መዝሙር 16:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔርን “አንተ ጌታዬ ነህ፤ ያለኝ መልካም ነገር ሁሉ ያንተ ስጦታ ነው” አልኩት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔርን፣ “አንተ ጌታዬ ነህ፤ ከአንተ በቀር በጎነት የለኝም” አልሁት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታን፦ “አንተ ጌታዬ ነህ አልሁ”፥ ከአንተ በቀር በጎነት የለኝም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ፍርዴ ከፊትህ ይወጣል፥ ዐይኖቼም ጽድቅህን አዩ። |
“አንዱ ‘እኔ የእግዚአብሔር ነኝ’ ይላል፤ ሌላው በያዕቆብ ስም ይጠራል፤ ሌላው ደግሞ ‘የእግዚአብሔር ሰው ነኝ’ ብሎ በእጁ ላይ ይነቅሳል፤ እስራኤል በሚለውም ስም ይጠራል።”
እነርሱንም ወደ እሳት እጨምራቸዋለሁ፤ ብርም በእሳት እንደሚጠራ አጠራቸዋለሁ፤ ወርቅም እንደሚፈተን እፈትናቸዋለሁ፤ ከዚያን በኋላ ወደ እኔ ይጸልያሉ፤ እኔም እመልስላቸዋለሁ። እኔ ‘ሕዝቤ’ ብዬ እጠራቸዋለሁ፤ እነርሱም ‘እግዚአብሔር አምላካችን’ ብለው ይጠሩኛል።”