Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዳንኤል 3:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 በዚያን ጊዜ አንድ ዐዋጅ ነጋሪ ድምፁን ከፍ አድርጎ እንዲህ አለ፦ “እናንተ ከልዩ ልዩ ሀገር የመጣችሁ ሕዝቦችና ልዩ ልዩ ቋንቋ የምትናገሩ ነገዶች ሆይ!

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 ከዚያም ከፍ ባለ ድምፅ እንዲህ የሚል ዐዋጅ ታወጀ፤ “ሕዝቦች ሆይ፤ መንግሥታትና ልዩ ልዩ ቋንቋ የምትናገሩ ሰዎች ሁሉ፤ እንድታደርጉ የታዘዛችሁት ይህ ነው፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 አዋጅ ነጋሪውም እየጮኸ እንዲህ አለ፦ ወገኖችና አሕዛብ በልዩ ልዩ ቋንቋም የምትናገሩ ሆይ፥

Ver Capítulo Copiar




ዳንኤል 3:4
13 Referencias Cruzadas  

ከዚህ በኋላ ንጉሥ ዳርዮስ በየአገሩ ለሚኖሩ ሕዝቦችና ልዩ ልዩ ቋንቋ ለሚናገሩ ነገዶች በጽሑፍ እንዲህ የሚል መልእክት አስተላለፈ፥ “ሰላም ለእናንተ ይሁን!


ንጉሡ ናቡከደነፆር በዓለም ሁሉ ለሚኖሩ ሕዝቦችና ልዩ ልዩ ቋንቋ ለሚናገሩ ነገዶች የሚከተለውን መልእክት አስተላለፈ፦ “ሰላም ለእናንተ ይሁን!


ይህ ሁሉ የሚደርስባችሁ የንጉሥ ዖምሪን ሥርዓት ስለ ጠበቃችሁና የንጉሥ አክዓብን አካሄድ ሁሉ ስለ ተከተላችሁ ነው፤ በእነርሱ ባህል ስለ ተመራችሁ አጠፋችኋለሁ፤ የከተማይቱን ነዋሪዎችም የሰው ሁሉ መሳቂያ አደርጋቸዋለሁ፤ በሕዝቤ ላይ የተሰነዘረውን ነቀፋ እንድትሸከሙ አደርጋችኋለሁ።”


እስራኤል ከንቱ ነገርን በመከተል ላይ ስለ ጸና ጭቈናና ፍትሕ ማጣት ደረሰበት።


መልአኩም ድምፁን ከፍ አድርጎ እንዲህ አለ፦ ‘ዛፉን ቊረጡ፤ ቅርንጫፎቹንም ጨፍጭፉ፥ ቅጠሎቹን ሸምጥጡ፥ ፍሬውንም በትኑ፥ አራዊቱ ከጥላው ሥር፥ ወፎችም ከቅርንጫፎቹ ይሽሹ።


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ድምፅህን ሳትቈጥብ ጩኽ! ድምፅህ እንደ እምቢልታ ከፍ ይበል! ለሕዝቤ ለእስራኤል ዐመፃቸውንና ኃጢአታቸውን ንገራቸው።


ለጽዮን መልካም ነገርን የምታበሥሩ ሆይ! ወደ ከፍተኛ ተራራ ውጡ! እናንተ ለኢየሩሳሌም መልካም ዜናን የምታበሥሩ ሆይ! ድምፃችሁን ከፍ አድርጋችሁ ጩኹ! ጮክ በሉ አትፍሩ! ለይሁዳ ከተሞች፥ “እነሆ፥ አምላካችሁ” በሉ።


ይህም የሆነው ሲዋን ተብሎ የሚጠራው ሦስተኛ ወር በገባ በሃያ ሦስተኛው ቀን ነበር፤ መርዶክዮስ የንጉሡን ጸሐፊዎች ሁሉ ጠርቶ ለአይሁድ፥ ከሕንድ እስከ ኢትዮጵያ ያሉትን መቶ ኻያ ሰባት አገሮች ለሚያስተዳድሩ አገረ ገዢዎችና ሌሎችም ባለሥልጣኖች የሚላኩ ደብዳቤዎችን አስጻፈ፤ ደብዳቤዎቹም በእያንዳንዱ አገር ቋንቋና የአጻጻፍ ሥርዓት እንዲሁም በአይሁድ ቋንቋና የአጻጻፍ ሥርዓት ተከትለው እንዲጻፉ ተደረገ።


አዲስ መዝሙርም እንዲህ እያሉ ዘመሩ፦ “በደምህ ከየነገዱ፥ ከየቋንቋው፥ ከየወገኑ፥ ከየሕዝቡ ሰዎችን ለእግዚአብሔር ለመዋጀት፥ አንተ ስለ ታረድህ የብራናውን ጥቅል መጽሐፍ ለመውሰድና ማኅተሞቹን ለመክፈት የተገባህ ሆነሃል፤


እነዚህ ሁሉ ባለሥልጣኖች ለምረቃው በዓል በአንድነት ተሰብስበው በምስሉ ፊት ለፊት ቆሙ፤


ስለዚህ ወገኖች፥ ከልዩ ልዩ ሀገር የመጡ ሕዝቦችና ልዩ ልዩ ቋንቋ የሚናገሩ ነገዶች ሁሉ የመለከትና፥ የእንቢልታ፥ የመሰንቆና፥ የክራር፥ የበገና፥ የዋሽንትና የሙዚቃ ሁሉ ድምፅ በሰሙ ጊዜ በመሬት ላይ ተደፍተው ንጉሡ ናቡከደነፆር ላቆመው የወርቅ ምስል ሰገዱ።


ንጉሥ ሆይ! አንተ የመለከት፥ የእንቢልታ፥ የመሰንቆ፥ የክራር፥ የበገናና የዋሽንት፥ የሙዚቃ ሁሉ ድምፅ የሚሰማ ማናቸውም ሰው በመሬት ላይ ተደፍቶ ለወርቁ ምስል እንዲሰግድ ዐዋጅ አውጥተህ ነበር።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios