መዝሙር 10:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ንግግሩም በእርግማን፥ በሐሰትና በዛቻ የተሞላ ነው፤ ተንኰልና ክፉ ነገር በአንደበቱ ናቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አፉ መርገምን፣ ቅጥፈትንና ግፍን የተሞላ ነው፤ ሽንገላና ክፋት ከምላሱ ሥር ይገኛሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አፉ በመርገም፥ በሽንገላና በዐመፃ የተመላ ነው፥ ከምላሱ በታች ተንኰልና ክፋት አሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔር ጻድቅ ነውና፥ ጽድቅንም ይወድዳል፤ ቅንነት ግን ፊቱን ታየዋለች። |
ጠላቶቼ የሚናገሩት ሁሉ ከእውነት የራቀ ስለ ሆነ፥ ከአፋቸው እውነት አይገኝም፤ ሐሳባቸውም በተንኰል የተሞላ ነው፤ ጒሮሮአቸውም እንደ ተከፈተ መቃብር ነው፤ በምላሳቸውም ሰውን ይሸነግላሉ።
ንግግሩ እንደ ቅቤ የለዘበ ነው፤ በልቡ የሚያስበው ግን ጦርነትን ነበር አንደበቱ ከዘይት ይበልጥ የለሰለሰ ነው፤ ነገር ግን እንደ ተመዘዘ ሰይፍ ነው።
በቊጣህ አጥፋቸው፤ ፈጽመህም ደምስሳቸው፤ በዚያን ጊዜ እግዚአብሔር እስራኤልን እንደሚያስተዳድርና ግዛቱም በምድር ሁሉ እንደ ተንሰራፋ፥ ሰው ሁሉ ያውቃል።
ማንም ሰው ክስ ሲመሠርት ትክክለኛውን ጉዳይ ይዞ አይመጣም ወደ ፍርድ ሸንጎም ሲቀርብ ለሕግ ታማኝ ሆኖ አይደለም፤ እነርሱ ከንቱ በሆነ አቤቱታ ላይ ተመሥርተው ውሸትን ይናገራሉ፤ ተንኰልን አስበው በደልን ይፈጽማሉ።
እነርሱ በአንደበታቸው ሐሰት ለመናገር ዘወትር የተዘጋጁ ናቸው፤ ስለዚህም በምድሪቱ ላይ በእውነት ፈንታ ሐሰት ነግሦአል። እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ሕዝቤ ከአንዱ ኃጢአት ወደ ሌላው ኃጢአት ይተላለፋሉ፤ የእኔንም አምላክነት ዐውቀው አላከበሩኝም።”