Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ራእይ 17:15 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 መልአኩም እንዲህ አለኝ፤ “አመንዝራይቱ ተቀምጣባቸው ያየሃቸው ውሃዎች፥ ሕዝቦችና፥ ሰዎች፥ ወገኖችና የተለያዩ ቋንቋዎችን የሚናገሩ ናቸው፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 መልአኩም እንዲህ አለኝ፤ “አመንዝራዪቱ ተቀምጣባቸው ያየሃቸው ውሆች፣ ወገኖች፣ ብዙ ሰዎች፣ ሕዝቦችና ቋንቋዎች ናቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 እንዲህም አለኝ “አመንዝራይቱ የተቀመጠችባቸው ያየሃቸው ውሃዎች፥ ወገኖችና ብዙ ሰዎች፥ አሕዛብም፥ ቋንቋዎችም ናቸው።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 አለኝም “ጋለሞታይቱ የተቀመጠችባቸው ያየሃቸው ውሃዎች፥ ወገኖችና ብዙ ሰዎች አሕዛብም ቋንቋዎችም ናቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 አለኝም፦ ጋለሞታይቱ የተቀመጠችባቸው ያየሃቸው ውኃዎች፥ ወገኖችና ብዙ ሰዎች አሕዛብም ቋንቋዎችም ናቸው።

Ver Capítulo Copiar




ራእይ 17:15
14 Referencias Cruzadas  

የሞት ጣር ከበበኝ፤ የጥፋት ጐርፍም አጥለቀለቀኝ።


ከባሕሩ መናወጥ የተነሣ የሚያስገመግመውን የማዕበል ድምፅ ጸጥ ታደርጋለህ፤ የሕዝቦችንም ሁከት ዝም ታሰኛለህ።


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “እነሆ፥ ውሃ ከሰሜን በኩል ተነሥቶ በጐርፍ እንደ ተሞላ ወንዝ ይፈስሳል፤ ምድርንና በምድር ላይ ያለውን ሁሉ ከተሞችንና በውስጣቸው የሚኖሩትን ሕዝብ በሙሉ ይሸፍናል። ሕዝቡ ሁሉ ርዳታ ለማግኘት ይጮኻሉ፤ በምድር ላይ የሚኖሩ ሰዎች ሁሉ ምርር ብለው ያለቅሳሉ።


አንቺ በታላላቅ ወንዞች አጠገብ የምትኖሪ ሀብታሚቱ ባቢሎን ሆይ! የተወሰነብሽ የመጥፊያሽ ዘመን ደርሶአል።


የባቢሎን ጠላቶች እንደ ውቅያኖስ ማዕበል ወጥተው ከተማይቱን አጥለቀለቋት።


እንደ ባሕር ሞገድ የሚያስገመግም ሠራዊት በድንገት በባቢሎን ላይ ደርሶ እየደነፋ አደጋ ይጥልባታል፤ በዚህም እኔ አጠፋታለሁ፤ ጸጥም አደርጋታለሁ።


እዚያም ዛፉን የሚያሳድገው በቂ ውሃ ነበረው፤ በመሬት ውስጥ ያለው ጥልቅ ውሃ ዛፉን ያሳድገዋል፤ ጅረቶችም በሜዳ በተተከሉ ዛፎች ዙሪያ ይፈስሳሉ።


ከዚህ በኋላ “ስለ ብዙ ወገኖች፥ ሕዝቦች፥ ልዩ ልዩ ቋንቋ ስለሚናገሩ ሰዎችና ስለ ነገሥታት እንደ ገና ትንቢት መናገር አለብህ” ተብሎ ተነገረኝ።


ልዩ ልዩ ወገንና፥ ነገድ፥ ልዩ ልዩ ቋንቋ ተናጋሪዎችና ሕዝቦች ሦስት ቀን ተኩል ሬሳቸውን ይመለከታሉ፤ ሬሳቸው እንዳይቀበርም ይከለክላሉ።


ሰባቱን ጽዋዎች ይዘው ከነበሩት ከሰባቱ መላእክት አንዱ ወደ እኔ መጥቶ እንዲህ አለኝ፦ “ና! በብዙ ውሃዎች ላይ በተቀመጠችው በታላቂቱ አመንዝራ ሴት ላይ የሚደርሰውን ፍርድ አሳይሃለሁ፤


አዲስ መዝሙርም እንዲህ እያሉ ዘመሩ፦ “በደምህ ከየነገዱ፥ ከየቋንቋው፥ ከየወገኑ፥ ከየሕዝቡ ሰዎችን ለእግዚአብሔር ለመዋጀት፥ አንተ ስለ ታረድህ የብራናውን ጥቅል መጽሐፍ ለመውሰድና ማኅተሞቹን ለመክፈት የተገባህ ሆነሃል፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos