Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




መዝሙር 73:25 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

25 በሰማይ ከአንተ ሌላ ማን አለኝ? በምድርስ አንተን ካገኘሁ ሌላ ምን እሻለሁ?

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

25 በሰማይ ከአንተ በቀር ማን አለኝ? በምድርም ከአንተ ሌላ የምሻው የለኝም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

25 በሰማይ ከአንተ ሌላ ማን አለኝ? በምድርስ ከአንተ ጋር ሆኜ ሌላ ምን እሻለሁ?

Ver Capítulo Copiar




መዝሙር 73:25
19 Referencias Cruzadas  

ከዚህም በቀር ጌታዬን ኢየሱስ ክርስቶስን ከማወቅ የበለጠ ሌላ ምንም ነገር እንደሌለ ስለማምን ሁሉን ነገር እንደ ኪሣራ እቈጥረዋለሁ፤ ስለ እርሱም ሁሉን ነገር አጥቻለሁ። ክርስቶስንም ለማግኘት ስል ሁሉን ነገር እንደ ቤት ጥራጊ እቈጥራለሁ።


እግዚአብሔርን “አንተ ጌታዬ ነህ፤ ያለኝ መልካም ነገር ሁሉ ያንተ ስጦታ ነው” አልኩት።


ዘለዓለማዊው ፍቅርህ ከሕይወት እንኳ የሚሻል ስለ ሆነ አመሰግንሃለሁ።


እግዚአብሔር ሆይ! ዕድል ፈንታዬና ጽዋዬ አንተ ነህ፤ ድርሻዬንም አስተማማኝ ታደርገዋለህ።


ከእኔ ይልቅ አባቱን ወይም እናቱን የሚወድ፥ የእኔ ሊሆን አይገባውም፤ ከእኔ ይልቅ ወንድ ልጁን ወይም ሴት ልጁን የሚወድ፥ የእኔ ሊሆን አይገባውም።


ደስታዬ በእርሱ ስለ ሆነ እርሱም በማቀርብለት የተመስጦ ጸሎት ደስ ይበለው።


በእግዚአብሔር ደስ ይበልህ፤ እርሱም የልብህን ፍላጎት ሁሉ ይሰጥሃል።


በሰማይ እግዚአብሔርን የሚመስል የለም፤ ከሰማይ መላእክትም መካከል ከእግዚአብሔር ጋር የሚስተካከል የለም።


አምላክ ሆይ! ከዚያም በኋላ ለአንተ ለምታስደስተኝ ወደ መሠዊያህ ሄጄ እሰግድልሃለሁ፤ አንተ አምላኬ ነህ፤ በገናዬን እየደረደርኩ አመሰግንሃለሁ።


የሕይወትን መንገድ ታሳየኛለህ፤ በአንተ ፊት ሙሉ ደስታ፥ በቀኝህም የዘለዓለም እርካታ ይገኛል።


እንዲህም የሚል ከፍተኛ ድምፅ ከዙፋኑ ሲወጣ ሰማሁ፤ “እነሆ! የእግዚአብሔር ማደሪያ ከሰዎች ጋር ነው፤ ከእነርሱም ጋር ይኖራል፤ እነርሱም የእርሱ ሕዝብ ይሆናሉ። እግዚአብሔር ራሱ ከእነርሱ ጋር ይሆናል፤ አምላካቸውም ይሆናል፤


ወዳጆች ሆይ፥ አሁን የእግዚአብሔር ልጆች ነን፤ ወደፊት ምን እንደምንሆንም ገና አልታወቀም፤ ነገር ግን ክርስቶስ በሚገለጥበት ጊዜ እውነተኛ መልኩን ስለምናይ እርሱን እንደምንመስል እናውቃለን።


እግዚአብሔርን ስለሚያዩት ንጹሕ ልብ ያላቸው የተባረኩ ናቸው።


እኔ በጽድቅ ፊትህን አያለሁ፤ በምነቃበት ጊዜም የአንተን አምሳያ በማየቴ እደሰታለሁ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios