Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘካርያስ 13:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 እነርሱንም ወደ እሳት እጨምራቸዋለሁ፤ ብርም በእሳት እንደሚጠራ አጠራቸዋለሁ፤ ወርቅም እንደሚፈተን እፈትናቸዋለሁ፤ ከዚያን በኋላ ወደ እኔ ይጸልያሉ፤ እኔም እመልስላቸዋለሁ። እኔ ‘ሕዝቤ’ ብዬ እጠራቸዋለሁ፤ እነርሱም ‘እግዚአብሔር አምላካችን’ ብለው ይጠሩኛል።”

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 ይህን አንድ ሦስተኛውን ክፍል ወደ እሳት አመጣለሁ፤ እንደ ብር አነጥራቸዋለሁ፤ እንደ ወርቅም እፈትናቸዋለሁ፤ እነርሱ ስሜን ይጠራሉ፤ እኔም እመልስላቸዋለሁ፤ እኔም፣ ‘ሕዝቤ ናቸው’ እላለሁ፤ እነርሱም፣ ‘እግዚአብሔር አምላካችን ነው’ ይላሉ።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 አንድ ሦስተኛውን ክፍል ወደ እሳት አስገባለሁ፤ ብርም እንደሚነጥር አነጥራቸዋለሁ፤ ወርቅም እንደሚፈተን እፈትናቸዋለሁ፤ እነርሱም ስሜን ይጠራሉ፥ እኔም እሰማቸዋለሁ፤ እኔም፦ “ይህ ሕዝቤ ነው” እላለሁ፥ እርሱም፦ “ጌታ አምላኬ ነው” ይላል።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 ሦስተኛውንም ክፍል ወደ እሳት አገባለሁ፥ ብርም እንደሚነጥር አነጥራቸዋለሁ፥ ወርቅም እንደሚፈተን እፈትናቸዋለሁ፣ እነርሱም ስሜን ይጠራሉ፥ እኔም እሰማቸዋለሁ፣ እኔም፦ ይህ ሕዝቤ ነው እላለሁ፣ እርሱም፦ እግዚአብሔር አምላኬ ነው ይላል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 ሦስተኛውንም ክፍል ወደ እሳት አገባለሁ፥ ብርም እንደሚነጥር አነጥራቸዋለሁ፥ ወርቅም እንደሚፈተን እፈትናቸዋለሁ፥ እነርሱም ስሜን ይጠራሉ፥ እኔም እሰማቸዋለሁ፥ እኔም፦ ይህ ሕዝቤ ነው እላለሁ፥ እርሱም፦ እግዚአብሔር አምላኬ ነው ይላል።

Ver Capítulo Copiar




ዘካርያስ 13:9
54 Referencias Cruzadas  

መከራ በሚደርስብህ ጊዜ ጥራኝ፤ እኔም አድንሃለሁ፤ አንተም ታከብረኛለህ።”


የጌታን ስም የሚጠራ ሁሉ ይድናል።’


እንደ ብር ሳይሆን በመከራ እሳት አንጥሬአችኋለሁ፥ በችግር እቶንም ፈትኜአችኋለሁ።


በሚጠራኝም ጊዜ እሰማዋለሁ፤ በመከራው ጊዜ ከእርሱ ጋር እሆናለሁ፤ አድነዋለሁ፤ አከብረዋለሁም።


ድል የሚነሣ ይህን ይወርሳል፤ እኔ አምላክ እሆነዋለሁ፤ እርሱም ልጄ ይሆናል፤


ወዳጆች ሆይ! እንደ እሳት በሚፈትን መከራ ውስጥ ስትገኙ ያልተለመደ እንግዳ ነገር እንደ ደረሰባችሁ አድርጋችሁ አትደነቁ፤


እነርሱ ሕዝቤ ይሆናሉ፤ እኔም አምላካቸው እሆናለሁ፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።”


በውሃ ውስጥ በምታልፉበት ጊዜ እኔ ከእናንተ ጋር እሆናለሁ፤ በወንዞች መካከል በምታልፉበት ጊዜ አያሰጥሙአችሁም፤ በእሳትም ውስጥ በምታልፉበት ጊዜ አያቃጥላችሁም፤ ነበልባሉም ዐመድ አያደርጋችሁም።


ጌታ በቃል ኪዳኑ መሠረት ለወዳጆቹ የሚሰጠውን የሕይወት አክሊል ስለሚቀበል ፈተናን ታግሦ የሚጸና ሰው የተባረከ ነው።


“እኔ የይሁዳን ሕዝብ ብርቱ አደርጋለሁ፤ የእስራኤልንም ሕዝብ እታደጋለሁ፤ ስለምራራላቸውም ሁሉንም ወደ አገራቸው እመልሳለሁ፤ ከዚህ በፊት ከቶ ጥዬአቸው እንደማላውቅ ይሆናሉ፤ እኔ እግዚአብሔር አምላካቸው ስለ ሆንኩ ጸሎታቸውን እሰማለሁ።


“እነሆ፥ ከዚህ ጊዜ በኋላ ከእስራኤል ሕዝብ ጋር የምገባው ቃል ኪዳን የሚከተለው ነው ይላል ጌታ፤ እኔ ሕጌን በአእምሮአቸው አኖራለሁ፤ በልባቸውም እጽፈዋለሁ፤ አምላካቸውም እሆናለሁ፤ እነርሱም ሕዝቤ ይሆናሉ።


እርሱ እርምጃዬን ሁሉ ያውቃል፤ ቢፈትነኝም እንደ ወርቅ ንጹሕ ሆኜ ያገኘኛል።


መልሼ በማምጣት በኢየሩሳሌም እንዲኖሩ አደርጋቸዋለሁ፤ እነርሱ ሕዝቤ ይሆናሉ፤ እኔም በእውነትና በጽድቅ አምላካቸው እሆናለሁ።


እነሆ ከዚህ ጊዜ በኋላ ከእስራኤል ሕዝብ ጋር የምገባው ቃል ኪዳን ይህ ነው፤ ሕጌን በልቡናቸው አኖራለሁ፤ በልባቸውም እጽፈዋለሁ፤ አምላካቸውም እሆናለሁ፤ እነርሱም ሕዝቤ ይሆናሉ፤


ከዚያ በኋላ ትጸልያላችሁ፤ እኔም ጸሎታችሁን እሰማለሁ፤ የእርዳታ ጩኸት ትጮኻላችሁ፤ እኔም አለሁ እላችኋለሁ፤ እናንተ የጭቈናን ቀንበር ብታስወግዱ፥ የጣት ጥቆማንና የተንኰልን ንግግር ብታቆሙ፥


እኔ ከእናንተ ጋር እሄዳለሁ፤ አምላካችሁ እሆናለሁ፤ እናንተም ሕዝቤ ትሆናላችሁ።


“በዚያን ጊዜ በዳዊት ዘሮችና በኢየሩሳሌም ነዋሪዎች ላይ የርኅራኄና የጸሎት መንፈስ እሞላለሁ፤ ይህንንም የማደርገው እነርሱ ለአንድያ ልጅና ለበኲር ልጅ እንደሚለቀስ ለወጉት ምርር ብለው እንዲያለቅሱለት ነው።


ወርቅና ብር በእሳት እንደሚፈተን እግዚአብሔርም የሰውን ልብ ይፈትናል።


እንደዚህ የሚሆንለት ሕዝብ የተባረከ ነው! እግዚአብሔር አምላኩ የሆነለት ሕዝብ የተባረከ ነው!


የእግዚአብሔርንም ስም የሚጠራ ሁሉ ይድናል፤ እግዚአብሔርም እንደ ተናገረው ከጽዮን ተራራና ከኢየሩሳሌም መዳን ይገኛል፤ ከሚድኑትም መካከል እግዚአብሔር የጠራቸው ይገኙበታል።”


እኔም በዚያ ከእነርሱ ጋር እኖራለሁ፤ እኔ አምላካቸው እሆናለሁ፤ እነርሱም ሕዝቤ ይሆናሉ።


ከዚያም በኋላ ለቀድሞ አባቶቻችሁ በሰጠኋት ምድር ትኖራላችሁ፤ እናንተ ሕዝቤ ትሆናላችሁ፤ እኔም አምላካችሁ እሆናለሁ።


በዚያን ጊዜ ሕጌን ይፈጽማሉ፤ ሥርዓቴንም ሁሉ ያከብራሉ፤ እነርሱ ሕዝቤ ይሆናሉ፤ እኔም አምላካቸው እሆናለሁ።


እነርሱ ሕዝቤ ይሆናሉ፤ እኔም አምላካቸው እሆናለሁ፤


የመጀመሪያው መልአክ መለከቱን ነፋ፤ በረዶና ደም የተቀላቀለበት እሳት ሆነ፤ ወደ ምድርም ተጣለ፤ የምድር ሢሶ ተቃጠለ፤ የዛፎችም ሢሶ ተቃጠለ፤ የለመለመ ሣርም ሁሉ ተቃጠለ።


ሁለተኛውም መልአክ መለከቱን ነፋ፤ ትልቅ ተራራ የሚመስል ነገር እየነደደ ወደ ባሕር ተጣለ፤ የባሕር ሢሶው ደም ሆነ፤


በባሕር ውስጥ ከሚኖሩት ሕይወት ካላቸው ፍጥረቶች ሢሶው ሞተ፤ የመርከቦችም ሢሶ ወደመ።


ሦስተኛውም መልአክ መለከቱን ነፋ፤ እንደ ችቦ የሚቃጠል ታላቅ ኮከብ ከሰማይ ወደቀ፤ የወደቀውም በወንዞች ሢሶና በውሃ ምንጮች ላይ ነው።


የኮከቡም ስም እሬቶ ይባላል፤ የውሃው አንድ ሦስተኛ መራራ ሆነ፤ መራራ በሆነውም ውሃ ጠንቅ ብዙ ሰዎች ሞቱ።


አራተኛው መልአክ መለከቱን ነፋ፤ የፀሐይ አንድ ሦስተኛ፥ የጨረቃ አንድ ሦስተኛ፥ የኮከቦች አንድ ሦስተኛ ተመታ፤ ስለዚህ የእነርሱ አንድ ሦስተኛቸው ጨለመ፤ በዚህ ዐይነት የቀን አንድ ሦስተኛና የሌሊት አንድ ሦስተኛ ያለ ብርሃን ሆነ።


“እኔ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ወደ ባቢሎን የላክኋቸውን ሕዝብ እንደነዚህ ጥሩ የበለስ ፍሬዎች እንደ ሆኑ እቈጥራለሁ፤


ዐመፀኞችንና የበደሉኝን ከመካከላችሁ አስወግዳለሁ፤ አሁን ከሚኖሩባቸው አገሮች አወጣቸዋለሁ፤ ነገር ግን ወደ እስራኤል ምድር እንዲመለሱ ከቶ አልፈቅድላቸውም፤ በዚያን ጊዜ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ታውቃላችሁ።”


ከጠቢባን አንዳንዶቹ ከባድ መከራ ይደርስባቸዋል፤ ይሁን እንጂ በዚህ ምክንያት ነጥረውና ጠርተው በመውጣት እንከን የሌለባቸው ይሆናሉ፤ ይህም ሁኔታ የሚዘልቀው እግዚአብሔር ያቀደው መጨረሻ ጊዜ እስከሚደርስ ነው።


ብዙዎች ነጥረውና ጠርተው በመውጣት ነውር የሌለባቸው ይሆናሉ፤ ክፉዎች ግን ምንም ስለማያስተውሉ በክፋት ላይ ክፋት እየጨመሩ ይሄዳሉ፤ የማስተዋል ችሎታ የሚኖራቸው ጠቢባን ብቻ ናቸው።


እስራኤልንም ለዘለዓለም ሕዝብህ አደረግህ፤ ጌታ ሆይ፥ አንተም አምላካቸው ሆንክ።


“በእውነቱ ማዕድን ተቈፍሮ ብር የሚወጣበትና ወርቅ የሚጣራበት ቦታ አለ።


አምላክ ሆይ! ከዚያም በኋላ ለአንተ ለምታስደስተኝ ወደ መሠዊያህ ሄጄ እሰግድልሃለሁ፤ አንተ አምላኬ ነህ፤ በገናዬን እየደረደርኩ አመሰግንሃለሁ።


ውዴ የእኔ ነው፤ እኔም የእርሱ ነኝ፤ በአሸንድዬ አበባዎች መካከል መንጋውን ያሰማራል።


ግፍን በግፍ ላይ ማታለልንም በማታለል ላይ እየጨመሩ ይሄዳሉ፤ “እኔም አምላካቸው መሆኔን ለመቀበል እምቢ ብለዋል” ይላል እግዚአብሔር።


ይህንንም የማደርገው የእስራኤል ሕዝብ ወደ እኔ የሚያደርሰውን መንገድ ከእንግዲህ ወዲህ እንዳይስቱና በበደላቸው ሁሉ ዳግመኛ ራሳቸውን እንዳያረክሱ ነው፤ በዚህም ከጸኑ እኔ አምላካቸው እሆናለሁ። እነርሱም ሕዝቤ ይሆናሉ፤” ይላል ልዑል እግዚአብሔር።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios