታችሁ አይደለምን? የመሠረታችሁስ እርሱ አይደለምን?


አምላክ ሆይ፥ ሕዝብህ እስኪያልፍ ድረስ፥ የተቤዠኸው ሕዝብ እስኪያልፍ ድረስ፥ ፍርሀትና ድንጋጤ ወደቀባቸው፤ በሥልጣንህ እንደ ድንጋይ ጸጥ አሉ።


ታላላቆችም ሆኑ ታናናሾች እያንዳንዱ ሰው ሕገወጥ በሆነ መንገድ ጥቅሙን ያግበሰብሳል፤ ነቢያትና ካህናት ሳይቀሩ ሕዝቡን ያታልላሉ፤


“በእግዚአብሔር ስም የሐሰት ትንቢት ቃል ስለሚነግሩአችሁም ስለ ቆላያ ልጅ አክዓብና ስለ ማዕሤያ ልጅ ሴዴቅያስ የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እንዲህ ብሎ ተናግሮአል፦ ‘እነርሱን ዐይናችሁ እያየ በፊታችሁ በሞት ለሚቀጣቸው ለባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ፤


ለራሱ ዘመዶች፥ ይልቁንም ለቅርብ ቤተሰቦቹ የማያስብ ሃይማኖቱን የካደ ነው፤ እንዲያውም ከማያምን ሰው እንኳ የባሰ ክፉ ነው።


እነርሱ በታላቅ ድምፅ “ቅዱስና እውነተኛ፥ ልዑል እግዚአብሔር ሆይ፥ በምድር ባሉት ሰዎች ላይ የማትፈርደውና ስለ ደማችንም የማትበቀለው እስከ መቼ ነው!” እያሉ ጮኹ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios