ታዛዦችም አልሆኑም። በመካከላቸው ያደረግኸውን ተአምራት ሁሉ ረሱ፤ እልኸኞችም ሆነው፤ ወደ ግብጹ ባርነታቸው እንዲመልሳቸው መሪ መረጡ። አንተ ግን በፍቅር የተሞላህ፥ ለቊጣ የዘገየህ፥ ይቅር ባይ፥ ቸርና መሐሪ አምላክ በመሆንህ አልተውካቸውም።
ዘኍል 14:18 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ‘እግዚአብሔር በቶሎ አይቈጣም፤ ምሕረቱና ፍቅሩ የበዛ ነው፤ ኃጢአትንና ዐመፃን ይቅር ይላል፤ ነገር ግን እስከ ሦስት ከዚያም እስከ አራት ትውልድ ድረስ ልጆችንና የልጅ ልጆችን ስለ ወላጆቻቸው ኃጢአት እቀጣለሁ’ እንዳልከው፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ‘እግዚአብሔር ለቍጣ የዘገየ፣ ፍቅሩ የበዛ፣ ኀጢአትንና ዐመፃን ይቅር የሚል፣ በደለኛውን ግን ሳይቀጣ የማይተው፣ ስለ አባቶቻቸውም ኀጢአት ልጆችን እስከ ሦስትና አራት ትውልድ የሚቀጣ ነው።’ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ‘ጌታ ታጋሽና ጽኑ ፍቅሩ የበዛ፥ በደልንና መተላለፍን ይቅር የሚል፥ በደለኛውንም ከቶ የማያነጻ፥ የአባቶችን በደል እስከ ሦስትና እስከ አራት ትውልድ ድረስ በልጆች ላይ የሚያመጣ ነው።’ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔር መዓቱ የራቀ ምሕረቱ የበዛ ጻድቅ፥ አበሳን፥ መተላለፍንና ኀጢአትን ይቅር የሚል፥ ኀጢአተኞችንም ከቶ የማያነጻ፥ የአባቶችን ኀጢአት እስከ ሦስትና አራት ትውልድ ድረስ በልጆች ላይ የሚያመጣ ነው። |
ታዛዦችም አልሆኑም። በመካከላቸው ያደረግኸውን ተአምራት ሁሉ ረሱ፤ እልኸኞችም ሆነው፤ ወደ ግብጹ ባርነታቸው እንዲመልሳቸው መሪ መረጡ። አንተ ግን በፍቅር የተሞላህ፥ ለቊጣ የዘገየህ፥ ይቅር ባይ፥ ቸርና መሐሪ አምላክ በመሆንህ አልተውካቸውም።
“እናንተ ‘እግዚአብሔር በአባቶች በደል ልጆችን ይቀጣል’ ትላላችሁ፤ እስቲ እግዚአብሔር ኃጢአተኞችን ራሳቸውን ይቅጣቸው፤ ይህ ከሆነ በደለኛነታቸውን ሊገነዘቡት ይችላሉ።
ሆኖም እግዚአብሔር ለሕዝቡ ምሕረትን አደረገ፤ ኃጢአታቸውን ይቅር አላቸው እንጂ አላጠፋቸውም። ብዙ ጊዜ ቊጣውን መለሰ፤ ብዙ ጊዜም መዓቱን ገታ።
እኔ እግዚአብሔር አምላክህ እጅግ ቀናተኛ ስለ ሆንኩ ተቀርጾ የተሠራውን ማንኛውም ጣዖት አታምልክ፤ አትስገድለትም፤ እኔ የሚጠሉኝን ሁሉ እቀጣለሁ፤ ዘራቸውንም ሁሉ እስከ ሦስትና አራት ትውልድ ድረስ እበቀላለሁ።
የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር የሕዝቡ ጠባቂዎች መሆን ስለሚገባቸው መሪዎች እንዲህ ይላል፦ “ሕዝቤን እንደሚገባ አልጠበቃችሁም፤ ይልቁንም አሳዳችሁ በተናችሁ፤ ስለዚህ ስለ ፈጸማችሁት ክፋት ሁሉ እቀጣችኋለሁ።
ለብዙ ሺህ ሕዝብ ዘለዓለማዊ ፍቅርህን አሳይተሃል፤ ይሁን እንጂ አባቶቻቸው በሠሩት ኃጢአት ምክንያት ልጆቻቸውን ትቀጣለህ፤ አንተ ታላቅና ኀያል አምላክ ነህ፤ አንተ ሁሉን ቻይና ስምህም የሠራዊት ጌታ ነው፤
እንዲህም ሲል ወደ እግዚአብሔር ጸለየ፦ “እግዚአብሔር ሆይ! አንተ ይህን እንደምታደርግ ገና በአገሬ ሳለሁ ተናግሬ አልነበረምን? ከፊትህ ኰብልዬ ወደ ተርሴስ ለመሄድ ያቀድኩትም በዚህ ምክንያት ነበር፤ አንተ ቸርና ይቅር ባይ፥ ታጋሽና ምሕረትህ የበዛ፥ በዘለዓለማዊ ፍቅር የተመላህ፥ ቊጣህን መልሰህ ምሕረት የምታደርግ አምላክ መሆንህን ዐውቅ ነበር።
ኃጢአትን ይቅር የሚል፥ በቀሪውም ሕዝቡ ላይ በደልን የማይቈጥር እንደ አንተ ያለ አምላክ ማን ነው? ምሕረት ማድረግ ስለሚያስደስትህ ቊጣህ ለዘለዓለም የሚቈይ አይደለም።
በእስራኤል ሕዝብ ላይ ክፉ አጋጣሚ ወይም ችግር እንደማይደርስባቸው ይታያል፤ እግዚአብሔር ከእነርሱ ጋር ነው፤ እግዚአብሔር ንጉሥ መሆኑንም በይፋ ይናገራሉ።
ይህም የሆነው በሞት ምክንያት ኃጢአት እንደ ነገሠ ሁሉ እንዲሁም በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት ዘለዓለማዊ ሕይወት እንዲገኝ የእግዚአብሔር ጸጋ ጽድቅን በመስጠት ይነግሣል።
እኔ አምላክህ እግዚአብሔር፥ እኔን ትተው ሌሎች አማልክትን የሚያመልኩትን ሰዎች፥ የአባቶችን ኃጢአት በልጆች፥ እስከ ሦስት ትውልድ ድረስ የምበቀል ቀናተኛ አምላክ ስለ ሆንኩ እነዚያን የተቀረጹ ምስሎች አትስገድላቸው፤ አታምልካቸውም።
ስለዚህ እግዚአብሔር አምላካችሁ በፍጹም የታመነ አምላክ መሆኑን አስታውሱ፤ እርሱ ቃል ኪዳኑን ይጠብቃል፤ ለሚወዱትና ትእዛዞቹንም ለሚፈጽሙ ሁሉ እስከ ሺህ ትውልድ ድረስ ዘለዓለማዊ ፍቅሩን ያሳያል።